ጊዜው አሁን ነው
ለመማር የምንችለው አሁን ብቻ ነው። ንስሀ ለመግባት የምንችለው አሁን ብቻ ነው። ንስሀ ለመግባት የምንችለው አሁን ብቻ ነው።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ይህ ጉባኤ በብዙ መንገዶች ታሪካዊ ነበር። በጸሎቶች፣ መልእክቶች፣ እና መዝሙሮች ተባርከናል። በጌታ አገልጋዮች ተነሳስተናል።
ለወደፊትም አስፈላጊ መመሪያዎችን ተቀብለናል። ጸሎቴም ጌታ እናንተ ልታደርጉ ስለሚፈልጋችሁን ነገሮች መንፈስ በቀጥታ እንዲያነጋገራችሁ ነው።
የወደፊቱ ሁልጊዜም እርግጠኛ አይደለም። የአየር ሁኔታ ይቀየራል። የኢኮኖሚ ዑደቶች ያልተጠበቁ ናቸው። መዓቶች፣ አደጋዎች እና ህመም ሕይወትን በፍጥነት ሊለውጡ ይችላሉ። እነዚህ ድርጊቶች እኛ ከምንቆጣጠራቸው በላይ ታላቅ ናቸው። ነገር ግን ጊዜአችንን እንዴት እንደምናሳልፍ ጨምሮ፣ እኛ ለመቆጣጠር የምንችላቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ።
ገጣሚው ሔንሪ ቫን ዳይክ በኒውዮርክ ዌልስ ኮሌጅ ሰንዳይል ላይ የጻፈውን እወዳለሁ። እንዲህም ይነበባል፦
በጣቴ የተጣለበት ጥላ
የወደፊቱን ካለፈው ይከፋፍላል፦
ከእርሱ በፊት፣ ያልተወለደውን ሰዓት ይተኛል፣
በጨለማ ውስጥ፣ እና ከኃይልህ በላይም።
ከማይመለሰው መስመር በስተጀርባም፣
የጠፋው ሰዓት፣ የአንተ አይደለም፦
አንድ ሰዓት ብቻ በእጅህ ነው፣—
ጥላው በቆመበት አሁን።1
አዎን፣ ወደፊት ከነበረው መማር ይገባናልም፣ እንዲሁም፣ አዎን፣ ለወደፊት ለመዘጋጀት ይገባናል። ነገር ግን ለማድረግ የምንችለም አሁን ነው። ለመማር የምንችለው አሁን ብቻ ነው። ንስሀ ለመግባት የምንችለው አሁን ብቻ ነው። አሁንም ነው ሌሎችን ለመባረክ እና “የዛሉትን እጆች [ለማቅናት]”2 የምንችልበት ጊዜ ያለው። ሞርሞን ልጁን ሞሮኒ እንደመከረው፣ “ተግተን እንስራ፤ … የፅድቅ ጠላት የሆነውን ሁሉ እናሸንፍ ዘንድ፣ እናም ነፍሳችንን በእግዚአብሔር መንግስት እናሳርፍ ዘንድ፣ በዚህ በጭቃ ሰውነታችን የምናከናውነው ስራ አለንና።”3
ጠላት በምንም አያንቀላፋም። ለእውነት ሁልጊዜም ተቃራኒ ይኖራል። በማናቸውም ተግዳሮቶች እና እድሎች ወደፊት እንድትራመዱ፣ አወንታዊ መንፈሳዊ ግስጋሴን፣ እንዲሁም ሽማግሌ ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ ሲነጋገሩበት የነበረውን ያን ማንሳትን፣ የሚጨምሩትን ነገሮች እንድታደርጉ ዛሬ ጠዋት በትጋት ያበረታታችኋችሁን እደግመዋለሁ።
አወንታዊ መንፈሳዊ ግስጋሴ በቤተመቅደስ ውስጥ ስናመልክ ይጨምራል እንዲሁም በዚያም ለመቀበል የምንችለውን አስደናቂ በረከቶችን ስፋት እና ጥልቀት የምንረዳበትም ያድጋል። በቤተመቅደስ ዘለአለማዊ በረከቶች ላይ በማተኮር አለማዊ መንገዶችን እንድታስወግዱ እለምናችኋለሁ። በዚያ የምታሳልፉት ጊዜ ዘለአለማዊ በረከቶችን ያመጣሉ።
ቤተክርስቲያኗ ስታድግ፣ ተጨማሪ ቤተመቅደሶችን በመገንባት ለመከተል እንጥራለን። አርባ አራት አዲስ ቤተመቅደሶች አሁን እየተገነቡ ናቸው። ተጨማሪዎችም እየታደሱ ናቸው። በአለም አቀፍ ላሉ ለእነዚህ ስራዎች ለሚሳተፉት ለባለሙያ ሰዎች እጸልያለሁ።
በጸሎታዊ ምስጋና መንፈስም፣ በሚቀጥሉት ቦታዎች ላይ አዲስ ቤተመቅደሶችን ስለመገንባት ለማስተዋወቅ ደስተኛ ነኝ፡ ዌሊግተን፣ ኒው ዚላንድ፤ ብራዛቪ፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ፤ ባርሴሎና፣ ስፓኛ፤ በርሚንግሃም፣ እንግሊዝ፤ ኩስኮ፣ ፔሩ፤ ማሴዮ፣ ብራዚል፤ ሳንቶስ፣ ብራዚል፤ ሳን ሉዊዝ ፖቶሲ፣ ሜክሲኮ፤ ሜክሲኮ ስቲ ቤኔሚሪቶ፣ ሜክሲኮ፤ ታምፓ፣ ፍሎሪዳ፤ ኖክስቪል፣ ቴነሲ፤ ክሊቭላንድ፣ ኦሀዮ፤ ዊችታ፣ ካንሳስ፤ ኦስትን፣ ቴክሳስ፤ ምዙላ፣ ማንታና፤ ሞንትፔሊየር፣ አይደሆ፤ እና ሞዴስቶ፣ ካሊፎርኒያ።
እነዚህ 17 ቤተመቅደሶች ከቁጥር በላይ የሆኑ ህይወቶችን በመጋረጃው ሁለት በኩል ይባርካሉ። እወዳችኋለሁ፣ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ። ከሁሉም በላይ አስፈላጊነት፣ ጌታ ይወዳችኋል። አዳኛችሁ እና ቤዛችሁ ነው። እርሱ ቤተክርስቲያኑን ይመራል። እኛም “እናንት ህዝቤ እኔም አምላካችሁ እሆን ዘንድ”4 ለሚለው ጌታ ብቁ እንሁን።
ለዚህም የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።