አጠቃላይ ጉባኤ
ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት
የሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


13:17

ግንኙነታችን ከእግዚአብሔር ጋር

የሟችነት ልምዳችን ምንም ነገር ቢያመጣ በእግዚአብሔር ማመን እና በእርሱ ሀሴት ማግኘት እንችላለን።

ልክ በብሉይ ኪዳን ውስጥ እንዳለው ኢዮብ በስቃይ ጊዜ አንዳንዶች እግዚዘብሄር አንደተዋቸው ሊሰማቸው ይችላል። እግዚአብሄር ማንኛውም ስቃይን መከላከል ወይም ማስዋገድ እንደሚችል በማወቃችን እንደዛ ካላደረገ ለማጉረምረም ልንገፋፋ እንችላለን ምናልባት “ጸልዬ የምጠይቀውን እርዳታ እግዚአብሄር የማይሰጠኝ ከሆነ እንዴት በሱ ላይ እምነት ሊኖረኝ ይችላል?” ብለን እንጠይቃለን። ጻድቁ ኢዮብ በከባዱ ፈተናው ውስጥ ሳለ የሆነ ጊዜ ላይ እንዲህ አለ፤

“እንግዲህ እግዚአብሄር እንደገለበጠኝ፤ በመረቡም እንደ ከበበኝ እወቁ።

“እነሆ ‘ስለተደረገብኝ ግፍ’ ብጮህ! ማንም አይመልስልኝም፤ አሰምቼም ብጠራ ፍርድ የለኝም።”1

እግዚአብሄር ለኢዮብ በምላሹ “አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ትፈርዳለህን?” ብሎ ይጠይቋል።2 ወይም በሌላ አባባል ስህተት ላይ ታስቀምጠኛለህ?” አንተ ትክክል እንድትሆን እኔን ትወቅሰኛለህ?”3 ያህዌ ኢዮብን የሱን ሁሉን የማይሳን እና ሁሉ አዋቂነት በሀይል አስታወሰው እና ኢዮብ ከእግዚአብሄር እውቀት፣ ሀይል፣ እና ጽድቅ ጋር የሚቀርብ እንኳን ምንም ነገር እንደሌለው እና ከሀያሉ ፍርድ ውስጥ መቆም እንደማይችል በጥልቅ ትህትና አመነ።

“አንተ ሁሉን ማድረግ ትችላለህ፣” አለ “ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ።

“… ስለዚህ እኔ የማላስተውለውን፤ የማላቀውንም ድንቅ ነገር ተናግሬአለሁ።…

ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በትቢያና በዐመድ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”4

በስተመጨረሻ ኢዮብ ጌታን ለማየት ታድሎ ነበር እና “እግዚአብሄርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ።”5

በሟችነት የቅርብ እይታችን እግዚአብሄርን ለመፍረድ ማሰብ ለምሳሌ “ደስተኛ አይደለሁም ስለዚህ እግዚአብሄር የሆነ የተሳሳተ ነገር እየሰራ መሆን አለበት” ብሎ ማሰብ የእውነት ጅልነት ነው። ለእኛ በወደቀው አለም ውስጥ ላሉት ስለአለፈው፣ ስለአሁኑ፣ ስለሚመጣው በጣም ጥቂት ለሚያውቁት የሱ ሟች ልጆች እንዲህ ብሎ ያውጃል “ሁሉም ነገሮች እኔ ዘንድ አሉ፣ ሁሉንም ነገሮች አውቃቸዋለሁና።”6 ያቆብ በጥበብ ያስጠነቅቀናል “ከእጁ ምክርን ለመቀበል እንጂ ጌታን ለመምከር አትሞክሩ። እነሆም፣ እናንተም በጥበብና፣ በፍርድ፣ እናም በታላቅ ምህረት፣ በስራው ላይ ሁሉ እንደሚመክር ታውቃላችሁ።”7

አንዳንዶች የእግዚአብሄር ቃልኪዳኖች ማለት ለሱ መታዘዝ የሆነ አንድ ውጤትን በተወሰነ የሰአት ገደብ ውስጥ ያመጣል ማለት ነው ብለው በስህተት ይረዳሉ። “በትጋት የሙሉ ጊዜ ሚስዮን ካገለገልኩ፤ እግዚአብሄር በደሰተኛ ጋብቻና ልጆች ይባርከኛል ወይም በሰንበት የትምህርት ቤት ስራዎችን ከመስራት ከተቆጠብኩኝ እግዚአብሄር በጥሩ ውጤት ይባርከኛል ወይም አስራቴን ከከፈልኩኝ እግዚአበሄር በዛ በምፈልገው ስራ ይባርከኛል” ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ህይወት ልክ በዚህ መንገድ ካልሆነችላቸው ወይም በጠበቁት የሰአት ሰንጠረዥ ውስጥ ፤ በእግዚአብሄር እንደተከዱ ሊሰማቸው ይችላል። ነገር ግን በመለኮታዊ ኢኮኖሚ ውስጥ ነገሮች መካኒካል አይደሉም። የእግዚአብሄርን እቅድ (1) የምንፈልገውን በረከት መርጠን፣ (2) አስፈላጊውን የመልካም ስራዎች መርጠን አስገብተን እና፣ (3) ትእዛዛችን በቶሎ እንደሚላክበት የሰማይ የሽያጭ ማሽን ነው ብለን ማሰብ የለብንም።8

እግዚአብሄር በእርግጥ ለኛ የገባቸውን ቃል ኪዳናትና ቃሎችን ያከብራል። ስለሱ መጨነቅ የለብንም።9 የኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ሀይል—እርሱም…ወደላይ ያረገው፣ ደግሞም ከሁሉም ነገሮች በታች የወረደው ነው10 (እናም) ስልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር (የተሰጠው)11—እግዚአብሄር እንደሚችልና ቃሎቹን እንደሚፈጽም ያረጋግጣል። የእርሱን ህግጋት ማክበራችን እና መታዘዛችን አስፈላጊ ነው፣ ግን ለህግ ታዛዥ በመሆን ላይ የሚመረኮዘው እያንዳንዱ በረከት12 እኛ በምንጠብቀው መልክ አይሰራም፣ አይቀረጽም፣ ሰአቱ አይወሰንም። የተቻለንን እናደርጋለን ግን የሁለቱንም የአካላዊና የመንፈሳዊ በረከቶችን አስተዳደር ለሱ መተው አለብን።

ፕሬዝደንት ብሪገም ያንግ እምነታቸው በተወሰኑ ውጤቶች ወይም በረከቶች ላይ እንዳልተገነቡ፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላቸው ምስክርነት እና ግንኙነት እንደሆነ ገለጹ። እሱ እንዲህ አለ፦ “እምነቴ በውቅያኖስ ደሴት ላይ ባለው በጌታ ስራ ላይ፣ ህዝቦችን እዚህ ስላመጣቸው … ወይም በዚህ ህዝቦች ወይም በእነዛ ህዝቦች ላይ ባለው አድሎት፣ ወይም በመባረካችን ወይም ባለማበረካችን አይደለም፣ ነገር ግንእምቴ በኢየሱስ ክርስቶስ እና ከእርሱ በተቀበልኩት እውቀት ላይ ነው።”13

ንስሀችን እና ታዛዥነታችን፣ አገልግሎታችን እና መስዋእቶቻችን አስፈላጊ ናቸው። ኤተር “ሁል ጊዜም በርካታ መልካም ነገሮችን (የሚሰሩ)” ብሎ ከገለጻቸው ከነኛ መሀል መሆን እንፈልጋለን።14 ግን በሴሌስቲያል የመዝገብ መጽሀፎች ውስጥ ለሚቀመጠው መዝገብ ስንል አይደለም ብዙውን ምናደርገው። እነዚህ ነገሮች አስፈላጊ የሆኑበት ምክንያት በእግዚአብሄር ስራ ውስጥ ስለሚያሳትፉንና ከተፈጥሮአዊው ሰውነት ወደ ቅዱስነት በምናደርገው ለውጥ ውስጥ ከሱ ጋር የምንተባበርበት መንገድ ነው።15 የሰማይ አባታችን ለኛ የሚያቀርብልን እራሱን እና ልጁን ነው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በአዳኛችን ጸጋ እና አማላጅነት አማካኝነት ከእነርሱ ጋር ያለን ዘላቂ ግንኙነት።

እኛ የእግዚአብሄር ልጆች ነን፤ ለሟች አልባነትና ለዘላለማዊ ህይወት ተለይተን የተቀባን ነን። እጣፈንታችን የሱ ወራሾች እንድንሆን ነው፤ “ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።”16 አባታችን እንደግል ፍላጎታችን በተዘጋጁ እና ለኛ ከሱ ጋር የመጨረሻ ደስታ እንዲኖረን ካለው እቅዱ ጋር በተቀረጹ ደረጃዎች ጋር በሱ የቃልኪዳን መንገድ ላይ ሊመራን ፍቃደኛ ነው። በአባቱ እና በልጁ ላይ የሚያድግ አመኔታ እና እምነትን፣ የበለጠ የነሱን ፍቅር መሰማትን፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ቋሚ መጽናኛ እና ምሪትን መጠበቅ እንችላለን።

ቢሆንም ግን ይሄ መንገድ ለኛ ቀላል ሊሆን አይችልም። ቀላል እንዲሆን ብዙ ንጥረት ያስፈልጋል። ኢየሱስ እንዲህ አለ፤

“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፣ ገበሬውም አባቴ ነው።

“ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ (አባት) ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።”17

በእግዚአብሄር የሚመራው የቆሻሻ ውገዳ እና ጽዳት እንዳንድ ጊዜ በጣም የሚያምና የሚያሰቃይ ይሆናል፤ እንደዛ መሆኑ አስፈላጊ ስለሆነ። የጳውሎስ አገላለጽን ስናስታውስ እኛ “አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር፣ አብረን ወራሾች ነን።”18

ስለዚህ በአንጣሪው እሳት ውስጥ እግዚአብሄር ላይ ከመናደድ ይልቅ ወደ እግዚአብሄር ቅረቡ። በልጁ ስም አባቱን ተጣሩ። በመንፈሱ ቀን በቀን፣ ከእነሱ ጋር ተጓዙ። ታማኝነታቸውን በጊዜ ውስጥ ለእናንተ እንዲያሳዩ ፍቀዱላቸው። የእውነት እነሱን ወደማወቅ ኑ እናም እራሳችሁን ወደማወቅ፡19 እግዚአብሔር ያሸንፍ።20 አዳኙ በድጋሚ ያረጋግጥልናል

“ከአብ ፊት አማላጅ የሆነውን፣ ፊቱም ስለእናንተ እንዲህ በማለት የሚማጸንላችሁን ስሙ--

“አባት ሆይ ሀጥያት ያልሰራውን በእርሱም የተደሰትከውን ስቃይና ሞት ተመልከት፤ የፈሰሰውን የልጅህን ደም ተመልከት፣ ስምህ ይከበር ዘንድ አንተ የሰጠኸውን የልጅህን ደም ተመልከት፤

ስለዚህም፣ አባት ሆይ በስሜ የሚያምኑትን ወደ እኔም መተው ዘላለማዊ ህይወት ይኖራቸው ዘንድ እነዚህ ወንድሞቼን (እና እህቶቼን) አድናቸው።”21

እግዚአብሔርን ስላመኑ፣ የእርሱ ቃል የተገቡ በረከቶች በሕይወት ወይም በሞት ከእነሱ ጋር እንደሚሆን ስለሚተማመኑ አማኝ ሰዎች የተወሰኑ ምሳሌዎችን አስቡ። እምነታቸው እግዚአብሔር በሆነ ሁኔታ ወይም ጊዜ ውስጥ ባደረገው ወይም ባላደረገው ላይ መሰረት አላደረገም፣ ነገር ግን እርሱን እንደ ተወዳጅ አባታቸው እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አማኝ ቤዛቸው በማወቅ ላይ ነው።

አብርሀም በግብጹ ቄስ ኤልካናህ ሊሰዋ ሲል እንዲያድነው ለእግዚአብሄር ጮኸ እናም አዳነው።22 በአብርሐም በእሱ ዘር ሁሉም የምድር ቤተሰቦች እንዲባረኩ የአማኞች አባት ለመሆን ኖረ።23 በፊት ግን በዚሁ መሰዊያ ላይ ተመሳሳዩ የኤልካናህ ቄስ “በንጽህናቸው የተነሳ … ለእንጨት ወይም ለድንጋይ ጣኦት አንሰግድም” ያሉትን ሰውቷል።24 እንደሰማዕታት እዛው ሞቱ።

ወጣት ሳለ በወንድሞቹ ወደ ባርነት የተሸጠው የድሮው ዮሴፍ በስቃዩ ወቅት ወደ እግዚአብሔር ዞረ። ቀስ በቀስ በግብፅ ውስጥ በአለቃው ቤት ውስጥ ታዋቂ በመሆን ተነሳ፣ ነገር ግን በጲጥፋራ ሚስት የተሳሳተ ውንጀላ ምክንያት ሁሉም ነገር ተነጠቀበት። ዮሴፍ “የንፅህነትን ህግ በመጠበቅ የማገኘው እስር ቤት ነውን” በማለት ለማሰብ ይችል ነበር። በምትኩም ወደ እግዚአብሔር በመዞር ቀጠለ እናም በእስር ቤት ውስጥም በለጸገ። ዮሴፍ ጓደኛ ያደረገው ታሳሪ ምንም እንኳን ለዮሴፍ ቃል ገብቶለት ቢሆንም በፈርኦን ግቢ ውስጥ ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ ሁሉንም በመርሳቱ ዮሴፍ የበለጠ አዘነ። መጨረሻ ላይ እንደምታውቁት፣ ጌታ ዮሴፍ የእስራኤል ቤትን እና ሌሎችን እንዲያድን በማስቻል ከፈርኦን ጎን ወደ እምነት እና ኃይል ከፍተኛ ቦታ ላይ ሊያስቀምጠው ጣልቃ ገባ። በእርግጥ፣ “እግዚአብሄርንም ለሚወዱት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ” ዮሴፍ መመስከር ይችላል።25

አቢናዲ መለኮታዊ ስራውን የማከናወን አላማ ነበረው። “ነገር ግን መልእክቴን እጨርሳለው፣ የምድን እስከሆነም (በኔ ላይ የምታደርጉትም)፣ እናም የትም መሄዴ ችግር አያመጣም” ብሏል።26 የሰማእታት ሞት አልቀረለትም ግን በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ድኗል ዕና በሱ የተቀየረው ውዱ አልማ እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጫ ድረስ የኔፋውያንን ታሪክ ቀይሯል።

አልማ እና አሙሌቅ ለልመናቸው መልስ ከአሞኒሀህ እስርቤት ወተዋል እናም አሳዳጆቻቸው ተገለዋል።27 ከዛ በፊት ግን እኚሁ ተመሳሳዮቹ አሳዳጆች አማኝ ሴቶችንና ልጆቻቸውን ወደ ሚንቦገቦግ እሳት ጥለዋል። አልማ በሀዘን ይህን አሰቃቂ ትእይንት ሲመለከት በክብር እግዚአብሄር እንዲቀበላቸው የእግዚአብሄርን ሀይል “እነሱን ከነበልባሉ እሳት”28 ለማዳን እንዳይጠቀም ታግቶ ነበር።29

ነቢዩ ጆስፍ ስሚዝ በሚዙሪ ሊበርቲ አስር ቤት ውስጥ እየማቀቀ ቅዱሳኖቹ በቀዝቃዛው ክረምት ውስጥ ሲዘረፉ እና ከቤታቸው ሲባረሩ እነሱን ለመርዳት አቅም አልነበረውም። “እግዚአብሄር ሆይ የት ነህ?” በማለት ጆሴፍ አለቀሰ። “እስከመቼ እጅህ (ይታገሳል)?”30 በምላሹም ጌታ እንዲህ ቃል ገባ “ጭንቀትህ እና ስቃይህ ለጥቂት ጊዜ ቢሆን ነው፤ ከዚያም በመልካም ይህን ብትፀና፤ እግዚአብሔር ወደ ላይ ዘላለማዊ ክብር ይሰጥሀል ። … እንደ ኢዮብም ገና አይደለህም፤”31

በስተመጨረሻም ጆሴፍ ከኢዮብ ጋር “ቢገድለኝ ስንኳ እርሱን በትግስት እጠባበቃለው።” ብሎ አወጀ።32

ሽማግሌ ብሩክ ፒ. ሄልስ ከጤናማ ዕይታ ጋር ተወልዳ ግን በ11 አመቷ አይነ ስውር ስለሆነችው እህት ፓትርሺያ ፓርኪንሰን ታሪክ አያይዘው ተናግረዋል።

ሽማግሌ ሄልስ እንዲህ አሉ፣ “ፓትን ለብዙ አመታት አውቃታለሁ እናም በቅርቡ ሁልጊዜ ቀና እና ደስተኛ የመሆኗን እውነታ እንደማደንቅ ነገርኳት። አንዲህ መለሰች “ደህና ከእኔ ጋር በቤት አልነበርክም አይደል፣ ነበርክ እንዴ? ጊዜያቶች አሉኝ። በጣም ከባድ የአይምሮ ጭንቀት ነበረብኝ እናም ብዙ አልቅሻለሁ።” ሆኖም እንዲህ ስትል አከለች፣ “እይታዬን ማጣት ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ እንግዳ ነገር ነበር፣ ነገር ግን የሰማይ አባት እና አዳኙ ከቤተሰቤ እና ከእኔ ጋር መሆናቸውን አውቂያለሁ። … አይነ ስውር በመሆኔ እናደድ እንደሆነ ለሚጠይቁኝ እንዲህ እመልሳለሁ፣ ‘በማን ነው የምናደደው? የሰማይ አባት በዚህ ነገር ከእኔ ጋር ነው፤ ብቻዬን አይደለሁም። በሁሉም ጊዜ ከእኔ ጋር ነው።’”33

በስተመጨረሻ ከአባታችንና ከልጁ ጋር ቅርብ እና ዘላቂ ግንኙነትን በረከት ነው የምንሻው። ብዙ ለውጥን ያመጣል እና የምንከፍለው ዋጋ ለዘላለም ይገባዋል፡ ከጳውሎስ ጋር እንዲህ እንመሰክራለን “ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ስቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለው።”34 የሟችነት ልምዳችን ምንም ነገር ቢያመጣ በእግዚአብሄር ማመን እና በሱ ሀሴት ማግኘት እንደምንችል እመሰክራለው።

“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሄር ታመን፤ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ።

በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”35

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።