2022 (እ.አ.አ)
የፓትርያርክ በረከታችሁን መቀበል
ነሐሴ 2022 (እ.አ.አ)


የቃል ኪዳን ጉዞዬ

የፓትርያርክ በረከታችሁን መቀበል

የራሳችሁ የግል ሊያሆና ይጠብቃችኋል!

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን (1927–2018) እንዲህ ብለዋል፣ “የፓትርያርክ በረከታችሁ ቃል በቃል የዘላለም እድሎቻችሁን ከያዘው መፅሐፋችሁ ውስጥ የተወሰዱ ምዕራፎችን ይዟል።…

“ልታነቡት… ልትወዱት… ልትከተሉት ይገባል። ለእናንተ የግል ሊያሆናችሁ ነው… በህይወት ውስጥ ባሉ አደጋዎች መካከል ይመራችኋል። በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የነገሮችን እውነታ ወደማወቅ ይመራችኋል።

“በዚህ ህይወት ወደሰላም የምትሄዱበት ፓስፖርታችሁ ነው።”1

እያንዳንዱ ብቁ የሆነ የተጠመቀ አባል የፓትርያርክ በረከት የማግኘት መብት አለው፤ እንዲሁም ሊኖረውም ይገባል። በረከታችሁ ዘላለማዊ እና ቅዱስ ነው። ለእናንተ በግልጽ የመጣ መገለጥ ነው። እንዲሁም በእስራኤል ቤት ውስጥ ያላችሁን የዘር ግንድንም ያውጃል።

የፓትርያርክ በረከት የሚሰጠው በተለይ ለዚህ ቅዱስ ጥሪ በተመረጠ እና በተሾመ የክህነት ተሸካሚ ነው። የእርሱ ኃላፊነት የሰማይ አባትን ማዳመጥ እና ዝግጁ በሆናችሁበት ጊዜ የእናንተን ልዩ በረከት መስጠት ነው። የእናንተ ሃላፊነት ስለፓትርያርክ በረከቶች መማር፣ የፓትርያርክ በረከታችሁን ለመቀበል መቼ ዝግጁ እንደምትሆኑ መወሰን ከዚያም የግል በረከታችሁን እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ ለማወቅ ኤጲስ ቆጶሳችሁን ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንታችሁን ማግኘት ነው።

የፓትርያርክ በረከት በየቀኑ ሊረዳችሁ እና ሊመራችሁ ይችላል። እነዚህ ምስክርነቶች ያበርቷችሁ፦

በናይሮቢ ኬንያ ዌስት ካስማ የካቢሪያ ቅርንጫፍ አባል የሆነችውን አሚያ ኢኖትን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ስሄድ፣ በጸጥታ ፈገግ አለች እና እንዲህ አለች “ኦ፣ ስለፓትርያርክ በረከቴ እያሰብኩኝ ነበር! አውጥቻቸው በነበሩት አንዳንድ ግቦች ላይ እድገት እያደረግሁ አልነበረም እናም ትኩረቴን ወደዚያ ለመመለስ እችል ዘንድ በረከቴን ለማንበብ ሄድኩ። በሕይወቴ ውስጥ በእውነት አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ያስታውሰኛል። ከዚያም እንዴት ወደፊት መጓዝ እንዳለብኝ ለማየት እችላለሁ።ከኔ የሚፈለግብኝን ካደረኩ ብዙ አስደናቂ በረከቶች ቃል ተገብተውልኛል። በረከቴ ለእኔ እንደ ሊያሆና ነው።”

በዲአርሲ ኪንሻሳ ንጋሊኤማ ካስማ ውስጥ የማንጉንጉ አጥቢያ አባል የሆነችው ሄሪትየር ቡካሳ እንዲህ ብላለች “በረከቴን ከተቀበልኩኝ በኋላ ለህይወቴ መመሪያ ሆነልኝ። ትንሽ በትንሽ በረከቶቹን እና ቃል ኪዳኖቹን በእኔ እና በወጣት ቤተሰቤ ህይወት ውስጥ ሲከሰቱ አያለሁ። በጣም አመስጋኝ ነኝ።”

በኬንያ የናይሮቢ ጋስት ስቴክ የካዮሌ የመጀመሪያ አጥቢያ አባል የሆነው ሃሮን ካምቶ እንደ አዋቂ በረከቱን በ2012 (እ.አ.አ) ተቀበለ። “የፓትርያርክ በረከቴን ወደቤተመቅደስ ልሄድ ስል እንደዝግጅቴ አካል ተቀበልኩኝ።በወቅቱ መንፈሱ በጣምተሰማኝ እንዲሁም ምክር ለማግኘት፣ ለመጽናናት፣ ለመበረታታት፣ በችግር ጊዜ ማጽናኛ ለማግኘት እና ምሪትን ለመቀበል ባነበብኩት ቁጥር ያው ጠንካራ መንፈስ ይሰማኛል፤ ስለዚህም እነዚህ የጌታ ቃላት እንደሆኑ እንዲሁም ለእኔ የተገቡ ቃልኪዳኖች መሆናቸውን እመሰክራለሁ።”

የሰማይ አባት በስጋዊ ህይወት ውስጥ ይረዳን ዘንድ ለእያንዳንዳችን የግል በረከት ሰጥቶናል።ለዚያ በረከት መዘጋጀት እና በረከቱን መፈለግ የአንተ እና የእኔ ጉዳይ ነው። እያንዳንዳችን የየራሳችን ሊያሆና ያስፈልገናል።

ማስታወሻዎች

  1. ቶማ ኤስ ሞንሰን፣ “የፓትርያርክ በረከታችሁ”, ኢንዛይን፣ ጥቅምት 1986(እ.አ.አ)።

አትም