2022 (እ.አ.አ)
የሰንበትን ቀን መቀደስ
ነሐሴ 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ መሪ መልእክት

የሰንበትን ቀን መቀደስ

አንድ እሁድ ጠዋት ቤተክርስቲያን እየሄድን እያለ በዛን ሰአት 6 አመቱ የነበረው ልጃችን ስቲቨን አንዳንድ ወጣቶች በመንገዳችን ላይ ኳስ ሲጫወቱ ተመልክቶ ለራሱ እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሰዎች ቤተክርስቲያን መካፈል ሲገባቸው በእሁድ ለምን ኳስ ይጫወታሉ!” ልጃችን እሁድ የሆኑ ነገሮችን እንድናደርግ የሚጠበቅብን ልዩ ቀን ስለመሆኑ እና ስለዚህም ከሌሎች ነገሮች መራቅ እንደሚጠበቅብን እንደሚያውቅ ግልጽ ነበር። ስቲቨን እሁድ የጌታ ቀን እንደሆነና ቀድሰን ልንጠብቀው እንደሚገባን ያውቅ ነበር።

በዘጸአት 20፥8 ላይ “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ” የሚለውን እናነባለን። በእብራይስጥ ሰንበት የሚለው ቃል እረፍት ማለት ነው።እሁድ (የጌታ) የእረፍት ቀን መሆኑን፣ እሱ ከሁሉም ስራው በሰባተኛው ቀን ስላረፈ ቀድሰን ልንጠብቀው አንደሚገባን ማስተዋል አስፈላጊ ነው1። በአጠቃላይ እሁድን እንደ እረፍት ቀናችን አስበን እና የምር እረፍት መዉሰድ ፈታኝ ሊመስል ይችላል ነገር ግን ቀድሶ መጠበቅ ይጠበቅብናል።

በአስራሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ ውስጥ በማገለግልበት ሰአት ፕሬዚደንት ረስል ኤም ኔልሰን ቀጣዩን ጥያቄ መልሰዋል፦ “እንዴት ነው የሰንበት ቀንን የምንቀድሰው?” እንዲህ አሉ “በጣም ወጣት በነበርኩበት አመታት በሰንበት ማድረግ ያለብኝን እና ማድረግ የሌለብኝን ነገሮች ዝርዝር ሌሎች ሰዎች አሰባስበው ካስቀመጡት ላይ ነበር ያጠናሁት። ከጊዜ በኋላ ነበር በሰንበት ቀን ላይ ያለኝ ተግባር እና ጸባይ በሰማይ አባቴና በኔ መሀከል ምልክትን እንደያዘ ከቅዱስ መጻሕፍት የተማርኩት። በዛ አረዳድ ከዛ በኋላ አድርግ እና አታድርግ የሚል ዝርዝር አላስፈለገኝም።”2

ይህ የፕሬዝዳንት ኔልሰን አስተምሮ በዘጸአት 31:13 ላይ ያለውን ጥቅስ ያመለክታል እንዲህም ይላል “ሰንበቴን ማክበር አለባችሁ፤ ይህም ምልክት ይሆናል፤ ይኸውም የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ እንድታውቁ ነው።” ፕሬዝዳንት ኔልሰን በሰንበት ቀን ላይ ያለው ተግባር እና ጸባይ በሰማይ አባቱና በሱ መሀከል ምልክትን እንደያዘ ተናግሯል፡ ይህ ለኛም ይሰራል። ከቀን ስራዎቻችን ከማረፍ በላይ የሱን ቅዱስ ቀን እየጠበቅን መሆኑን ለሰማይ አባታችን ምን ምልክት እንሰጣለን? ይህ ቤተክርስቲያን ሄዶ ቅዱስ ቁርባን መካፈልን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳናችንን ማደስን፣ የእግዚአብሔር ቃልን ለመመገብ የ ኑ፣ ተከተሉኝ ስብሰባን በቤታችን ማድረግን፣ የመለኮታዊው እውነት እውቀታችንን ማሳደግን፣ እና ኢየሱስ በሰንበት እንዳረገው3 መልካም ማድረግን4 ያጠቃልላል። ይህን በማድረግ የመንፈስ ቅዱስ አብሮነትን እንቀበላለን፣ ሰላም ይሰማናል፣ በዚህ ቋሚ ቃልኪዳን ወደ ጌታ እንቀርባለን5

ማስታወሻዎች

  1. ኦሪት ዘፍጥረት 2፥2–3 ይመልከቱ።

  2. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ሰንበት ደስታ ናት”፣ ሚያዚያ 2015(እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ይመልከቱ።

  3. የሉቃስ ወንጌል 13፥11–17፣ የዮሐንስ ወንጌል 5፥1–18 ይመልከቱ። የሉቃስ ወንጌል 6፥1–11 ይመልከቱ።

  4. የሉቃስ ወንጌል 6፥1–11 ይመልከቱ።

  5. ኦሪት ዘጸአት 31፥16–17 ይመልከቱ።

አትም