መውደድ፣ ማካፈል፣ መጋበዝ
ስንወድ፣ ስናካፍል እና ስንጋብዝ፣ ምድርን ለመሲህ መመለስ በሚያዘጋጀው ታላቅ እና ክቡር ስራ እንሳተፋለን።
ለአፍታ ከኔ ጋር ሆናቹ፣ ከገሊላ ተራራ ላይ ቆማቹ ከሞት የተነሳው አዳኝ፣ ደቀ መዛሙርቱን ሲጎበኝ ተአምሩን እና ክብሩን እያያቹ አስቡ። እርሱ ከእነርሱ ጋር የተካፈለውን እነዚህን ቃላቶች “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወ ልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ የሚለው የክብር ትእዛዙ በግል መስማትን ማሰብ እንዴት የሚያበረታታ ነው።”1 በእርግጥ፣ እነዚህ ቃላቶች ልክ እንደ ሐዋርያቶቹ፣ እያንዳንዳችንን ያበረታናል፣ ያነሳሳናል እና ያንቀሳቅሰናል። በእርግጥም፣ የቀረውን ሕይወታቸውን ይህንኑ ለማድረግ በመሰጠት አሳልፈዋል።
የሚገርመው፣ የኢየሱስን ቃላት በልባቸው የያዙት ሐዋርያት ብቻ አልነበሩም። የጥንቷ ቤተ-ክርስቲያን አባላት፣ ከአዲሱ እስከ ብዙ ልምድ ያካበቱት፣ በአዳኙ ታላቅ ጥሪ ውስጥ ለሚያገኙት እና ለሚያውቋቸው የወንጌልን መልካም ዜና በማካፈል ተሳትፈዋል። የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት ለማካፈል ያላቸው ቁርጠኝነት፣ አዲስ ለተቋቋመችው ቤተ-ክርስቲያኑ ሰፊ እድገትን ፈጠረ። 2
እኛም፣ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን፣ እርሱ መጀመሪያ በዚያ በገሊላ ተራራ ላይ በተናገረበት ጊዜ እንደነበርን ያህል፣ የሰጠውን ተልእኮ ዛሬ እንድንከተል ተጋብዘናል። ይህ ስራ እንደገና የጀመረው በ1830 (እ.አ.አ) ጆሴፍ ስሚዝ ወንድሙን ሳሙኤልን የመጀመሪያ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን ሚስዮናዊ አድርጎ ሲለየው ነው።3 ከዛ ጊሄ ጀምሮ፣ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚያክሉ ሚሲዮናዊዮች ሁሉንም አህዛብ እያስተማሩ እና የተመለሰውን ወንጌል መልካም ዜና የሚያደንቁትን ሁሉ እያጠመቁ፣ በአለም ዙሪያ ተጉዘዋል።
ይህ የኛ አስተምህሮት ነው። ያገኘነው ፍላጎት።
ከትንሽ ልጆቻችን ጀምሮ በመካከላችን እስካሉት ታላላቆች፣ የአዳኙን ጥሪ ተፈፃሚ የምናደግበትን እና ወንጌልን ለአለም የምናካፍልበትን ጊዜ እንናፍቃለን። እናንተ ወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች፣ አዳኝ ከሐዋርያቱ ጋር እንዳደረገው የሙሉ ጊዜ የሚስዮናዊነት አገልግሎት እንድትዘጋጁ ነብያችን ትላንትና ሲጋብዛችሁ ተመሳሳይ የሚያበረታታ ፈተና ተሰምቷችሁ እንደነበር እርግጠኛ ነኝ።
ልክ እንደ መጀመሪያው ቦታ ላይ እንደ ስፕሪንተርስ፣ የውድድሩን መጀመር የነቢዩን ምልክት በማሳየት ዋናውን ግብዣ በጉጉት እንጠብቃለን። ይህ ፍላጎት ክቡር እና አነሳሽ ነው፣ ቢሆንም፣ ይህን ጥያቄ ታሳቢ እናድርግ፦ እኛ ሁላችንምለምን አሁን አንጀምርም።
“የስም ባጅ ከሌለኝ እንዴት ሚስዮናዊ መሆን እችላለሁ?” ብላቹ ልትጠይቁ ትችላላቹ። ወይም ለራሳችን እንዲህ እንላለን፦ “የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን ይህን ሥራ ለመሥራት ተዘጋጅተዋል። መርዳት እፈልጋለሁ፣ ግን ምናልባት በኋላ ህይወት ትንሽ ሲረጋጋ።”
ወንድሞች እና እህቶች፣ ከዛ በላይ በጣም ቀላል ነው! በአመስጋኝነት፣ የአዳኙ ታላቅ ተልእኮ ከልጅነት ጀምሮ እያንዳንዳችን በተማርነው ቀላል በሆኑ እና በቀላሉ ለመረዳት በሚያስችሉ መርሆች፣ ፍቅር፣ ማካፈል እና መጋበዝ በኩል ሊሳካ ይችላል።
ፍቅር
ማድረግ የምንችለው የመጀመሪያው ነገር ክርስቶስ እንደወደደው መውደድ ነው።
በዚህ ውዥንብር ጊዜ ውስጥ በአለም ላይ በምናየው የሰው ልጅ ስቃይ እና ውጥረት ልባችን ከብዷል። ሆኖም፣ የተገለሉትን ማለትም ከቤታቸው የተፈናቀሉ፣ ከቤተሰባቸው የተነጠሉ፣ ወይም ሌላ ዓይነት ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ላሉት፣ ሰዎች በየቦታው ባሳዩት ርህራሄ እና ሰብአዊነት ለተጎዱት ለመድረስ ባላቸው ጥረት፣ መነሳሳት እንችላለን።
በፖላንድ የሚገኝ የእናቶች ቡድን፣ ተስፋ ለቆረጡ ቤተሰቦች በማሰብ በባቡር ጣቢያ መድረክ ላይ በእቃ የተሞሉ ጋሪዎችን በጠራ መስመር ላይ አስቀምጠው ከባቡር ሲወርዱ በድንበር መሻገሪያው ላይ የነሱ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ስደተኛ እናቶች እና ህጻናትን እየጠበቁ እንደሆነ በቅርቡ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። በእርግጥ፣ የሰማይ አባታችን እንደዚህ ባሉ ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ የልግስና ተግባራት፣ ፈገግ ይላል፣ ምክንያቱም አንዳችን የሌላውን ሸክም በምንሸከምበት ጊዜ፣ “የክርስቶስን ህግ እናሟላለን።4
ማንም እንኳን አንድ ቃል ባንናገርም፣---ለባልንጀራችን የክርስቶስ ዓይነት ፍቅር ስናሳይ ወንጌልን እንሰብካለን።
ለሌሎች ፍቅር ማለት፣ ባልንጀራችንን እንድንወድ የሁለተኛው ታላቅ ትእዛዝ አነጋጋሪ መግለጫ ነው፤ ይህም መንፈስ ቅዱስ ራሳችን ነፍስ ውስጥ የሚሰራውን የማጥራት ሂደት ያሳያል።5 ክርስቶስ ለሌሎች ያለውን ፍቅር በማሳየት መልካም ሥራችንን የሚመለከቱ ሰዎች “በሰማያት ያለውን አባታችንን እንዲያከብሩ ልናደርጋቸው እንችላለን።6
ይህን የምናደርገው በምላሹ ምንም ሳንጠብቅ ነው።
ምን ዓይነት ምላሽ እንደሚሰጡ በእኛ ቁጥጥር ስር ባይሆንም በርግጥ ተስፋችን ፍቅራችንን እና መልዕክታችን ይቀበላሉ የሚል ነው።
እኛ የምናደርገው እናእኛ ማን እንደሆንን እርግጠኛ ነው።
የክርስቶስን መሰል ፍቅር ለሌሎች በመስጠት፣ የክርስቶስን የወንጌል ክብር፣ ህይወትን የሚቀይር ባህሪያትን እንሰብካለን፣ እንዲሁም ታላቁን ተልእኮውን በመፈጸም ረገድ ጉልህ ተሳትፎ እናደርጋለን።
አካፍሉ
እኛ ማድረግ የምንችለው ሁለተኛው ነገር ማካፈል ነው።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመጀመሪያዎቹ ወራት አካቢ፣ ከታይላንድ የመጣው ወንድም ዊሳን በማህበራዊ ሚዲያ መለያው ላይ በመጽሐፈ ሞርሞን በጥናቱ ላይ የተማረውን ስሜት እና የተሰማውን ለማካፈል ተገፋፍቶ ነበር። በአንደኛው የግል ልጥፎቹ ውስጥ፣ የሁለት መጽሃፈ ሞርሞን ሚስዮናውያንን፣ አልማን እና አሙሌክን ታሪክ አጋርቷል።
ወንድሙ ዊናይ፣ ምንም እንኳን በሃይማኖታዊ እምነቱ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም በፖስቱ ጽሁፍ ተነካ እና ሳይታሰብ “ይህን መጽሐፍ በታይኛ ላገኘው እችላለሁ?” ሲል ጠየቀ።
ዊሳን የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂ በሁለት እህት ሚስዮናውያን እንዲደርስ በጥበብ አዘጋጀ፣ እነሱም ወንድሙን ማስተማር ጀመሩ።
ዊሳን በኮምፒተር በታገዘው የርቀት ትምህርት ተቀላቀለና ስለመጽሐፈ ሞርሞን ያለውን ስሜት አካፈለ። ዊናይ እውነትን በሚፈልግ መንፈስ መጸለይን እና ማጥናትን፣ እውነትን መቀበል እና መቀበልን ተማረ። በወራት ውስጥ ዊናይ ተጠመቀ!
ዊሳን በኋላ እንዲህ አለ፣ “በእግዚአብሔር እጅ ያለን መሳሪያ የመሆን ሃላፊነት አለብን፣ እና እሱ በእኛ በኩል ስራውን እንዲሰራ ሁል ጊዜ ዝግጁ መሆን አለብን። የቤተሰባቸው ተአምር የመጣው ዊሳን በተለመደው እና በተፈጥሮ መንገድ ወንጌልን ስላካፈለ ነው።
ሁላችንም ነገሮችን ለሌሎች እናካፍላለን። ብዙ ጊዜ እናደርጋለን። የምንወዳቸውን ፊልሞች እና ምግቦች፣ የምናያቸው አስቂኝ ነገሮች፣ የምንጎበኛቸው ቦታዎች፣ የምናደንቃቸው ስነ ጥበቦች፣ የተነሳሳንባቸውን ጥቅሶች እናካፍላለን።
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የምንወደውን የምናካፍላቸው ነገሮች ዝርዝር ውስጥ እንዴት በቀላሉ መጨመር እንችላለን?
ሽማግሌ ዲዬተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዲህ በማለት ገልፀዋል፡ “አንድ ሰው ስለ ቅዳሜና እሁድዎ ከጠየቀ፣ በቤተክርስቲያን ስላጋጠመዎት ነገር ከመናገር ወደኋላ አይበሉ። በጉባኤ ፊት ለፊት ቆመው ኢየሱስን ለመምሰል እየሞከርኩኝ ነው የሚለውን መዝሙር በጉጉት ስለዘመሩት ትንንሽ ልጆች ንገሯቸው። በእረፍት ቤቶች ውስጥ ያሉ አረጋውያንን በመርዳት የግል ታሪኮችን ለማዘጋጀት ጊዜ ስላሳለፉት የወጣት ቡድን ተናገሩ።7
ማካፈል ወንጌልን “መሸጥ” አይደለም። ስብከት መጻፍ ወይም የአንድን ሰው የተሳሳተ አመለካከት ማረም የለብዎትም።
ወደ ሚስዮናዊ ሥራ ስንመጣ እግዚአብሔር አንተን የእርሱ ስራ አስኪያጅ እንድትሆን አይፈልግም ነገር ግን እርሱ ተካፋይ እንድትሆን ይጠይቃል።
በወንጌል ውስጥ ያለንን አወንታዊ ልምዶቻችንን ለሌሎች በማካፈል፣ የአዳኙን ታላቅ ተልዕኮ በመፈጸም እንሳተፋለን።
ጋብዙ
ማድረግ የሚችሉት ሶስተኛው ነገር መጋበዝ ነው።
እህት ሜይራ ከኢኳዶር በቅርቡ ቤተክርስቲያንን የተቀላቀለች ናት። ከተጠመቀች በኋላ በዙሪያዋ ያሉትን ጓደኞቿን እና የምትወዳቸውን ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ስትጋብዝ የወንጌል ደስታዋ ጨምሯል። ልጥፎቿን ያዩ ብዙ የቤተሰብ አባላት እና ጓደኞች በጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ሜይራ ከእነሱ ጋር ትገናኝ ነበር፤ ብዙውን ጊዜ ሚስዮናውያንን ለማግኘት ወደ ቤቷ ትጋብዛቸው ነበር።
የሜይራ ወላጆች፣ ወንድሞቿ፣ እህቶቿ፣ አክስቷ፣ ሁለት የአክስቶቿ ልጆች እና በርካታ ጓደኞቿ ተጠመቁ፣ ምክንያቱም “ኑና እዩ፣” “ኑና አገልግሉ” እና “ኑና ኑሩ” በማለት በድፍረት ስለጋበዘቻቸው። በተለመደው እና በተፈጥሯዊ ግብዣዎቿ፣ ከ20 በላይ ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት እንዲሆኑ ጥሪዋን ተቀብለዋል። ይህ የሆነበት ምክንያት እህት ሜይራ እንደ ቤተክርስቲያኗ አባል ሆና የተሰማትን ደስታ እንዲካፈሉ በመጋበዟ ነው።
ለሌሎች ልናቀርብላቸው የምንችላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብዣዎች አሉ። የቅዱስ ቁርባን አገልግሎትን፣ የአውራጃ እንቅስቃሴን፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የሚያብራራ የኦንላይን ቪዲዮን “መጥተው እንዲያዩ” ሌሎችን መጋበዝ እንችላለን። “ኑና እዩ” ከመመረቁ በፊት መፅሐፈ ሞርሞንን ለማንበብ ወይም ለመጎብኘት ክፍት ሲሆን አዲስ የተመረቀን ቤተመቅደስን ለመጎብኘት ግብዣ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ፣ ግብዣው ለራሳችን የምናቀርበው ነው—እርምጃ ልንውስድባቸው ስለሚገቡን በዙሪያችን ስላሉ እድሎች ግንዛቤ እና ራዕይ የሚሰጠን ለራሳችን የሚቀርብ ግብዣ።
በእኛ የዲጂታል ዘመን፣ አባላት ብዙ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቶችን ይጋራሉ። ለመጋራት ብቁ ሆነው ሊያገኟቸው የሚችሏቸው በመቶዎች፣ ካልሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ የሚያንጹ ነገሮች አሉ። ይህ ይዘት “ኑና እዩ”፣ “ኑና አገልግሉ” እና “ኑና ኑሩ” ግብዣዎችን ያቀርባል።
ሌሎችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የበለጠ እንዲማሩ ስንጋብዝ፣ በአዳኝ በተሰጠዉ ተልእኮ ስራ ለመሳተፍ በሚያቀርበው ጥሪ ላይ እንሳተፋለን።
መደምደሚያ
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ማንም ሰው ሊያደርጋቸው ስለሚችላቸው ሶስት ቀላል ነገሮች ዛሬ ተናግረናል። እናንተማድረግ የምትችሏቸው ነገሮች! ምናልባት እርስዎ ሙሉ በሙሉ እያደረጋችሁት መሆኑን ሳትገነዘቡ—እያደረጋችሁት ሊሆን ይችላል!
መውደድ፣ ማካፈል እና መጋበዝ የምትችልባቸውን መንገዶች እንድታስቡ እጋብዛችኋለሁ። ይህንን ስታደርጉ፣ የተወደደውን አዳኛችን ቃል እየሰማህ እንደሆነ በማወቅ የተወሰነ ደስታ ይሰማችኋል።
እኔ እየተማጸንኩ ያለሁት አዲስ ፕሮግራም እንድታደርጉ አይደለም። ይህንን መርህ ከዚ በፊት ሰምታችኋል። ይህ ቤተክርስቲያንና እንድታያደርጉ የምትጠይቅ “ቀጣዩ ትልቅ ነገር” አይደለም። እኚህ ሦስቱ ነገሮች የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆናችንን ለማሳያ ብቻ ናቸው።
ምንም ስም ባጅ ወይም ፊደል አያስፈልግም።
መደበኛ ጥሪ አያስፈልግም።
እነዚህ ሦስቱ ነገሮች የማንነታችን እና የአኗኗራችን ተፈጥሯዊ አካል ሲሆኑ፣ አውቶማቲክ፣ የማይገደድ የእውነተኛ ፍቅር መግለጫ ይሆናሉ።
ከ2,000 ዓመታት በፊት በገሊላ ከእርሱ ለመማር የተሰበሰቡ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን፣ እኛም የአዳኙን ትእዛዝ ተቀብለን ወንጌልን በመስበክ ወደ ዓለም ሁሉ መሄድ እንችላለን።
ስንወድ፣ ስንካፈል እና ስንጋብዝ፣ ምድርን ለመሲህ መመለስ በሚያዘጋጀው ታላቅ እና ክቡር ስራ እንሳተፋለን።
የአዳኙን ጥሪ እንድንሰማ እና በታላቅ ተልእኮው ለመሳተፍ እንድንጥር ጸሎቴ በኢየሱስ ነው፣ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።