“ጌተሰማኔ” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሚያዚያ፣ 2023 (እ.አ.አ)
ቦታዎች ከቅዱሳት መጻሕፍት
ጌተሰማኔ
በእኛ ፋንታ የአዳኙ ስቃይ ስለጀመረበት ቦታ ይበልጥ ተማሩ።
የት ነው ያለው?
ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ባለው የደብረ ዘይት ቁልቁለት (በሥዕሉ ላይ በስተቀኝ፣ ትልቅ ዛፍ ካለበት)።
የኢየሩሳሌም ካርታ ምሳሌ በጂም ማድሰን
እዚያ ምን ነበር?
የወይራ ዛፎች ቁጥቋጦ እና ምናልባትም ከወይራዎቹ ዘይት ለማውጣት የሚጠቅም መጭመቂያ።
እዚህ ምን ተፈጠረ?
ከመጨረሻው እራት በኋላ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአስራ አንዱ ሃዋሪያቶች ጋር ወደ ጌቴሰማኔ ሄደ። ከዚያም ጴጥሮስንና ያቆብን ዩሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰዶ ሊጸልይ ወጣ።
“ሊደነግጥም ሊተክዝም ጀመረና” እንዲህ ሲል ተናገረ ፦ ”ነፍሴ እስከሞት ድረስ እጅግ አዘነች” (ማርቆስ 14: 33-34)።
እንዲህ ሲል ጸለየ “አባ አባት ሆይ ሁሉ ይቻልሃል ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው ግን እኔ የምወደው አይሁን።
“ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው።
“በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር፣ ወዙም በምድር ለይ እንደሚወርድ የደም ነጠብጣብ ነበር” (ሉቃስ 22:42-44)።
ከዚህ ከአዳኙ ከባድ ስቃይ በኋላ፣ በይሁዳ አሳልፎ ተሰጠ እና በአይሁድ መኮንኖች እና በሮማውያን ወታደሮች ታሰረ።
ጌተሰማኔ፣ በማይክል. ማልም
© 2023 Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የ ለወጣቶች ጥንካሬ ወርሃዊ መልዕክት፣ ሰኔ 2023 (እ.አ.አ) ትርጉም። Language. 19026 506