2022 (እ.አ.አ)
“ለልኡሉ አክብሮታችንን ለመስጠት”
ነሐሴ 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ አመራር መልእክት

“ለልኡሉ አክብሮታችንን ለመስጠት”

የሰንበት ቀኑን እየጠበቅን ስለመሆናችን ለጌታ ምን አይነት ምልክት እያሳየነው ነው?

ከብዙ አመታት በፊት በ1960ዎቹ ውስጥ ወጣት ልጅ በነበርኩበት ጊዜ በእያንዳንዱ እሁድ ከቤተሰቤ ጋር ቤተክርስቲያን እካፈል ነበር። በዛን ጊዜ በሰንበት ትምህርት ቤት ጠዋት እንካፈልና የቅዱስ ቁርባን ስብሰባን ደግሞ ረፋድ ከሰአት ላይ እንካፈል ነበር። የትንሾች የሰንበት ክፍል ፤ የህጻናት ክፍል ውስጥ ከሌሎች ልጆች ጋር ቁጭ ብዬ “ክርስቶስም አንዴ ህጻን ነበር”፣ “በድጋሜ መቼ እንደሚመጣ አስባለሁ”፣ እና “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ” የመሳሰሉትን መዝሙሮች ስንዘምር አስታውሳለሁ። አንድ እሁድ ጠዋት ላይ ከሌሎች ልጆች ጋር እየዘመርኩ ሳለሁ ልቤን የጋለ ስሜት ሲሞላው ተሰማኝ። ለነፍሴ ሰላምን ያመጣ የጋለ ስሜት ነበር። ከልቤ ወደ ደረቴ ሄደና ከዛ ሙሉ ሰውነቴን ሞላው። በዛ ጊዜ አባት እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ አና እንደሚያውቀኝ፤ መንፈስ ቅዱስ እየመሰከረልኝ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የመጀመሪያ ልምዴ ተሰማኝ። ከሀምሳ አመታት በኋላ በግልጽ የማስታውሰው ቀላል ነገር ግን ለኔ ጣፋጭ ልምድ ነበር።

በሰንበት ቀን ወደ እግዚአብሔር በሚያቀርቡን እንቅስቃሴዎች ውሰጥ ስንሳተፍ አፍቃሪ የሰማይ አባት ከኛ ጋር እንዲነጋገር—እኛን እንደሚያውቀን እና የሚያስፈልገንን እንደሚያውቅ እንዲያሳውቀን በሩን እንከፍታለን።እንዲህ ብሏል “ወደ እኔ ቅረቡ እና እኔም ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ ተግታችሁም ፈልጉኝ እናም ታገኙኝማላችሁ፤ ለምኑ፣ እናም ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችሁማል።”1

የሰንበት ቀንን ቀድሰን ስንጠብቅ የሰማይ አባት ህይወታችንንም አንዲባርክ በር እንከፍታለን። “የድካም መንፈስ ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ አካለ ስንኩል ያደረጋት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም ከመጒበጧ የተነሣ ፈጽሞ ቀና ማለት አትችልም ነበር።”2. በሉቃስ ወንጌል ውስጥ የዚችን ሴት ልምድ እንማራለን። ከህመሟ ጋር ሆና እንኳን ቤተክርስቲያን በመሄድ (በዚ ሁኔታ ሲሆን ምኩራብ) በመሄድ እግዚአብሔርን በሰንበት ቀን ታመልክ ነበር። በጭንቅላቴ አይን ወደምኩራቡ ለመራመድ በአካላዊ መልኩ ስትቸገር አስባለው። አንድ ቀን ይህች ሴት በታማኝነት ቤተክርስቲያን ስትካፈል ክርስቶስ ገባና አያት “ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፣ አንቺ ሴት፤ ከሕመምሽ ነጻ ወጥተሻል አላት፤

“እጁንም በላይዋ ጫነ፤ እርሷም ወዲያው ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች”።3

በቀድሞ ህመሟ ሳቢያ ከዛ በኋላ አልተቸገረችም። በታማኝነት እግዚአብሔርን እያመለከች ነበር እናም በአፍቃሪ የሰማይ አባቷ ሰአት መሠረት ተፈወሰች። የዛን ቀን ቤተክርስቲያን ባትካፈል ኖሮ ትፈወስ ነበር? ቤተክርስቲያንን በመካፈል እናንተ እና እኔ መዳን እንችላለን? ቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔር በአካላዊ እና በመንፈሳዊ ለመፈወስ ሀያል እንደሆነ ያስተምሩናል። ከእግዚአብሔር ጋር ሁሉም ነገር ይቻላል4—ነገር ግን በሱ ፍቃድ እና ሰአት መሠረት ነው።

በጥረቱ ሁሉ መጨረሻ እግዚአብሔር ይህችን ውብ ምድር ሲፈጥር ከስራዎቹ አረፈ። ሰባተኛውን ቀን የተቀደሰ ቀን፤ ሀሳቦቻችንን እና ትጋታችንን ወደሱ ልናዞር የሚገባበት ቀን አደረገው። የሰንበት ቀንን ቀድሰን እንድንጠብቅ አዞናል። “በእውነት ከስራህ እንድታርፍ እናም ለልዑልም አምልኮህን እንድትሰጥ ይህ ቀን ተሰጥቶሀልና”5። ኘሬዘደንት ኔልሰን የሰንበት ቀንን ቀድሰን እየጠበቅን ስለመሆኑ ለጌታ ምን አይነት ምልክት እያሳየን እንደሆነ እንድናስብ ጋብዘውናል6። የሰንበት ቀንን አስመልክቶ ትእዛዙን እየጠበቅን መሆኑን ለእግዚአብሔር ለማሳየት ሰንበት ቀን ምን እያደረግን ነው?

አምልኳችንን ለእግዚአብሔር የምናሳይበት አንዱ መንገድ እሱን በማምለክ ነው። በኦርጅናል ትርጉሙ “አቮዳ” የሚለው የእብራይስጥ ቃል ስራ፣ አምልኮ፣ እና አገልግሎት ማለት ነው እናም በእየሩሳሌም ቤተመቅደስ ውስጥ የሚቀርቡትን መስዋእቶች ያሳያል። እግዚአብሔርን ስናመልክ እናገለግለዋለን፣ እና ጥሪዎቻችንን ማጉላትን ጨምሮ የሱን ስራ እንሰራለን። ቤተክርስቲያን ስንካፈልና በብቁነት ቅዱስ ቁርባን ስንወስድ እግዚአብሔርን እያመለክን ነው። የተሻለ የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንዲሆኑ ለመርዳት፣ አጠገባችን ያሉትን ስናገለግል እግዚአብሔርን እያገለገልን ነው። “እናንተ ሰዎችን በምታገለግሉበት ጊዜ እግዚአብሔርን ብቻ እያገለገላችሁ” ነው7. እግዚአብሔርን በማምለክ የሰንበት ቀንን ቀድሰው ለሚጠብቁ እሱ ጠንካራና ግልጽ ቃልኪዳን ይሰጣል—እናም እግዚአብሔር ቃልኪዳኖቹን ሁሌም ይጠብቃል። ይህንም ይነግረናል “ይህን ነገር ካደረግህ፣ የምድር ሙላት፣ሁሉ የአንተ ይሆናሉ” ፤ “ከአለም ነገሮች ንጹህ” ሆነን እንደምንጠበቅ፣ ደስታ(ችን)” ሙሉ እንደሚሆን፣ እንዲሁም “በዚህ አለም ሰላም፣ እና በሚመጣው አለምም ዘለአለማዊ ህይወትን እንደምንቀበል ይነግረናል” (ት እና ቃ 59:9፣ 13፣ 16፣ 23)።

በጥቅምት 2021(እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ኘሬዘደንት ኔልሰን ቀጣዩን ምክር ሰተዋል፦ “ትኩረታችሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ከማስተካከል የበለጠ መንፈስን የሚጋብዝ ነገር የለም። ስለ ክርስቶስ ተናገሩ፣ በክርስቶስ ደስ ይበላችሁ፣ የክርስቶስን ቃሎች ተመገቡ፣ እናም በክርስቶስ ጽናት ወደፊት ቀጥሉ። እርሱን በማምለክ፣ ቅዱስ ቁርባንን በመካፈል፣ እና ቀኑን ቅዱስ አድርጋችሁ በመጠበቅ ሰንበታችሁን አስደሳች አድርጉ።”8

ይህን በምታነቡበት ስአት አግዚአብሔርን ስለምታሳዩት ምልክት ምን ሀሳቦች ወደናንተ መጡ? በነዛ ሀሳቦች ላይ አንድትሰሩ እጋብዛችኋለሁ። እንደ እግዚአብሔር ምሪት የሰንበት ቀንን ቀድሳችሁ ስትጠብቁ ፥ አካላዊና መንፈሳዊ በረከቶች ህይወታችሁ ውስጥ ይፈሳሉ ።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥63።

  2. ሉቃስ 13፥11 ይመልከቱ።

  3. ሉቃስ 13፥12–13።

  4. የማቴዎስ ወንጌል 19፥26፣ የማርቆስ ወንጌል 10፥27 ይመልከቱ።

  5. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥10።

  6. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ሰንበት ደስታ ናት”፣ ሚያዚያ 2015(እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ይመልከቱ።

  7. ሞዛያ 2፥17።

  8. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለጌታ ግዜ ስጡ”፣ ጥቅምት 2021 እ.አ.አ አጠቃላይ ጉባዔ።

አትም