አጠቃላይ ጉባኤ
የበለጠ የሚያስፈልገውን ነገር አድርጉ
የሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:46

የበለጠ የሚያስፈልገውን ነገር አድርጉ

ሕይወታችንን በኢሱስ ክርስቶስ ላይ ስናተኩር በመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ በእርካታ እና በደስታ እንባረካለን።

ብዙም ሳይርቅ፣ አንድ ውድ ጓደኛ አንዲት ሴትን በዋርዷ ውስጥ ለመጎብኘት መነሳሳትን አገኘች። በደንብ ስለማታውቃት መነሳሳቱን ችላ አለችው—የመነሳሻው ትርጉም አልገባትም ነበር። ነገር ግን ሃሳቡ ወደ እሷ ስለመጣ ተግባራዊ ለማድረግ ወሰነች። እሷን መጎብኘት ብዙም ስላልተመቻት፣ ለሴቲቷ የሆነን ነገር መውሰድ ጭንቀቷን እንደሚቀንስላት ተሰማት። በእርግጥ ባዶ እጇን መሄድ አትችልም! ስለሆነም አይስ ክሬም ገዝታላት የሚደብር ጉብኝት ይሆናል ብላ ወዳሰበችው ጉዞዋን ቀጠለች።

የሴቲቷን በር አንኳኳች፣ እናም ከአጭር ጊዜ በኋላ እህትም በሩን ከፈተች። ጓደኛዬ አይስ ክሬሙን በቡኒ የወረቀት ውስጥ አድርጋ አቀበለቻት እና ንግግራቸውን ጀመሩ። ግቡኝቱ ለምን አስፈላጊ እደነበረ ለመገንዘብ ለጓደኛዬ ብዙም አልወሰደባትም። በረንዳው ላይ ተቀምጠው ሳሉ፣ ሴቲቷ ያጋፍጧት የነበረውን ችግሮች መግለፅ ጀመረች። በሞቃቱ የበጋ የአየር ንብረት ውስጥ ከአንድ ሰዓት ንግግር በኋላ፣ ጓደኛዬ አይስክሬሙ በቡኒው የወረቀት ቦርሳ ስር እየቀለጠ መሆኑን ተገነዘበች።

“በጣም አዝናለው አይስ ክሬምሽ ቀለጠ!” ብላ አለች።

ሴቲቷ በለዘበ አንደበት እንዲህ መለሰች፣ “ችግር የለም! የወተት ውጤቶች አይስማሙኝም!”

ለነብዩ ሌሂ ጌታ በህልም እንዲህ ተናገረው፣ “ሌሂ ባደረግሃቸው ነገሮች ምክያት የተባረክህ ነህ።”1

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ተስፋ ከማድረግ እና ከማመን የላቀ ነው። ጥረትን፣ እንቅስቃሴን እና ቆራጥነትን ይጠይቃል። የሆነ ነገር እንድናደርግ ይጠይቃል፣ “ቃሉን የምናደርግ እንጂ የምንሰማ ብቻ መሆን የለብንም።”2

በቀለጠው አይስ ክሬም ጉዳይ ላይ፣ ምንድን ነው የበለጠ አስፈላጊ የሆነው? አይስ ክሬሙ ነውን? ወይም ጓደኛዬ የሆነ ነገር ማድረጓ ነው?

አንድ ውድ ወጣት ሴት እንደዚህ ዓይነት ከልብ የሆነ ጥያቄ ስትጠይቀኝ ደስ የሚል ልምድ አጋጠመኝ፣ “እህት ክሬቭን፣ ስለቤተክርስቲያኗ የሆነ ማንኛውን ነገር እውነት እንደሆነ እንዴት ነው የምታውቂው? ምክንይቱም እኔ ምንም አይሰማኝም።”

ወደ መልሱ ከመግባቴ በፊት የተወሰኑ ጥያቄዎችን መጀመሪያ ጠየቅኳት። “ስለ ግላዊ የቅዱሳት መጽሐፍ ጥናትሽ ንገሪኝ።”

“ቅዱሳት መጻህፍትን አላነብም” ብላ መለሰች።

“ከቤተሰባችሁስ ጋር? ብዬ ጠየቅኳት። ኑ ተከተሉኝን አብረሽ ታጠኛለሽን?” ብዬ ጠየቅኳት።

“አላጠናም” ብላ መለሰች።

“ስትጸልዪ ምን ይሰማሻል?” ብዬ ስለጸሎት ጠየቅኳት።

“አልጸልይም” ነበር መልሷ።

የኔ ምላሽ እዲህ ነበር፣ “የሆነ ነገር ማወቅ ከፈለግሽ፣ የሆነ ነገር ማድረግ ይኖርብሻል።”

ለመማር ወይም ለማወቅ ለምንፈልገው ማንኛውም ነገር ይህ እውነት አይደለምን? አዲሷን ጓደኛዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማድረግ እንድትጀምር ጋበዝኳት፣ እነሱም መጸለይ፣ ማጥናት፣ ሌሎችን ማገልገል እና በጌታ ማመን ናቸው። ምንም ነገር ሳይደረግ መለወጥ አይመጣም። ለማወቅ በመጠየቅ፣ በመሻት እና በማንኳኳት ጥረት ስናደርግ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት ይመጣል። በማድረግ ይመጣል።3

በትምህርት እና ቃል ኪዳን ውስጥ ጌታ አንድ አንድ ጊዜ እንዲህ ይላል፣ “አያስፈልግም።”4 የተወሰኑ ነገሮች የማያስፈልጉ ከሆኑ ወይም ጥቅማቸው ትንሽ ከሆነ፣ የሚያስፈልጉ ነገሮች እንዳሉ እንዳስብ ያደርገኛል። የሆነ ነገር በማድረግ ወይም ማንኛውንም ነገር በማድረግ፣ ጥረታችን ውስጥ እንዲህ ብለን እራሳችንን እንጠይቅ ይሆናል፣ “የበለጠ ምን አስፈላጊ ነው?”

አስተዋዋቂዎች ብዙውን ጊዜ የሚሸጡትን ምርት ለደስታችን ወይም ለጤናችን አስፈላጊ እንደሆኑ ሊያሳምኑን “ጠቃሚ” ወይም “ሊኖራቹ ይገባል” ያሉበትን መፈክሮች ይጠቀማሉ። ነገር ግን የሚሸጡት ነገሮች በእርግጥ አስፈላጊ ናቸውን? በእርግጥ ሊኖረን ይገባናልን? በእርግጥ አስፈላጊ ነውን?

ሊታሰብባቸው የሚገቡ አንዳንድ ሃሳቦች እነኚህ ናቸው። የበለጠ የሚያስፈልገውን ነገር ምንድን ነው?

  • በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ውስጥ ምን ያህል “መውደዶች” ማግኘታችን ነውን? ወይም በሰማይ አባታችን ምን ያህል እንደምንወደድ እና እንደምንፈለግ ነውን?

  • ዘመንኛ የሚባሉትን መልበስ ነውን? ወይም አግባብ ያላቸውን በመልበስ ለአካላችን ክብር ማሳየት ነውን?

  • መልሶችን ከይነመረብ በመፈለግ ማግኘት ነውን? ወይም መልሶችን ከእግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት መቀበል ነውን?

  • የበለጠ በመሻት ነውን? ወይም በተሰጠን ነገር በመርካት ነውን?

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ አስተማሩ፦

“መንፈስ ቅዱስ እንደ ጓደኛችሁ በመሆን፣ ማህበረሰባችንን የመታውን የዝነኛ ባህል አሻግራችሁ ማየት ትችላላችሁ። የቀድሞ ትውልዶች ከሆኑት በላይ የበለጠ ብልሆች መሆን ትችላላችሁ። …

ለተቀረው ዓለም አርዓያ አስቀምጡ!”5

ለዘለቄታዊ ደስታ በእውነት ጠቃሚ የሆነ ነገር ላይ አተኩሮ መቆየት ጥረትን ይወስዳል። ከዘለአለማዊ ዋጋዎቻችን ከማስራቅ ውድ ሰዓቶችን፣ ችሎታዎችን ወይም መንፈሳዊ ጥንካሬን በማይረቡ ነገሮ ላይ እንድናጠፋ ከማድረግ የበለጠ ሰይጣን ምንም አይፈልግም። የበለጠ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች የሚያሰናክሉንን ነገሮችን በጸሎት እንድናስብ እያንዳንዳችንን እጋብዛለው።

የታላቅ ልጃችን የሶስተኛ ክፍል አስተማሪ ተማሪዎቿን “አእምሮአቸውን እንዲቆጣጠሩ” አስተማረች። ለወጣት ተማሪዎቿ ሃሳባቸውን መቆጣጠር ስለሚችሉ እና የሚያደርጉትን ነገር መቆጣጠር እንደሚችሉ ማስታወሻ ነበር። ብዙም ጥቅም ወደሌላቸው ነገር ተስቤ እራሴን ሳገኝ “የእኔን አእምሮ እንድቆጣጠር” እራሴን እንዳስታውስ አደርጋለሁ።

አንድ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በተወሰኑ የቤተክርስቲያን ወጣቶች መካከል ንስሃ በኋላ ለመግባት በማቀድ ትዕዛዛትን ችላ ማለት ታዋቂ እየሆነ እንደመጣ ነገረኝ። ይህም “የክብር መአረግ እንደሆነ” ተነገረኝ። በእርግጥ፣ “በእውነተኛ ስሜት”6 በትህትና ንስሃ ለሚገቡት ሰዎች ጌታ ይቅርታ ማድረጉን ይቀጥላል። ነገር ግን የአዳኙ ምህረት የተሞላበት የኃጢያት ክፍያ በእንደዚህ ዓይነት የመሳለቂያ መንገድ መጠቀም የለበትም። ስለጠፋው አንድ በግ ምሳሌ እናውቃለን። በእርግጥ፣ አንድ እረኛ 99 በጎችን ትቶ አንድ የጠፋውን በግ ፍለጋ ይሄዳል። ነገር ግን 99ኞች ለመሆን የመረጡት በጎች ለመልካሙ እረኛ የሚያመጡትን ደስታ ማሰብ ትችላላችሁን? አብረው የሚሆኑ እና ቃል ኪዳናቸውን ለመጠበቅ እርስ በእርስ የሚረዳዱን? ታዛዥ መሆን ታዋቂ ነገር ቢሆን ዓለም ወይም ትምህርት ቤታችሁ ወይም ስራችሁ ወይም ቤታችሁ ምን እንደሚሆኑ ማሰብ ትችላላችሁን? ህይወትን በፍፁም ስለመኖር አይደለም—ከጌታ ጋር የገባነውን ቃል ኪዳኖች ለመኖር የተቻለንን በማድረግ ደስታን ስለማግኘት ነው።

ስለ እግዚአብሔር የበለጠ ጥርጣሬን እና ግራ መጋባትን እና ቀጣይነት ያለውን ግፊት እየገለፀ ባለ ዓለም ውስጥ፣ ይህ ወደ ነቢይ መቅረብ ያለብን ጊዜ ነው። እሱ እንደ ጌታ ቃል አቀባይ በመሆኑ እሱ የሚያበረታታውን፣ የሚመክረውን እና የሚማፀነውን ነገሮች ማድረግ የበለጠ ጠቃሚ እንደሆነ ማመን እንችላለን።

ምንም እንኳን ቀላል ባይሆንም፣ ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ሁሌም መንገድ አለ። በትምህርት ቤት ውስጥ ከጓደኞች ጋር በመነጋገር፣ ንግግሩ የቤተክርስቲያኗን አቋሞች ወደመተቸት ሲለወጥ የአንድ ወጣት ልብ ተሰበረ። ዝም ማለት እንደማትችል ተገነዘበች—የሆነ ነገር ማድረግ ነበረባት። ክብር በተሞለው መልኩ፣ ስለ የሰማይ አባት ፍቅር እና እርሱ ያስቀመጠው ትዕዛዛት ልጆቹን ለመባረክ እና ለመጠበቅ እንደሆነ ተናገረች። ምንም አለማድረግ የበለጠ ቀላል ይሆን ነበር ለእሷ። ነገር ግን ምንድን ነው የበለጠ አስፈላጊ የሆነው? ከሌሎቹ ጋር መመሳሰል? ወይም “በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ነገር እና በሁሉም ቦታ” እንደ የእግዚአብሔር ምስክር ሆኖ መቆም?7

በዳግም የተመለሰውችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከጨለማ መውጣት ካለባት፣ እኛም ከጨለማ መውጣት አለብን። እንደ ቃል ኪዳን ጠባቂ ሴቶች፣ በመሻሻል እና ተለይተን በመቆም የወንጌል ብርሃናችንን በዓለም ዙሪያ ማንፀባረቅ አለብን። ይህንን በጋራ እንደ የእግዚአብሔር ሴት ልጆች እናደርጋለን—ከ11 ዓመት ጀምሮ ያሉ የ8.2 ሚሊዮኖች ሴቶች ኃይል በተመሳሳይ መንገድ ነው የሚሰራው። በማዳን ስራ ውስጥ ስንሳተፍ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለመኖር ስንጥር፣ ፍላጎት ያላቸውን ስንንከባከብ፣ ሁሉንም ወንጌልን እንዲቀበሉ ስንጋብዝ እና ቤተሰቦችን ለዘላለም ስናገናኝ እስራኤልን እየሰበሰብን ነን።8 የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የተግባር እና የደስታ ወንጌል ነው። የበለጠ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን የማድግ ችሎታችንን አንናቅ። የእኛ መለኮታዊ ውርስ አፍቃሪው የሰማይ አባታችን እንድናደርግ እና እንድንሆን እንደምንችል የሚያውቀውን ለማከናወን ብርታት እና በራስ መተማመን ይሰጠናል።

ለዚህ ዓመት የወጣቶች ጭብጥ ከምሳሌ 3፥5–6 ነው፦

“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን በራስህም ማስተዋል አትደገፍ።

በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”

በጌታ ማመን ቁልፋማ አካል ሁሉንም መልስ ባይኖረን እንኳን እርሱ እንደሚመራን በማመን ወደ ፊት መሄድ ነው።

እህቶች ስለ አይስ ክሬሙ አይደለም። እንዲሁም የበለጠ ስለማድረግ አይደለም። የሚያስፈልገውን ነገር ስለማድረግ ነው። ይህም በለጠ እንደ እርሱ ለመሆን ስንጥር የክርስቶስን ትምህርት በህይወታችን ውስጥ መተግበር ነው።

በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ለመቆየት የበለጠ ስንሰራ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን እምነታችን የበለጠ ያድጋል። የበለጠ እምነታችን ሲያድግ፣ ንስሃ የመግባት ፍላጎታችን የበለጠ ይሆናል። እናም የበለጠ ንስሃ ስንገባ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን የቃል ኪዳን ግንኙነት የበለጠ እናጠነክራለን። ያ የቃል ኪዳን ግንኙነት ወደ ቤተመቅደስ ይስበናል ምክንያቱም እስከ መጨረሻ የምንፀናው የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን በመጠበቅ ነው።

ሕይወታችንን በኢሱስ ክርስቶስ ላይ ስናተኩር የበለጠ አስፈላጊ የሆነ ነገርን እንድናደርግ እንመራለን። እናም በመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ በእርካታ እና በደስታ እንባረካለን! በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. 1 ኔፊ 2፥1፣ አትኩሮት ተጨምሮበታል።

  2. ያዕቆብ 1፥22

  3. አልማ 5፥45–46፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የኢየሱስ ክርስቶስን ሀይል ወደ ህይወታችን መሳብ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 39-42 ይመልከቱ።

  4. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥280፥3 ይመልከቱ።

  5. ረስልኤም ኔልሰን፣ “Hope of Israel” (ዓለም አቀፋዊ የወጣቶች አምልኮ፣ ሰኔ3፣ 2018 እ.አ.አ)፣ HopeofIsrael.ChurchofJesusChrist.org።

  6. ሞሮኒ 6፥8

  7. ሞዛያ 18፥9፤ እንዲሁም “የወጣት ሴቶች ጭብጥን፣” ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

  8. አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ-በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል1.2፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።