2023 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማካፈል
ሐምሌ 2023 (እ.አ.አ)


የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማካፈል’’ ሊያሆና፣ ሐምሌ 2023 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ሐምሌ 2023 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማካፈል

ምስል
ወጣት ሴት ጭኖቿ ላይ ቅዱሳት መጽሃፍትን ከፍታ

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን አባል በመሆናችን ስለምንቀበለው በረከት ስናስብ ወንጌልን ለምንወዳቸው ለማካፈል እንፈልጋለን። ስለ እውነታው ያለንን ምስክርነት በቃላችን እና ምሳሌ በመሆን ልናካፍል እንችላለን። ለማን እንደምናካፍል እና ምን እንደምንል ለማወቅ ተነሳሽነት ለማግኘት መጸለይ እንችላለን።

ምስል
ኢየሱስ ለበሽተኛው ሰው ሲደርስለት

ሌሎችን ውደዱ

ወንጌልን የማካፈል ወሳኙ ክፍል ሌሎችን መውደድ ነው። ክርስቶስን በሚመስል ተግባር ለሌሎች ፍቅራችንን ስናሳይ፣ አንዳንድ ጊዜ ምንም ቃል ሳንናገር-የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለሊሎች እያካፈልን ነው። ሌሎች ደግሞ ስለ እነሱ እንደምናስብ ሲያውቁ ስለወንጌሉ ያለንን ሃሳብ ለማዳመጥ ይበልጥ ዝግጁ ሊሆኑ ይችላሉ። (ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን፣ “መውደደ፣ ማካፈል፣ መጋበዝ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 84-87።)

በተለመደው እና ተቀባይነት ባለው መንገድ አካፍሉ

ስለ ወንጌሉ የምንወደውን ማካፈል እንችላለን። ይህንን የእለት ተእለት የህይወታችን ክፍል ስናደርግ፣ ከባድ ወይም ምቾት የሚነሳ አይሆንም። ለምሳሌ፣ እሁድ ስለምናደርገው ነገር ከቤተሰባችን እና ከጓደኞቻችን ጋር መነጋገር እንችላለን። ወይም ሊሎችን ስናገለግል ስለሚሰማን ደስታ ልንነግራቸው እንችላለን። ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “የሚስዮናዊነት ሥራ፤ በልባችሁ ውስጥ ያለውን ማካፈል፣” ሊያሆና፣፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 15–18።)

ሌሎች እንዲቀላቀሉን ጋብዙ።

ስለወንጌሉ ይበልጥ እንዲማሩ ሌሎችን መጋበዝ እንችላለን። ለምሳሌ፣ ወደ ቤተ-ክርስቲያን ስብሰባ ወይም አክቲቪቲ እንዲመጡ፣ መጽሃፈ ሞርሞንን እንዲያነቡ፣ የቤተ-ክርስቲያን ቪዲዮን እንዲመለከቱ ወይም ሚሲዮናዊያንን እንዲጎበኙ ልንጋብዛቸው እንችላለን። እነዚህ ተሞክሮዎች መንፈስ ቅዱስ እንዲሰማቸው እና ይበልጥ የማወቅ ፍላጎት እንዲኖራቸው ሊረዳ ይችላል።

ምስል
ሁለት በእድሜ ተለቅ ያሉ ሴቶች ቁጭ ብለው ሲነጋገሩ።

ስለ ተሞክሮዎቻቸው ጠይቁ

ጓደኞች እና የቤተሰብ አባላት ወደ ቤተ-ክርስቲያን ከመጡ በኋላ ወይም በሚሲዮናዊያን ትምህርት ከተሠጣቸው በኋላ፣ ስለነበራቸው ተሞክሮ ልንጠይቃቸው እንችላለን። አንዳንድ የወንጌል አስተምህሮቶች አዲስ ሊሆኑባቸው ይችላሉ፣ ስለዚህ የሚኖራቸውን ጥያቄዎች ልንመልስ እንችላለን። ወደ ክርስቶስ ለመምጣት ስለሚያደርጉት ጥረት ፍቅራችንን እና ድጋፋችንን ልናሳያቸው እንችላለን።

እምነታቸው ላይ ጨምሩ

የሌሎችን እምነት ከፍ አድርገን እንመለከታለን እንዲሁም እናከብራለን፣ እናም እነሱ አስቀድሞ ባላቸው እምነት ላይ ለመጨመር እንሞክራለን። ለምሳሌ፣ ከመጽሃፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ መጽናናትን ያገኘ ጓደኛ ከመጽሃፈ ሞርሞን በምናካፍለው አስተምሮት መጽናናትን ሊያገኝ ይችል ይሆናል።

ምስል
ወጣት ሴት በእድሜ የገፋችን ሴት መንገድ በማሻገር ስትረዳት።

የቤተ-ክርስቲያን አባላትን እርዱ

ሰዎች ቤተ-ክርስቲያንን ሲቀላቀሉ፣ እምነታቸውን ማጠንከር እንችላለን። ጓደኛቸው መሆን፣ ጥያቄዎቻቸውን መመለስ እና ጥሪዎችን ሲቀበሉ ልንደግፋቸው እንችላለን። ኢየሱስ ክርስቶስን መከተላቸውን እና ስለ ወንጌሉ መማራቸውን እንዲቀጥሉ መደገፍ እንችላለን።

ምስል
ሁለት ሚሲዮናዊያን እና አንድ ሰው አብረው ስልክ እየተመለከቱ

የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ በመሆን አገልግሉ

ወንጌልን በእለት ተእለት ህይወታችን ውስጥ ከማካፈል በተጨማሪ፣ የቤተ-ክርስቲያን አባላት እንደ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሆነው ለማገልገል ሊጠሩ ይችላሉ። የተዘጋጁ ከሆነ፣ ወጣት ወንዶች ከ18 አመት ጀምሮ ማገልገል ይችላሉ። ወጣት ሴቶች እና እድሜያቸው ከፍ ያሉ ሴቶችም ሊያገለግሉ ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ በ ChurchofJesusChrist.org/callings/missionary ልታገኙ ትችላላችሁ።

አትም