2022 (እ.አ.አ)
አዲስ የአካባቢ አመራሮች እንኳን ደህና መጣችሁ
ነሐሴ 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ ዜናዎች

አዲስ የአካባቢ አመራሮች እንኳን ደህና መጣችሁ

በነሃሴ ወር የአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ ለአዳዲስ አመራሮች አቀባበል አድርጓል። እነዚህ የክህነት መሪዎች በማዕከላዊ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገራትን በበላይነት ይመራሉ። ለሰባዎቹ አመራር ሪፖርት ያደርጋሉ።

ማቲው ኤል. ካርፔንተር የአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ ፕሬዚዳንት ናቸው። የተወለዱት ጥቅምት 21 ቀን 1959 ዓ.ም(እ.አ.አ) በሶልት ሌክ ሲቲ ዩታ ነው። ከሚሼሌ(ሼሊ) ኬይ ብራውን ጋር በ1982(እ.አ.አ) ትዳር መስርተዋል። የአምስት ልጆች ወላጆችም ናቸው።

በቢዝነስ ማናጅመንት የሳይንስ ባችለር ዲግሪ ከብሪገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ በ1983 (እ.አ.አ) ተቀብለዋል።በ1987 (እ.አ.አ) የቢዝነስ አስተዳደር የማስተርስ ዲግሪያቸውን ከሃርቫርድ የቢዝነስ ትምህርት ቤት ተቀብለዋል።

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ሚስዮን የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ፣ የአጥቢያ ሚስዮናዊ፣ ስካውት ማስተር፣ የካስማ የወጣት ወንዶች ፕሬዚዳንት፣ በኤጲስ ቆጶስ አመራር ውስጥ አማካሪ፣ በካስማ የሚስዮን አመራር አማካሪ፣ የአጥቢያ የሚስዮን መሪ፣ ከፍተኛ አማካሪ፣ ኤጲስ ቆጶስ እና የካስማ ፕሬዚዳንት በመሆን ጨምሮ በብዙ የቤተክርስቲያን ጥሪዎች አገልግለዋል።

ከዚህ ጥሪ በፊት ሽማግሌ ካርፔንተር በአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ አመራር ውስጥ የመጀመሪያ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል።በሰሜን አሜሪካ ማዕከላዊ አካባቢ ውስጥ የአካባቢ ሰባ፣ የዩታ አካባቢ አመራር ረዳት፣ በሰሜን አሜሪካ ማዕከላዊ አካባቢ አመራር አማካሪ እንዲሁም በቤተክርስቲያኗ ዋና መስሪያ ቤት በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ አገልግለዋል።

በሙያ ዘመናቸው በተለያዩ የንግድ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ በዋና የፋይናንስ መኮንን ፣ በፕሬዚዳንትነት እና በዋና የስራ አስፈፃሚነት ሰርተዋል።

ቲየሪ ኬ. ሙቶምቦ በአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ የመጀመሪያ አማካሪ ናቸው። የተወለዱት በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኪንቻሳ በጥር 31 ቀን 1976(እ.አ.አ) ነው። በ2002 (እ.አ.አ) ከሻዪ ናታሊ ሲንዳ ጋር ጋብቻን መስርተዋል። ስድስት ልጆችንም አፍርተዋል።

በ2010 (እ.አ.አ) ከሴፕሮማድ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ማናጅመንትተመርቀዋል እንዲሁም በ2012 (እ.አ.አ) ከዚሁ ዩኒቨርሲቴ በሰው ሃብት አስተዳደር የባቺለር ዲግሪ ተቀብለዋል።

በኮትዲቯር አቢጃን ሚስዮን የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ፣ የአጥቢያ የሚስዮን መሪ፣ የአጥቢያ የሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪ፣ የካስማ ዋና ጸሃፊ፣ በካስማ አመራር ውስጥ አማካሪ፣ የካስማ ፕሬዚዳንት እንዲሁም የሜሪላንድ ባልቲሞር ሚስዮን ፕሬዚዳንት በመሆን ጨምሮ በተለያዩ የቤተክርስቲያን ጥሪዎች ላይ አገልግለዋል።

ጥሪው በተሰጣቸው ጊዜ በአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ አመራር ውስጥ ሁለተኛ አማካሪ በመሆን እያገለገሉ ነበር።

እ.አ.አ ከ2000 እስከ 2005 የጉዞ ድርጅት ባለቤት ነበሩ። የንብረት አስተዳደር ክፍል ሱፐርቫይዘር እና የሰው ሃብት ክፍል ማናጀር በመሆን በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውስጥ ለቤተክርስቲያኗ ሰርተዋል። እጅግ በቅርቡ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቤተሰብ ታሪክ ክፍል ማናጀር በመሆን አገልግለዋል።

ኢያን ኤስ. አርደርን በአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ አመራር ሁለተኛ አማካሪ ናቸው። የተወለዱት በቴ አሮሃ ኒው ዚላንድ በየካቲት 28 1954 (እ.አ.አ) ነው።በጥር 1976 (እ.አ.አ) ከፓውላ አን ጁድ ጋር ጋብቻ መስርተዋል።አራት ልጆችንም አፍርተዋል።

በ1982 (እ.አ.አ) በትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም እ.አ.አ በ1994 በትምህርት የማስትሬት ዲግሪያቸውን ኒው ዚላንድ ከሚገኘው የዌካቶ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።

በፈረንሳይ እና በቤልጂየም የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ፣ የካስማ የወጣት ወንዶች አማካሪ፣ ከፍተኛ አማካሪ፣ በኤጲስ ቆጶስ አመራር አማካሪ፣ ኤጲስ ቆጶስ፣ በካስማ አመራር ውሰጥ አማካሪ፣ የፊጂ ሱቫ ሚስዮን ፕሬዚዳንት፣ የአካባቢ ሰባ እና የፓሲፊክ አካባቢ ፕሬዚዳንት በመሆን ጨምሮ በተለያዩ የቤተክርስቲያን ጥሪዎች ላይ አገልግለዋል።።

በ1981 (እ.አ.አ) የቤተክርስቲያኗን የትምህርት ስርዓት በመምህርነት ተቀላቀሉ። ከዚያም ኒውዚላንድ የሚገኘው የቤተክርስቲያኗ ኮሌጅ ፕሪንሲፓል ሆኑ። በ2004 (እ.አ.አ) ለፓሲፊክ አካባቢ የቤተክርስቲያኗ የትምህርት ስርዓት ዳይሬክተር ሆኑ። ከዚያም ኒው ዚላንድ በሚገኘው የቤተክርስቲያኗ የኢንስቲቱት ዳይሬክተር እና የሴሚናሪ አስተባባሪ በመሆን ሰርተዋል።

አትም