አጠቃላይ ጉባኤ
ቪዲዮ፦ “እናንተ እሱ አስቀድሞ የተመለከታቸው ሴቶች ናችሁ”
የሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ቪዲዮ፦ “እናንተ እሱ አስቀድሞ የተመለከታቸው ሴቶች ናችሁ”

እ.ኤ.አ. በ1979 ፕሬዘዳንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምቦል ሆስፒታል ውስጥ ነበሩ፤ እናም ባለቤታቸው ካሚላ ንግግራቸውን ለአጠቃላይ የሴቶች ስብሰባ እንድታነብላቸው ጠየቋት።

እህት ካሚላ ኪምቦል፦ “በዚህ የመጨረሻ ጊዜያት በቤተክርስቲያኗ እየመጡ ያሉት አብዛኞቹ ወሳኝ እድገቶች የሚመጡበት ምክንያት በአለም ውስጥ ያሉ (አብዛኛውን ጊዜ ውስጣዊ የመንፈሳዊነት ስሜት ያላቸው) መልካም ሴቶች በብዙ ቁጥር ወደ ቤተክርስቲያኗ ስለሚሳቡ ነው። ይህም የሚሆነው የቤተክርስቲያኗ ሴቶች በህይወታቸው በሚያንፀባርቁት የቅድስና እና የግልፅነት መጠን እንዲሁም የቤተክርስቲያኗ ሴቶች፣ በደስታ መንገዶች፣ ከአለም ሴቶች ተለይተው በሚታዩበት መጠን ልክ ነው።”1

ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን፦ “በዚህ የመቋጫ ወቅት የእኛ ወሳኝ አጋሮች የሆናችሁ ውድ እህቶቼ፣ ፕሬዘዳንት ኪምቦል አስቀድመው የተመለከቱት ቀን ዛሬ ነው። እናንተ እሱ አስቀድሞ የተመለከታቸው ሴቶች ናችሁ! የእናንተ መልካምነት፣ ብርሀን፣ ፍቅር፣ እውቀት፣ ድፍረት፣ ባህርይ፣ እምነት እና የፅድቅ ህይወት የአለምን መልካም ሴቶች ከነቤተሰቦቻቸው በማይገለፅ ቁጥር ወደ ቤተክርስቲያን ይስባል።

“ጥንካሬያችሁ፣ መለወጣችሁ፣ ጽኑ አቋማችሁ፣ የመምራት አቅማችሁ፣ ጥበባችሁና ድምፃችሁ ያስፈልገናል። ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን የሚገቡ እና ከዚያም የሚጠብቁ በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን መናገር የሚችሉ ሴቶች በሌሉበት የእግዚአብሔር መንግስት ሙሉ አይደለም ሊሆንም አይችልም …

“… ጥሪያችሁ ምንም ይሁን፣ ሁኔታዎቻችሁ ምንም ይሁኑ፣ የእናንተን ስሜት፣ የእናንተን መረዳት እና የእናንተን መነሳሳት እንፈልጋለን። በአጥቢያ እና በካስማ ምክር ቤቶች ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ሃሳባችሁን እንድትገልጹ እንፈልጋለን። ያገባችሁ እህቶች ሁሉ ቤተሰባችሁን በመምራት ረገድ ከባላችሁ ጋር አንድ ስትሆኑ ‘አስተዋፅኦ እንዳላችሁ እና እንደ ሙሉ አጋር’ እንድትናገሩ እንፈልጋለን። ያገባችሁም ሆነ ያላገባችሁ ብትሆኑ፣ እናንተ እህቶች እንደ ስጦታ ከእግዚአብሔር የተቀበላችኋቸው የተለዩ ችሎታዎች እና ልዩ የማስተዋል ብቃት አላችሁ። እኛ ወንድሞች የእናንተን አይነት ልዩ አስተዋፅኦ ልናፈራ አንችልም።

“የፍጥረት ሁሉ መቋጫ የሴት መፈጠር እንደሆነ እናውቃለን! ጥንካሬያችሁን እንፈልጋለን!…

“…ውድ እህቶች አመሰግናችኋለሁ፣ እንዲሁም በዚህ ቅዱስ ስራ ውስጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንጓዝ ወደ ሙሉ ማዕረጋችሁ ከፍ እንድትሉ፣ የፍጥረታችሁን ሚዛን እንድታሟሉ እባርካችኋለሁ። አንድ ላይ በመሆን አለምን ለጌታ ዳግም ምጽዓት በማዘጋጀት እንረዳለን።”2

ማስታወሻዎች

  1. የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ስፔንሰር ደብልዩ.ኪምቦል (2006), 222–23.

  2. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለእህቶቼ ልመና፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 96 97።

አትም