2022 (እ.አ.አ)
የቤት ምሽት ምንድን ነው?
ነሐሴ 2022 (እ.አ.አ)


“የቤት ምሽት ምንድን ነው?” ሊያሆና፣ ነሐሴ 2022(እ.አ.አ)

ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ነሐሴ 2022(እ.አ.አ)

የቤት ምሽት ምንድን ነው?

ምስል
እናት፣ አባት፣ እና ትንሽ ሴት ልጅ ደጅ ተቀምጥው

የቤት ምሽት ቤተሰባችሁ የሚሰበሰብበት በሳምንቱ ውስጥ የተለየ ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ፣ “ስለወንጌል መማር፣ ምስክርነቶችን ማጠናከር፣ አንድነትን መገንባት እና እርስ በእርስ መደሰት” ትችላላችሁ (General Handbook: Serving in The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints, 2.2.4, ChurchofJesusChrist.org)። የቤት ምሽት ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የተለየ ይመስላል። ነገር ግን አላማው ይህን ጊዜ ተጠቅሞ አንዳችሁ ወደሌላችሁ እንዲሁም ወደ አዳኙ ለመቅረብ ነው።

ዝግጅት

ቤተሰባችሁ የሚወደውን ተግባር እንዲሁም አብረው ሊወያዩበት እና ሊማሩበት የሚፈልጉትን የወንጌል ርዕስ አስቡ። በተጨማሪም፣ በእያንዳንዱ ሳምንት አብዛኛው ወይም ሁሉም የቤተሰብ አባላት ሊገኙ የሚችሉበትን ቀን እና ሰአት ምረጡ። አባላት በሰኞ ምሽቶች የቤት ምሽት እንዲያደርጉ ቤተክርስቲያኗ ታበረታታለች። ነገር ግን ቤተሰቦች ለእነርሱ ምቹ በሆነው ጊዜ መሰብሰብ ይችላሉ።

ምስል
ቤተሰብ እየጸለየ

ጸሎት

ብዙ ቤተሰቦች የቤት ምሽትን በጸሎት ጀምረው በጸሎት ያጠናቅቃሉ። ይሄ መንፈስ ቅዱስን ወደ ቤታቸው ይጋብዛል። የቤት ምሽት፣ ልጆች እና ጎልማሶች አነስ ባለ ቡድን ውስጥ መጸለይን ለመማር አመቺ ጊዜ ነው።

መዝሙር

ብዙ ቤተሰቦች የመክፈቻ እና የመዝጊያ መዝሙርም ይዘምራሉ። ብዙውን ጊዜ ከመዝሙር መጽሐፍ ወይም ከልጆች የመዝሙር መጽሐፍ መዝሙርን ይመርጣሉ። ቤተክርስቲያኗ በ music.ChurchofJesusChrist.org ላይ የመዝሙሮች ፒያኖ ቅጂዎች አሏት። በቤተመቅደስ አደባባይ የተበርናክል መዘምራን ቪድዮዎችን ማየትም ትችላላችሁ። በቤት ምሽት ወቅት መዘመር አባላት በቤተ ክርስቲያን የሚዘመሩትን መዝሙሮች እንዲማሩ ይረዳል።

ትምህርት

ቤተክርስቲያን ለቤት ምሽት የሚረዱ ብዙ የመረጃ ምንጮች አሏት። ከ ሊያሆና፣ የ ጓደኛ፣ ወይም ለወጣቶች ጥንካሬላይ ጽሁፍ ለማንበብ እና ለመወያየት ጥቂት ደቂቃዎችን ልትወስዱ ትችላላችሁ። ይህ የቤተክርስቲያን ቪዲዮዎችን የመመልከቻ እና የመወያያ ጊዜ ሊሆንም ይችላል። ወይም ከጠቅላላ ጉባኤ የተወሰደ ንግግር ማንበብ ወይም ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ማንበብ ወይም ከ ኑ፣ ተከተሉኝ ውስጥ የዚያን ሳምንት ንባብ መወያየት ትችላላችሁ።

ምስል
ልጆች ብስኩቶችን እየሰሩ

ልጆች ብስኩቶችን እየሰሩ የሚያሳይ ፎቶ በ ሚሼል ልኦይንስ

የቤተሰብ ተሳትፎ

ልጆች በቤት ምሽት ሊሳተፉ ይችላሉ። ድርጊቶችን በማቀድ፣ በመጸለይ፣ ወይም መዝሙሮችን በመምረጥ እና በመምራት ሊያግዙ ይችላሉ። ትምህርቶችን ሊያስተምሩም ይችላሉ። ከቤት ምሽት በፊት፣ ልጃችሁ ከ ጓደኛ መጽሄት ወይም ከሚወደው የቅዱሳት መጻህፍት ታሪክ ላይ አንድ ታሪክ እንዲያነብ መርዳት ይችላሉ። ልጁ ያን ታሪክ እንደትምህርት ለቤተሰቡ መንገር ይችላል። ብዙ ልጆች ለቤት ምሽት የቅዱሳት መጻህፍት ታሪኮችን መተወንም ይወዳሉ። ተለቅ ያሉ ልጆች ትምህርቱን እንዲያቅዱ ወይም ማንበብ የሚፈልጉትን ከጠቅላላ ጉባኤ ንግግር እንዲመርጡ ፍቀዱ። ከዚያም ውይይቱን እንዲመሩ አድርጓቸው።

እንቅስቃሴዎች

ብዙ ቤተሰቦች እንቅስቃሴዎችን እንደ የቤት ምሽት አካል በማድረግ ይደሰታሉ። የቤት ውስጥ እንቅስቃሴዎች ጨዋታዎችን መጫወትን፣ የእጅ ስራዎችን መስራትን ወይም አብሮ ማብሰልን ሊያካትቱ ይችላሉ።

ከቤት ውጭ ለሆኑ እንቅስቃሴዎች በእግር መሄድ፣ የቤተሰብ የእግር ሽርሽር ማድረግ ወይም ከቤት ውጭ ስፖርት መጫወት ትችላላችሁ። ሁሉም የቤተሰብ አባላት ሊያደርጉት እና በጋራ ሊደሰቱ የሚችሉበት እንቅስቃሴን ፈልጉ። መንፈስን ሊያርቁ የሚችሉ የውድድር ሁኔታዎችን አስወግዱ።

አገልግሎት

የቤት ምሽት ቤተሰቦች ሌሎችን ለማገልገል የሚችሉበት ትልቅ ጊዜ ነው። ለምሳሌ፣ አንዳንድ በዕድሜ የገፉ ጎረቤቶችን መርዳት፣ በቤት አልባ መጠለያ ውስጥ ለሚኖሩ ምግብ ማቅረብ፣ ለሚስዮናውያን መጻፍ ወይም ቆሻሻን በማንሳት ልታግዙ ትችላላችሁ።

አትም