2023 (እ.አ.አ)
መንፈስ ቅዱስ ሊረዳን ይችላል።
ሰኔ 2023 (እ.አ.አ)


“መንፈስ ቅዱስ ሊረዳን ይችላል፣ ”ሊያሆና፣ ሰኔ 2023 (እ.አ.አ) ።

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ሰኔ 2023 (እ.አ.አ)

መንፈስ ቅዱስ ሊረዳን ይችላል

ምስል
አንድ ሰው ቁጭ ብሎ ጸሃይ ስትወጣ እያየ

መንፈስ ቅዱስ የአምላክ ሶስተኛው አባል ነው። ቅዱስ መፃሕፍትም መንፈስ፣ የተቀደሰው መንፈስ ወይም አጽናኙ በማለት ይገልጹታል። የእርሱን ድምጽ ማዳመጥን እስከተማርን ድረስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክርልናል እንዲሁም የወንጌልን እውነታ እንድንማር ይረዳናል።

የአምላክ አባል

የሰማይ አባት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና መንፈስ ቅዱስ የአምላክ አባል ናቸው። ይወዱናል እንዲሁም የደህንነት ዕቅድእንዲከናወን በአንድነት ይሰራሉ። የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ የስጋ እና የአጥንት አካል ቢኖራቸውም መንፈስ ቅዱስ የለውም። እርሱ መንፈስ ነው።

ምስል
የምስል መስታወት የአብ እና የወልድ ምስል

የአብ እና የወልድ ምስክር

“መንፈስ ቅዱስ ስለ አብ እና ወልድ ይመሰክራል” (2 ኔፊ 31:18)። ይህ ማለት በመንፈስ ቅዱስ በኩል ስለ ሰማይ አባት እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነትን ልንቀበል እንችላለን ማለት ነው።

ስለ እውነት ይመሰክራል

መንፈስ ቅዱስ ስለ ሁሉም እውነቶች ይመሰክራል። እርሱ— የደህንነትን እቅድ፣ የአምላክን ትእዛዛት፣ ዳግም መመለስን እና የኢየሱስ ክርስቶስን የሃጢያት ክፍያን ጨምሮ— ወንጌል እውነት እንደሆኑ እንድናውቅ ይረዳናል። መጸለይ፣ ትእዛዛትን ማክበር እና ወንጌሉን ማጥናት ስንቀጥል ምስክርነታችንን ያጠነክራል።

ምስል
ኮምፓስ የያዘ እጅ

ይመራናል እንዲሁም ይጠብቀናል

መንፈስ ቅዱስ በምርጫዎቻችን ሊመራን ይችላል እንዲሁም ከስጋዊ እና ከመንፈስዊ አደጋ ይጠብቀናል። የምንጸልይና ትክክል የሆነውን ለማድረግ የምንጥር ከሆነ ለጥያቄዎቻችን መልስ እንድናገኝ ይረዳናል። ሁሌም “መልካምን [ወደ መሥራት]” ይመራናል (ትምህርት እና ቃል ኪዳን 11:12)።

እኛን ያጽናናል

መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ጊዜ እንደ “አጽናኝ “በመባል ይታወቃል (ዮሃንስ 14:26)። ስንጨነቅ፣ ስናዝን ወይም ስንፈራ (ሞሮኒ 8:26) “በተስፋና በፍጹም ፍቅር ሊሞላን ይችላል”። እርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማን ሲረዳን፣ ተስፋ መቁረጥን እናሸንፋለን እና በፈተናዎቻችን ውስጥ እንበረታለን።

የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ

ከተጠመቅን በኋላ፣ የአባልነት ማረጋገጫ በሚባል ሥርዓት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እንቀበላለን። ይህን ስጦታ ከተቀበልን በኋላ፣ በጽድቅ እስከኖርን ድረስ የመንፈስ ቅዱስ ዘላቂ አጋርነት ሊኖረን ይችላል።

ምስል
ሴት ቅዱሳት መጻሕፍትን እያነበበች

ስዕል በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

መንፈስ ቅዱስን የምንሰማበት መንገድ

መንፈስ ቅዱስ በተለያየ መንገድ ከሰዎች ጋር ይነጋገራል። እነዚህ ምን መናገር ወይም ማድረግ እንዳለብን የሚጠቁሙ ሰላማዊ፣ አጽናኝ ስሜቶችን ወይም ግንዛቤዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ። ለምሪት ስንጸልይ እና ከእርሱ የሚመጣውን ተነሳሽነት ስናዳምጥ እንዴት እንደሚናገረን መማር እንችላለን።

አትም