2022 (እ.አ.አ)
የአካባቢ አመራር ሀላፊነቶች
ነሐሴ 2022 (እ.አ.አ)


የመመሪያ መጽሃፍ ጎላ ጎላ ያሉ ነጥቦች

የአካባቢ አመራር ሀላፊነቶች

ስለአዲሱ የአካባቢ አመራር ካነባበችሁ ምን እንደሆነ አስባችሁ ይሆናል። የአጠቃላይ መመሪያ መጽሀፍ ስለነዚህ በአካባቢ ደረጃ ቤተክርስቲያኗን ስለሚመሩ የክህነት ተሸካሚዎች ትንሽ በተጨማሪ ይነግረናል።

ቤተክርስቲያኗ መላውን አለም በሚሸፍኑ መልክአምድራዊ አካባቢዎች ተዋቅራለች።

በያንዳንዱ አካባቢ ውስጥ አጠቃላይ የሰባዎች ባለስልጣን በቀዳሚ አመራር እና በአስራሁለቱ ሀዋሪያት እንደ አካባቢ ፕሬዘዳንት እንዲያገለግል ይመረጣል። አጠቃላይ የሰባዎች ባለስልጣን ወይም የአካባቢ ሰባዎች የሆኑ ሁለት አማካሪዎች ፕሬዘዳንቱን እንዲያግዙ ይመረጣሉ።

“የአካባቢው አመራር የአካባቢውን የካስማ እና የሚስዮን ፕሬዘዳንቶች ይመራል እንዲሁም ያማክራል። በተጨማሪም የቤተመቅደስ ፕሬዘዳንቶችን እና ሜትረኖችን ያግዛሉ።

“የአካባቢ አመራር አባላት ለማገልገል፣ ለማስተማር እና የአካባቢ መሪዎችን፣ ሚስዮናዊያንን እና የቤተክርስቲያን አባላትን ለማበረታታት በተመደቡበት ክልል ውስጥ ይጓዛሉ። የካስማ ጉባኤዎችን እና ሌሎች ስብሰባዎችን እንዲመሩ በአስራሁለቱ ሀዋሪያት ቡድን ይመደባሉ።”

የአካባቢ አመራሩ የሰባዎችን ስልጣን የያዙ የመልከጸዲቅ የክህነት ስልጣን ተሸካሚዎችን ይይዛል። “በመልከጸዲቅ የክህነት ስልጣን ውስጥ የሰባዎቹ ስልጣን በብሉይም በአዲስ ኪዳንም ውስጥ ተጠቅሷል” በማለት የአጠቃላይ መመሪያዎች መጽሀፍ ይነግረናል ዘጸአት 24:1, 9–10፤ (ሉቃስ 10:1, 17 ይመልከቱ)።

ዛሬ ላይ አጠቃላይ የሰባዎች ባለስልጣናት እና የአካባቢ ሰባዎች አሉ። በአስራሁለቱ ሃዋሪያት ቡድን ቁልፍና አመራር ስር ይሰራሉ። በሁሉም አገራት ቤተክርስቲያኗን በመገንባት እና በመቆጣጠር ረገድ አስራሁለቱን ያግዛሉ። (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 107:34–35, 38 ይመልከቱ)።

አጠቃላይ የሰባዎች ባለስልጣናት በቤተክርስቲያን ውስጥ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ይሰጣሉ። 70 አመት ሲሞላቸው ከጥሪያቸው ይለቃሉ እናም የክብር የኢሜሪተስ ስም ይሰጣቸዋል። የሰባዎች አባልነታቸውን እንደያዙ ቢቀጥሉም ስብሰባዎችን አይመሩም።

ስለአካባቢ አመራሮች የበለጠ ለመማር ወደ አጠቃላይ መመሪያዎች ይሂዱ፦

  • በስልካችሁ ላይ Gospel Library መተገበሪያ ላይ ያግኙት፤ Handbooks and Callings የሚለውን ይጫኑ እና በመቀጠል General Handbook የሚለውን ይጫኑ።

  • https://www.churchofjesuschrist.org/study/manual/general-handbook/title-page?lang=eng ላይ ያግኙት።

አትም