አጠቃላይ ጉባኤ
አለምን ለመፈወስ
የሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


አለምን ለመፈወስ

የሁላችንም አባት የሆነውን እግዚአብሔርን እና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ስናከብር ቁስሎች እና ልዩነቶች ሊፈቱና አልፎ ተርፎም ሊፈወሱ ይችላሉ።

ወንድሞች እና እህቶች በዚህ የከበረ ወቅት የእግዚአብሄር አገልጋዮችን ስላገኘን እንዲሁም ከእነርሱ ምክር እና አቅጣጫ ስለተቀበልን ተባርከናል

ከሰማይ አባታችን የሚመጡ ቅዱስ ምሪቶች እና ትምህርቶች በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት ህይወታችንን ለመምራት ይረዱናል። እንደተተነበየው “እሳት እና ሃይለኛ ነፋስ፣” “ጦር የጦር ወሬ” እንዲሁም በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ፣” በሁሉም ዓይነት ርኩሰቶች [መሞላት]፣“ ”1 “ወረርሽኝ፣”2 “ራብና ቸነፈር፣”3 ቤተሰቦችን ፣ማህበረሰቦችን ብሎም ሃገራትን እየጎዱ ይገኛሉ።

አለምን እየጠራረገ ያለ ሌላ መቅሰፍትም አለ እርሱም በእኔ እና በእናንተ የሃይማኖት ነጻነት ላይ የሚደረግ ጥቃት ነው። ይህ እያደገ የመጣ ስሜት ሃይማኖትን እና በእግዚአብሄር ላይ ያለ እምነትን ከህዝብ አደባባይ፣ ከትምህርት ቤቶች፣ ከማህበረሰብ ደረጃዎች እና ከሲቪክ ንግግሮች ለማስወገድ ይፈልጋል። የሃይማኖት ነጻነት ተቀናቃኞች ልባዊ በሆኑ እምነቶቸ ላይ ገደቦችን ለመጣል ይፈልጋሉ። በእምነት ልማዶች ላይ ሳይቀር ትችት እና ፌዝ ያደርሳሉ።

እንዲህ አይነት ዝንባሌ የግል መርሆችን፣ ፍትሃዊነትን፣ ክብርን፣ መንፈሳዊነትን እና የህሊና ሰላምን ዝቅ በማድረግ ሰዎችን ያገልላል።

የሃይማኖት ነጻነት ምንድን ነው?

የመሰብሰብ ነፃነትን፣ የመናገር ነፃነትን፣ በግል እምነት ላይ ተመርኩዞ የመንቀሳቀስ ነፃነትን እንዲሁም ሌሎችም ያንን ተመሳሳይ ነገሮች እንዲያደርጉ ነፃነት በመስጠት አምልኮን ሙሉ በሙሉ በነፃነት ማከናወን ማለት ነው። የሃይማት ነጻነት እያንዳንዳችን ምን እንደምናምን፣ እንዴት እንደምናምን እና በእምነታችን ላይ ተመስርተን እና እግዚአብሄር እንደሚጠብቅብን እንድናደርግ ይፈቅድልናል።

እንዲህ አይነቱን የሃይማኖት ነፃነት ለመሸራረፍ የሚደረጉ ጥረቶች አዲስ አይደሉም። በመላው ታሪክ ውስጥ የእምነት ሰዎች በከፋ ሁኔታ ተሰቃይተዋል። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላትም ከዚህ አላመለጡም።

ከጅማሪያችን አንስቶ በኢየሱስ ክርስቶስና በኃጢያት ክፍያው ላይ ማመንን፣ ንስሃ መግባትን፣ የደስታ እቅድን እና የጌታችንን ዳግም ምጽአት ጨምሮ ባሏት መለኮታዊ ትምህርቶች ምክንያት እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ብዙዎች ወደዚህች ቤተክርስቲያን ተስበዋል።

ተቃውሞ፣ ስደት እና ብጥብጥ የመጀመሪያውን የኋለኛው ቀን ነቢያችንን ጆሴፍ ስሚዝን እና ተከታዮቹን አስቸግሯቸው ነበር።

በ1842 (እ.አ.አ) ጆሴፍ “ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሄርን ኅሊናችን እንደሚመራን የማምለክ መብት እንዳለን እናረጋግጣለን፣ እናም ሁሉም ሰዎች እንዴትም፣ የትም፣ ወይም ምንም የፈለጉትን እንዲያመልኩ እንደዚህ አይነት መብት እንዳላቸው እንቀበላለን”4የሚለውን ጨምሮ እያደገች የመጣችውን ቤተክርስቲያን 13 መሰረታዊ እምነቶች አሳተመ።

ቃላቶቹ ሁሉን አቀፍ የሆኑ፣ ነጻ የሚያወጡ እና አክባሪ ናቸው። ያ ነው የሃይማኖት ነጻነት ዋና ነገር።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የሚከተለውንም ተናግሯል።

“ለፕሬስቢቴሪያን፣ ለባፕቲስት ወይም በየትኛውም የሀይማኖት ወገን ላለ መልካም ሰው ለመሞት ዝግጁ መሆኔን በሰማይ ፊት በድፍረት እናገራለሁ፤ …የቅዱሳንን መብት የሚጨቁን በተመሳሳይ መርህ እንዲሁ በሮማ ካቶሊኮች ላይ ወይም በትኛውም ያልታወቀ የሌላ የሀይማኖት ወገን እና እራሳቸውን ለመከላከል በጣም ደካማ በሆኑትም ላይ የመብት ጭቆና ያደርሳል።

“የሲቪል እና የሃይማኖት ነጻነት ለመላው የሰው ዘር የሚለው [ያ] የነጻነት ፍቅር ነው ነፍሴን የሚያነሳሳት”5

አሁንም የቀድሞ ቤተክርስቲያን አባላት ተጠቅተውና በሺዎች ማይሎች ከኒው ዮርክ ወደ ኦሃዮ ከዚያም አስተዳዳሪው የቤተክርስቲያኗ አባላት “እንደጠላት መታየት እንዳለባቸው አንዲሁም መወገድ እና ከሃገሩ መባረር እንዳለባቸው ወዳዘዘባት ወደሚዙሪ ተሳደው ነበር።.”6 ወደኢሊኖይ ሸሹ ሆኖም ስቃዩ ቀጥሎ ነበር። እርሱን መግደል ቤተክርስቲያኗን እንደሚያፈርስ እና አማኞችን እንደሚበተን በማሰብ ነቢዩ ጆሴፍን በመንጋ ገደሉት። ነገር ግን ታማኞቹ ጸኑ። የጆሴፍ ተከታይ የነበረው ብሪገም ያንግ በሺዎች የሚቆጠሩትን የ2,100 ኪሜ በሚፈጅ የግዳጅ ስደት ዛሬ ዩታ ከምትባለው ስቴት በስምዕራብ መራቸው።7 ቅድመ አያቶቼ ከእነዚያ የጥንት አቅኚ ሰፋሪዎች መካከል ነበሩ።

ከእነዚያ ከፍተኛ የስደት ጊዜያት ጀምሮ የጌታ ቤተክርስቲያን 17 ሚሊዮን ወደሚጠጉ አባላት8ያለማቋረጥ ያደገች ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑትም ከዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ይኖራሉ።

በሚያዝያ 2020(እ.አ.አ) የወንጌልን ዳግም መመለስ 200ኛ አመት በቀዳሚ አመራር እና በአስራሁለቱ ሃዋርያት በተዘጋጀ ለዓለም የተላለፈ ዓዋጅ አክብራለች። እንዲህ በማለት ይጀምራል “እግዚአብሔር በሁሉም የአለም ሃገራት ያሉትን ልጆቹን እንደሚወድ በጥብቅ እናውጃለን።”9

ውድ ነብያችን ፕሬዚዳንት ረስል ኤም.ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፦

“በነፃነት፣ በደግነት እና ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ፍታዊ በመሆን እናምናለን።

“ሁላችንም ወንድም እና እህቶች ስንሆን እያንዳንዳችን የአፍቃሪ ሰማያዊ አባት ልጅ ነን። ልጁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ‘ጥቁርም ነጭም፣ ባሪያውንና ነፃውን፤ ወንድን እና ሴትን” ሁሉም ወደእርሱ እንዲመጡ ይጋብዛል’ (2 ኔፊ 26፥33)።”10

ህብረተሰቡ እና ግለሰቦች ከሃይማኖት ነፃነት ጥቅም የሚያገኙባቸውን አራት መንገዶች ከእኔ ጋር አስቡ።

አንደኛ የሃይማኖት ነፃነት እግዚአብሄርን የህይወታችን ማዕከል በማድረግ የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን ታላላቅ ትዕዛዛት ያከበራል። ማቴዎስ ላይ እንዲህ የሚል እናነባለን፦

“ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፣”11

“ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም። ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ ።”12

በጸሎት ቤት ይሁኑ በምኩራብ፣ በመስጊድ ይሁኑ ወይም ከቆርቆሮ በተሠራች ጎጆ ውስጥ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እና ሁሉም ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸው አማኞች እርሱን በማምለክ እና ልጆቹን ለማገልገል ፈቃደኛ በመሆን ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት መግለጽ ይችላሉ።

ኢየሱስ ክርስቶስ የዚህ ዓይነቱ ፍቅር እና አገልግሎት ፍጹም ምሳሌ ነው። በአገልግሎቱ ወቅት ድሆችን ተንከባክቧል፣13 የታመሙትን14 እና የታወሩትን ፈውሷል።15 የተራቡትን አብልቷል፣16 ለህጻናት እጆቹን ዘርግቷል17 እንዲሁም የሰቀሉትን ሳይቀር የበደሉትን ይቅር ብሏል።

ቅዱሳን ጽሁፎች ኢየሱስ “መልካም በማድረግ ሄደ” ሲሉ ይገልጻሉ።19 እኛም እንዲሁ ማድረግ ይኖርብናል።

ሁለተኛ የሃይማኖት ነፃነት እምነትን፣ ተስፋን እና ሰላምን መግለጽን ያበረታታል።

እንደቤተክርስቲያን የሁሉንም እምነቶች እንደሁም የሚያሳምኑ ሰዎች እና እምነታቸውን የመናገር መብታቸውን በመከላከል ረገድ ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር እንተባበራለን ። ይህ ማለት እምነታቸውን እንቀበላለን ወይም የእኛን ይቀበላሉ ማለት አይደለም ይልቁንም ዝም ሊያሰኙን ከሚፈልጉት ጋር ካለን የበለጠ የጋራ ነገር አለን።

በቅርቡ በጣልያን በተደረገው የጂ20 የእምነት ተቋማት ህብረት ፎረም ላይ ቤተክርስቲያኗን ወክዬ ተገኝቼ ነበር። ከአለም ዙሪያ ከመጡ የሃገር እና የእምነት መሪዎች ጋር ስገናኝ ተበረታታሁ፤ ተነቃቃሁም። የሁላችንም አባት የሆነውን እግዚአብሔርን እና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ስናከብር ቁስሎች እና ልዩነቶች ሊፈቱና አልፎ ተርፎም ሊፈወሱ እንደሚችሉ ተገነዘብኩ። የሁሉም ታላቅ ፈዋሽ ጌታችን አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ንግግሬን ሳበቃ አሰደሳች ጊዜ አጋጠመኝ። ቀዳሚዎቹ ሰባት ተናጋሪዎች በማንኛውም አይነት የእምነት ልማድ ወይም በእግዚያብሄር ስም ንግግራቸውን አልዘጉም ነበር። እየተናገርኩኝ እያለሁ “እንዲያው አመሰግናለሁ ብዬ ነው የምቀመጠው ወይንስ ‘በኢየሱስ ክርስቶስ ስም’ ብዬ እዘጋለሁ” ስል አሰብኩኝ። ማን እንደሆንኩኝ አስታወስኩኝ እናም መልዕክቴን ስጨርስ ጌታ ስሙን እንድጠራ እንደሚፈልግ አወቅኩኝ። እንደዚያው አደረኩኝ። ወደ ኋላ መለስ ብዬ ሳስበው ለእኔ እምነቴን የመግለጫ አጋጣሚዬ ነበር፤ እንዲሁም ስለ ቅዱስ ስሙ ምስክርነቴን ለመስጠት የሃይማኖት ነፃነት ነበረኝ።

ሶስተኛ ሃይማኖት ሰዎች ሌሎችን እንዲረዱ ያነሳሳል።

ሃይማኖት እንዲስፋፋ ቦታ እና ጊዜ ሲሰጠው አማኞች ቀላል እና አንዳንዴም ጀግንነትን የሚጠይቁ ተግባራትን ይፈጽማሉ። “ዓለምን ማደስ ወይንም መፈወስ” የሚል ፍቺ ያለው “ቲኩን ኦላም” የሚለው ጥንታዊው የአይሁድ ሃረግ ዛሬ ብዙዎች በሚያደርጉት ጥረት እየተንጸባረቀ ነው። ካሪታስ ኢንተርናሽናሊስ ከተሰኘ የካቶሊክ በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ከኢስላሚክ ሪሊፍ፣ እና ብዙ ቁጥር ካላቸው የአይሁድ፣ የሂንዱ፣ የቡድሂስት፣ የሲክ እና እንደ ሳልቬሽን አርሚ እና ብሔራዊ የክርስቲያን ፋውንዴሽን ካሉ የክርስቲያን ድርጅቶች ጋር ህብረት ፈጥረናል። አንድ ላይ በመሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግረኞችን እንረዳለን፤ በጣም በቅርቡ በጦርነት ለተፈናቀሉ የድንኳን፣ የመኝታ ከረጢቶች እና ምግብ በማቅረብ፣20 የፖሊዮን እና21 የኮቪድን ጨምሮ22 ክትባቶችን በማቅረብ ሲሆን እየተሰሩ ያሉት ነገሮች ዝርዝር ረጅም ናቸው፤ ሆኖም ፍላጎቶቹ እነዚህ ናቸው።

የእምነት ሰዎች በአንድነት ሲሰሩ ትርጉም ያለው አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉ ምንም ጥያቄ የለውም። በተመሳሳይ ጊዜ የአንድ ለአንድ አገልግሎት ብዙ ጊዜ አይነገርለትም ሆኖም ግን ውስጥ ለውስጥ ህይወትን ይለውጣል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የናይን መበለትን እንደረዳት የሚገልጸውን በሉቃስ ወንጌል ውስጥ ያለውን ምሳሌ አስባለሁ። ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋር በመሆን ወደመበለቷ ብቸኛ ልጅ የቀብር ስርዓት መጣ። እሱ ከሌለ ስሜታዊ፣ መንፈሳዊ እንዲሁም የገንዘብ ችግር ይገጥማታል። ኢየሱስ በእምባ የራሰውን ፊቷን ተመልክቶ “አታልቅሺ”27አላት ከዚያም አስከሬኑን የያዘውን ቃሬዛ ነካው ስርዓቱም ቆመ።

“አንተ ጎበዝ፣” “እልሃሁ ተነሳ ሲል አዘዘ

“የሞተውም ቀና ብሎ ተቀመጠ ሊናገርም ጀመረ።” ከዚያም [ኢየሱስ] ለእናቱ ሰጣት።”24

ሙታንን ማስነሳት ተዓምር ነው፤ ነገር ግን በችግር ውስጥ ላለ ሰው የምናደርገው እያንዳንዱ የደግነትና የአሳቢነት ድርጊት “እግዚአብሔር [ከእኛ] ጋር [እንደሆነ]”29በማወቅ እያንዳንዳችን “መልካምን እያደረግን [ለመሄድ]” የምንችልበት የቃል ኪዳን መንገድ ነው።

እናም አራተኛ. የሃይማኖት ነጻነት እሴቶችን እና ሞራልን ለመቅረጽ አንድ የሚያደርግና የሚያበረታታ ኃይል በመሆን ይሰራል።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙዎች ከኢየሱስ ክርስቶስ ዞር እንዳሉ እናባለን፤ “ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፣ ማን ሊሰማው ይችላል?” በማለት እያጉረመረሙ።26

ያ ጩኸት ሃይማኖትን ከስብከትና ከሚያደርገው ተጽዕኖ ለማስወጣት ከሚሹ ወገኖች ዛሬም በመሰማት ላይ ይገኛል። ይሁንና ሃይማኖት ባህርይን ለማስተካከል እና አስቸጋሪ ጊዜያትን ለማስታረቅ ባይኖር ኖሮ ይህን የሚያደርግ ማን ሊኖር ይችላል? ታማኝነትን፣ አመስጋኝነትን፣ ይቅር ባይትነን፣ እና ትዕግስትን ማን ያስተምራል? ለተረሱ እና ለተጨቆኑት ልግስናን፣ ርህራሄን እና ደግነትን ማን ያሳያል? የተለዩ የሆኑትን ሆኖም ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች እንደሚገባቸው ማን ይቀበላቸዋል? ለተቸገሩ እጆቹን የሚዘረጋ እና ለዚያም ዋጋ የማይሻ ማን ነው? በዘመኑ ከሚታየው በበለጠ ሰላምን የሚያከብረውና ሕጎችን የሚታዘዘው ማን ነው? “ሂድ፤ አንተም እንዲሁ አድርግ“ ለሚለው የአዳኝ ልመና ማን ምላሽ ይሰጥ ነበር?27

እኛ እንሰጣለን! አዎ፣ ወንድሞች እና እህቶች እኛ እናደርገዋለን።

የሃይማኖት ነፃነትን አላማ እንድታራምዱ እጋብዛችኋለሁ። የእግዚያብሄር ስጦታ የሆነው የመምረጥ ነጻነት መርህ መገለጫ ነው።

የሃይማኖት ነፃነት በተወዳዳሪ ፍልስፍናዎች መካከል ፍትህን ያመጣል። የሀይማኖት መልካም ነገሩ፣ ተደራሽነቱ እና በሀይማኖት አነሳሽነት የሚደረጉ የእለት ተእለት የፍቅር ተግባራት የሚበዙት ዋና ዋና እምነቶችን የመግለጽን እና በተግባር ላይ የማዋልን ነፃነት ስንጠብቅ ብቻ ነው።

ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልስን በህይወት ያሉ የእግዚአብሄር ነቢይ እንደሆኑ እመሰክራለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ይህችን ቤተክርስቲያን እየመራ እንደሆነ እመሰክራለሁ። ኃጢአታችንን አስተሰረየልን፣ በመስቀል ላይ ተሰቀለ፤ በሦስተኛው ቀንም ከሞት ተነሳ።28 በእርሱ ምክንያት እንደገና ለዘላለም ለመኖር እንችላለን እናም የሚፈልጉም ከአባታችን ጋር በሰማይ ለመኖር ይችላሉ። ይህንን አእውነት ለአለም ሁሉ አውጃለሁ። ይህንን ለማድረግ ነጻነት ስላለኝ አመስጋኝ ነኝ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም