አጠቃላይ ጉባኤ
በአባታችን እቅድ ውስጥ ያለው መለኮታዊ ፍቅር
የሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


በአባታችን እቅድ ውስጥ ያለው መለኮታዊ ፍቅር

የዚህች በዳግም የተመለሰች ቤተክርስቲያን የትምህርት እና የፖሊሲዎች አላማ የእግዚአብሔርን ልጆች ለደህንነት እና ለከፍታ ማዘጋጀት ነው።

የወንጌሉ እቅድ የሰማይ አባታችን ለሁሉም ልጆቹ ያለው ፍቅር ያሳያል። ይህን ለመረዳት የእርሱን እቅድ እና የእርሱን ትእዛዛት ለመረዳት መሻት አለብን። ልጆቹን በጣም ከመውደዱ የተነሳ አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛችን እና ቤዛችን እንዲሆን፣ እንዲሰቃይ ና እንዲሞትልን ሰጠን። ዳግም በተመለሰችው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ የሰማይ አባታችን እቅድ ልዩ የሆነ አረዳድ አለን። ይህ የሟችነት ህይወት አላማን፣ ከእርሱ የሚከተለውን መለኮታዊ ፍርድ፣ እናም የሁሉም የእግዚአብሄር ልጆች የመጨረሻውን የክብር እጣ ፈንታ የምንመለከትበትን ለየት ያለ እይታ ይሰጠናል።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ እወዳችኋለው። ሁሉንም የእግዚአብሄር ልጆች እወዳለው። ኢየሱስ “ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት?” ተብሎ ሲጠየቅ እግዚአብሄርን መውደድ እና ባልንጀሮቻችንን መውደድ የመጀመሪያዎቹ ታላቅ ትእዛዛት እንደሆኑ አስተምሮአል።1 እነዛ ትእዛዛት የመጀመሪያዎቹ የሆኑበት ምክንያት እግዚአብሄር ለኛ ያለውን ፍቅር ለማስመሰል በመሻት በመንፈሳዊ መልኩ እንድናድግ ስለሚረዱን ነው። ሁላችንም የሰማይ አባታችን እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ላስቀመጡት የፍቅር አስተምሮቶች እና መመሪያዎች የተሻለ አረዳድ ቢኖረን ኖሮ ብየ እመኛለው። እዚህ የምናገረው የእግዚአብሄር ፍቅር ያንን አስተምሮት እና በቤተክርስቲያን የተነሳሱ መመሪያዎችን እንዴት እንደሚያብራራ ለመግለጽ ይሻል።

1.

ከሟችነት ህይወት በኋላ ስለሚከተለው ፍርድ ያለው የተለመደ የተሳሳተ አረዳድ፣ መልካም ሰዎች ገነት ወደሚባል ቦታ እና መጥፎ ሰዎች ማለቂያ ወደሌለው ሲኦል ወደሚባል ቦታ እንደሚሄዱ ያለው አረዳድ ነው። ይህ የመጨረሻ ሁለት መዳረሻዎች ብቻ እንዳሉ ያለው የተሳሳተ ግምት ለገነት የሚጠበቁትን ሁሉንም ትእዛዛት መጠበቅ ያልቻሉ የዘለአለም እጣፈንታቸው ሲኦል እንደሆነ ያመለክታል።

አፍቃሪ የሰማይ አባት ለልጆቹ የተሻለ እቅድ አለው። ዳግም የተመለሰችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በኩል በተገለጠው አስተምሮት ሁሉም የእግዚአብሄር ልጆች—እዚህ ጋር ከጥቂት ከግምት ውስጥ ከማንከታቸው በስተቀር—በስተመጨረሻ በክብር ደረጃ ውስጥ ይገባሉ።2 “በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ”3 ብሎ ክርስቶስ አስተምሯል። ከዘመናዊ ራእዩ እነዚህ ቤቶች በሶስት የተለያዩ የክብር ደረጃዎች ውስጥ እንደሆኑ እናውቃለን። በመጨረሻው ፍርድ ላይ እያንዳንዳችን እንደስራችን እና የልባችን መሻት ይፈረድብናል።4 ከዛ በፊት ንስሃ ላልገባንባቸው ሀጢያቶች መሰቃየት ይኖርብናል። ቅዱሳት መጻህፍቶች በዛ ላይ ግልጽ ናቸው።5 ከዛም ጻድቁ ዳኛችን ከክብር ደረጃዎቹ አንዱ ውስጥ መኖሪያን ይቸረናል። ስለዚህ ከዘመናዊ ራእይ እንደምናውቀው ሁሉም “እንደ ስራቸውም መጠን ይፈረድባቸዋል፣ እናም ለእያንዳንዱ ሰውም እንደስራው በተዘጋጀለት መኖሪያ ግዛቱን ይቀበላል።”6

ጌታ በንጽጽሩ ስለሁለቱ የክብር ደረጃዎች ትንሽ ብቻ ለመግለጥ መርጧል። በንጽጽሩ ስለከፍተኛው የክብር ደረጃ መጽሀፍ ቅዱስ “የጸሀይ ክብር” ብሎ ስለሚገልጸው ጌታ ብዙ ነገሮችን ገልጧል።7

በሰለስቲያል ክብር ውስጥ8 ሶስት ደረጃዎች ወይም መጥኖች አሉ።9 ከእነዚህ ትልቁ እንደአባታችን እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ የምንሆንበት በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ከፍ መደረግ ነው። መለኮታዊ አቅማችንን ለማሳካት የሚያስፈልጉንን መለኮታዊ ባህሪያቶች እና ተፈጥሮአዊ ለውጦች እንድናዳብር ለመርዳት ጌታ በዘለአለማዊ ህግ ላይ አሰተምሮቶችን ገልጧል እና ትእዛዛቶችን መስርቷል። በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ውስጥ ይህን ነው ምናስተምረው ምክንያቱም የዚህች ዳግም የተመለሰች ቤተክርስትያን አስተምሮ እና መመሪያዎች አላማ የእግዚአብሄር ልጆችን በሰለስቲያል ክብር ውስጥ ለመዳን በተለይ ደግሞ በከፍተኛው ደረጃ ውስጥ ከፍ ከፍ ለመደረግ ለማዘጋጀት ነው።

በእግዚአብሄር ቤተመቅደሶች ውስጥ ለታማኞች የተገቡት ቃል ኪዳኖች እና ቃል የተገቡት በረከቶች ቁልፍ ናቸው። ይህም ዘማሪዎች በውብታዊ መንገድ የዘመሩበት የአለም አቀፍ የቤተመቅደሶች ግንባታችንን ያስረዳል። አንዳንዶች የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖች እና ስርአቶች ከፍተኝነትን ወደማግኘት እንደሚመሩን ባለመረዳት በዚህ አጽንኦት ግራ ይጋባሉ። ይህን መረዳት የሚቻለው ስለሶስቱ የክብር ደረጃዎች በተገለጠው እውነታ ብቻ ነው። የሰማይ አባታችን ለሁሉም ልጆቹ ባለው ታላቅ ፍቅር ምክንያት—ትላንትና ሽማግሌ ክዉንተን ኤል. ኩክ እንደገለጹት—እኛ ከምናስባቸው በላይ አሰደናቂ የሆኑ ሌሎች የክብር ደረጃዎችን አቅርቦልናል።10

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት እነዚህ ሁሉ ነገሮች እንዲቻል ያደርጋል። እርሱም አብን “እንደሚያከብር እናም … የእጆቹን ስራዎች ሁሉ እንደሚያድን11 ገለጸ። ያም ደህንነት በተለያዩ የክብር ደረጃዎች ውስጥ ይሰጣሉ። ከዘመናዊ ራእይ “ሁሉም መንግስታት የተሰጣቸው ህግ እንዳላቸው” አውቀናል።12 በጉልነት፦

“በሰለስቲያል መንግስት ህግ መፅናት የማይችለው በሰለስቲያል ክብር መፅናት አይችልምና።

እና በተረስትሪያል መንግስት ህግ መፅናት የማይችለውም በተረስትሪያል ክብር መፅናት አይችልም።

እና በቲለስቲያል መንግስት ህግ መፅናት የማይችለውም በቲለስቲያል ክብር መፅናት አይችልም።”13

በሌላ አነጋገር በመጨረሻው ፍርድ የምንቀበለው የክብር ደረጃ የሚወሰነው በሰማይ አባታችን የፍቅር እቅድ ውስጥ ለመጠበቅ በምንመርጠው ህጎች ነው። በበዚያ እቅድ ስር ሁሉም ልጆቹ “መቆየት” ወደሚችሉበት መንግስት እንዲመደቡ ብዙ መንግስታት አሉ።

2.

የጌታ ዳግም የተመለሰችው ቤተክርስትያን ትምህርቶች እና ፖሊሲዎች የሰማይ አባታችን ለሁሉም ልጆቹ ባለው እቅድ ንድፍ ውስጥ ብቻ ልንረዳቸው በምንችልበት መንገድ እነዚህን ዘላለማዊ እውነታዎች ይተገብራል።

ስለዚህም የግል ምርጫን እናከብራለን። ብዙዎች የሀይማኖትን ነጻነት ለማበረታታት ይህቺ ቤተክርስቲያን የምታረገውን ታላቅ ጥረት ታውቃላችሁ። እነዚህ ጥረቶች የሰማይ አባታችንን እቅድ አበረታቶ ለማሰቀጠል ነው። የእኛን አባላቶች ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ልጆቹን ውዱን የመምረጥ ነጻነትን እንዲደሰቱበት ለመርዳት እንሻለን።

በተመሳሳይ ለምን ሚሲዮናዊያንን ወደ ብዙ ሀገራት፣ እንዲሁም በክርስቲያን በሆኑ ህዝቦች መሀከልም እንኳን እንደምንልክ አንዳንዴ እንጠየቃለን። ከሚሲዮናዊ ስራ ጥረቶቻችን ጋር ሳናያይዝ ለምን ከፍተኛ የበጎ አድራጎት አርዳታዎችን አባል ላልሆኑ ሰዎች እንደምንሰጥም እንጠየቃለን። ይህን የምናደርገው ጌታ ሁሉንም ልጆቹን እንደ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንድናከብር ስላስተማረንና መንፈሳዊና አካላዊ መትረፍረፋችንን ለሁሉም ማካፈል ስለምንፈልግ ነው።

ዘለአለማዊ አሰተምሮም ደግሞ በልጆች ላይ ግልጽ የሆነን እይታ ይሰጠናል። በዚህ እይታ ልጆችን መውለድ እና መንከባከብን እንደመለኮታዊው እቅድ አካል እናየዋለን። በዚህ ውስጥ ለመሳተፍ ሀይል ለተሰጣቸው አስደሳች እና የተቀደሰ ግዴታ ነው። ስለዚህ፣ በእግዚአብሔር እቅድ ስር ለህፃናት እድገት እና ደስታ ምቹ ሁኔታዎችን የሚያቀርቡ መርሆዎችን እና ልምዶችን እንድናስተምር እና እንድንታገል ታዝዘናል።

3.

በስተመጨረሻ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአግባቡ ቤተሰብ ላይ እንደተመሰረተች ቤተክርስቲያን ትታወቃለች። ነገር ግን በደንብ ያልተረዱት ነገር ቢኖር በቤተሰብ ላይ መመስረታችን በሟችነት ጊዜ ባሉን ግንኙነቶቻችን የተወሰነ አለመሆኑን ነው። ዘለአለማዊ ግንኙነቶችም ለመንፈሳዊ ትምህርታችን መሰረታዊ ናቸው። ዳግም የተመለሰው ቤተክርስቲያን አላማ ሁሉንም የእግዚአብሄር ልጆች እግዚአብሔር ለሚፈልገው የመጨረሻ እጣፈንታቸውን ብቁ እንዲሆኑ መርዳት ነው። በክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት በተሰጠው ቤዛነት፣ ሁሉም የዘላለም ሕይወት (ከፍታን በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ) ያገኛሉ፣ እናት ሔዋን እንዲህ አወጀች “እግዚአብሔር ለታዛዦች ሁሉ ይሰጣል።”14 ይህ ከመዳን በላይ ነው። ፕሬዘደንት ረስል ኤም. ኔልሰን “በእግዚአብሄር ዘላለማዊ እቅድ ውስጥ መዳን የግል ጉዳይ ነው፤ ነገር ግን ከፍ መደረግ የቤተሰብ ጉዳይ ነው” በማለት አሰታውሰውናል።15

ለእኛ መሰረታዊ የሆነው ከፍ መደረግ ሊገኝ የሚችለው በወንድ እና በሴት መሀል ባለው ለዘለአለማዊ ጋብቻ ቃል ኪዳኖች ታማኝ በመሆን ብቻ እንደሆነ የሚገልጸው የእግዚአብሄር ራእይ ነው።16 ይህ መለኮታዊ አስተምሮ “ጾታ አስፈላጊ የሆነ የግለሰብ ቅድመ ህይወት፣ ሟች እና ዘላለማዊ መለያ እና አላማ እና ባህሪ ነው” ብለን የምናሰተምርበት ምክንያት ነው ።17

ለዚህም ነው ጌታ ዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያኑን ከእርሱ በወንድ እና በሴት መሀል ጋብቻ አስተምሮ እንዲያፈገፍጉ የሚጫኑ ማህበራዊ እና ህጋዊ ጫናዎችን እንዲቋወሙ፣ እና ጾታን የሚያወዛግቡ ወይም የሚቀይሩ ወይም በወንዶችና በሴቶች መሀል ያለውን ልዩነት የሚያመሳስሉ ለውጦችን ወይም ጾታን የሚቀይሩትን እንዲቃወሙ የሚፈልገው።

በዚህ መሰረታዊ ነገሮች ላይ ዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያን ያላት አቋም ብዙ ጊዜ ተቋውሞ ያስነሳል። እሱ ይገባናል። የሰማይ አባታችን ዕቅድ “በሁሉም ነገር ተቃርኖ” 18 እንዲኖር ይፈቅዳል እና የሰይጣን ብዙ ከባድ ተቋውሞ የሚሰነዘረው ለዚ እቅድ ማንኛውም በጣም አስፈላጊ በሆነ ነገር ላይ ነው። በዚህም ምክንያት ጋብቻን በማዛባት፣ ልጅ መውለድን ባለማበረታታት ወይም ጾታን በማደናገር ወደ ክብር የሚመጣን እድገት ለመቃወም ይፈልጋል። ይሁንና በስተመጨረሻ የሰማይ አባታችን አላማ እና እቅድ በብዙሀኑ ለማቻቻል ሲባል አይቀየርም። ግላዊ ሁኔታዎች ሊቀየሩ ይችላሉ እናም የእግዚአብሔር ዕቅድ ቃልኪዳናቸውን ለሚጠብቁ አማኞች ቃል ለተገባላቸው በረከቶች ብቁ ለመሆን እድል እንደሚኖራቸው ያረጋግጣል።19

“ከእግዚአብሄር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ”20 ለሆነው ለዘላለማዊ ህይወት እንድንዘጋጅ ልዩ ጠቃሚ የሆነው ትምህርት የ1995 (እ.አ.አ) የቤተሰብ አዋጅ ነው።21 አዋጆቹ በእርግጥ አሁን ካሉት አንዳንድ ህጎች፣ ክንውኖች፣ እና ሙግቶች የተለዩ ናቸው፣ ለምሳሌ እንደ አብሮ እንደመኖር እና ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ። የአባታችንን ለልጆቹ ያለውን የፍቅር እቅድ ሙሉ በሙሉ የማይረዱ ይህን የቤተሰብ አዋጅ ከፖሊሲ መቀየር መግለጫ በላይ አድርገው አያዩትም። በተቃራኒው እኛ በማይሻር አስተምሮ ላይ የተመሰረተው የቤተሰብ አዋጅ የዘላለማዊ እድገታችን ዋናው አስፈላጊ ክፍል የሚካሄድበትን የቤተሰብ ግንኙነቶችን አይነት ይገልጻል።

ይህ ዳግም ለተመለሰው ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ልዩ አስተምሮ እና ፖሊሲዎች አውድ ነው።

4.

በሟች ህይወት ውስጥ ባሉ በብዙ ግንኙነቶች እና ሁኔታዎች ውስጥ እያንዳንዳችን ከልዩነቶች ጋር መኖር አለብን። ባልንጀሮቻችንን መውደድ ያለብን የክርስቶስ ተከታዮች እንደመሆናችን እኛ እንደምናምነው ከማያምኑት ጋር በሰላም መኖር አለብን። ሁላችንም የአፍቃሪ የሰማይ አባት ልጆች ነን። ለሁላችንም ከሞት በኋላ ህይወት እና በስተመጨረሻም የክብር መንግስት አዘጋጅቷል። እግዚአብሄር ሁላችንም በአለም ዙሪያ እየተገነቡ ባሉት ቅዱስ ቤተመቅደሶች ውስጥ የሚደመደሙትን የእርሱን ታላቅ ትእዛዛት፣ ቃል ኪዳኖች፣ እና ስነስርአቶች በመጠበቅ ለእርሱ ከፍተኛ በረከቶች እንድንጥር ይሻል። እነዚህን ዘላለማዊ በረከቶች ለሌሎች ለማካፈል መሻት አለብን። ነገር ግን ከሁሉም ባልንጀሮቻችን ባለን የፍቅር እዳ ሁሌም ውሳኔዎቻቸውን እንቀበላለን። የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ እንዳስተማረው “የእግዚአብሄርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር” እየኖረን ወደፊት መቀጠል አለብን።22

ፕሬዘደንት ረስል ኤም ኔልሰን በባለፈው ጉባኤ ላይ እንዳወጁት፣ “አዳኛችንን ማወቅ በግል ይበልጥ አስፈላጊ እና ለሁሉም የሰው ነፍስ አግባብ የሆነበት ጊዜ በምድር ታሪክ ውስጥ ኖሮ አይታወቅም። … የክርስቶስ ንጹህ አስተምሮ ሀይለኛ ነው። የሚረዳውን እና በእርሱ ወይም በእርሷ ህይወት ላይ ለመተግበር የሚሻን ሰው ሁሉ ህይወት ይቀይራል።”23

ሁላችንም የተቀደሰ ትምህርት በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ እንድናደርግ የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

አትም