2022 (እ.አ.አ)
በሴራልዮን ውስጥ የመሰረት ድንጋይ መጣል
ነሐሴ 2022 (እ.አ.አ)


መስመር ላይ

በሴራልዮን ውስጥ የመሰረት ድንጋይ መጣል

በሴራልዮን ውስጥ ያሉ አባላት በመጋቢት ላይ ታሪካዊ የሆነ ጊዜን አከበሩ። በዚያ የምእራብ አፍሪካ ምድር አፈር ላይ ለሚገነባው የመጀመሪያ ቤተመቅደስ የመሰረት ድንጋይ ተጣለ።

የቤተክርስቲያኗ የምእራብ አፍሪካ አካባቢ ፕሬዘዳንት የሆነው ሽማግሌ ሁጎ ኢ. ማርቲኔዝ በምረቃው ጸሎታቸው ላይ “እንደ ልጅህ እየሱስ ክርስቶስ ተከታይነታችን አንተን የሚያስደስት ህይወትን እንድንኖር ባርከን።”

“ሁሉም ብቁ አባላት በበሮቹ ገብተው በዘላለማዊው የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውሰጥ ከሚካተቱት ጉዳዮች ሁሉ ታላቅ በሆነው ለዘሮቻቸው የውክልና ስርአቶችን በመፈጸም ሌሎችን ያገልግሉ። እንደዘላለማዊ ቤተሰቦች ወዳንተ መገኛ እንዲመለሱ መንፈስህ ይሰማቸው እናም እውቀትንና ምሪትን ያግኙ”ብለው ጸልየዋል።”

እመቤት ናቢላ ፋሪዳ ቱኒስ የሴራልዮን ምእራባዊ ክልል ሚኒስቴር በዝግጅቱ ላይ ታድመው ነበር። “ይህን ቤተክርስቲያን እና ቤተመቅደስ ወደሀገራችን ለማምጣት ላደረገው ጥረት ከልቤ አመሰግናለው። እግዚአብሄር ይህን ቤተክርስቲያን ይባርክ። እግዚአብሄር ሁላችንንም ይባርክ። እግዚአብሄር ሴራልዮንን ይባርክ”ብላ ተናግራለች።”

https://news-africa.churchofjesuschrist.org/ ላይ ምስሎችን ይመልከቱ እናም የበለጠ ያንብቡ።

አትም