የመግቢያ መልክቶች
በዚህ ልዩ ስብሰባ ሀሳባቸው በሆነው እና የእነርሱ የሆኑ አወቃቀሮች ላይ በማተኮር የእግዚሐብሄር ሴት ልጆች የሆኑትን እናከብራለን።
ይህን ልዩ የሴቶች አጠቃላይ ጉባኤ ስብሰባ ስንጀምር፣ ይህን የመጀመሪያ አመራር የመግቢያ መልእክት በማቅረብ ደስተኛ ነኝ።
የቅዳሜ ስብሰባችን የተለያዩ አላማዎች እና የተለያዩ ተመልካቾችን የያዘ ታሪክ አለው። ይህን ምሽት አዲስ አላማ ላይ እና መምጣቱ ስለማይቀረው የወደፊት ጊዜ፣ ሂደት ላይ ስናቶክር፣ በዚያ ታሪክ ላይ አንጨምራለን። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አይለወጥም። የወንጌሉ አስተምሮት አይለወጡም። የግል ቃል ኪዳኖቻችን አይለወጡም። ነገር ግን በአመታት ውስጥ፣ መልእክታችንን ለማስተላለፍ የምንጠጠቀመው ስብሰባዎች ይለወጣሉ እናም በሚጡት አመታት መለወጣቸውን ይቀጥላሉ።
ለአሁን፣ ይህ የአጠቃላይ ጉባኤ፣ የቅዳሜ ምሽት ስብሰባ የምንም ተቋም ስብሰባ አይደለም። እንደ ሁሉም የአጠቃላይ ጉባኤ ስብሰባዎች፣ እቅዱ፣ ተናጋሪዎቹ እና ሙዚቃው በመጀመሪያ አመራር የተዘጋጁ ናቸው።
የሴቶች መረዳጃ ክፍል ፕሬዘዳንት የሆነችውን ጄን ቢ. ቢንጋም ይህን ስብሰባ እንድትመራ ጠይቀናል። ወደፊት የሚመጡ የቅዳሜ ምሽት ስብሰባዎች በሌሎች የቤተክርስቲያን አጠቃላይ አመራር አንዱ ከሆኑት፣ እንዲሁም በቀዳሚ አመራር ምርጭ መሰረት የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣ የወጣት ሴቶች እና የመጀመሪያ ክፍል አጠቃላይ አመራሮች አባላት፣ ሊመራ ይችላል።
ይህን ምሽት፣ ይህ የቅዳሜ ምሽት አጠቃላይ ጉባኤ ስብሰባ፣ የኋለኛዋ ቀን ቅዱሳን ሴት ሀሳብ ላይ ያቶኮረ ይሆናል። ይህ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ፣ በተለይ ከሴቶች ጋር የሚዛመደው የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲዎች፣ እና የቤተክርስቲያኗን ሴቶች እና ልጃገረዶች የሚያካትቱ የተቋሞች ሰራተኞች አጠቃላይ ሀላፊነቶች እና ስራዎችን ይጨምራል። ይህም ስብሰባ እንደ ሁሉም የአጠቃላይ ጉባኤ ስብሰባ በስፋት አለም አቀፍ ለሆነ ተመላካች ስርጭቱ ቢተላለፍም፣ በዚህ ጉባኤ ስብሰባ መሀል አንዲገኙ የተጋበዙት ሴቶች እና እድሜያቸው 12 እና ከዛ በላይ ላሉ ሴት ልጆች ነው። ተሳትፎ ባላቸው ኣወቃቀሮች ላይ በበላይነት እንዲመሩ አንዳንድ የክህነት ስልጥን መሪዎችን አካተናል።
እዚህ እየጀመርን ያለነው በአሁኑ ጊዜ ለጌታ ዓለም አቀፋዊ የቤተክርስቲያን አመራር እና አባልነት ላሉ የመገናኛ ምንጮች ምላሽ የሚሰጥ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አስተምሮት ለሁሉም ነው። ታዲያ ይህ ተነሳሽነታችን ነው እናም የማሰራጨት መጠን ነው። በዚህ ልዩ ስብሰባ ሀሳባቸው በሆነው እና የእነርሱ የሆኑ አወቃቀሮች ላይ በማተኮር የእግዚሐብሄር ሴት ልጆች የሆኑትን እናከብራለን።
ቀጥታ ስርጭት ቴክኖሎጂ በአሁን ሰአት የቤተክርስቲያን መሪዎችን ግልጽ የሆነ ስልጠናን በአከባቢው ላይ ላሉ ግላዊ በሆነ መንገድ ለተመልካቾች ማድረስ በማስቻሉ አመስጋኞች ነን። አሁን ያለው የጉዞ እድሎች እየጨመሩ መምጣታቸውንም እንቀበላለን። ይህ በአሁን ሰአት ያሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች የተፈለጉ ጊዜያዊ የአመራር ስልጠናዎችን ፊት ለፊት በመገናኘት አንዲሰጡ ይረዳናል።
ይህ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ስራ ነው። እኛ በእርሱ መንፈስ ቅዱስ የምንመራ የእርሱ አገልጋዮች ነን። በእነዚህ ተቋማት መሪዎች እና በእነዚህ ተቋማት ውስጥ እና በግላዊ ሕይወታቸው ውስጥ ጌታን ለሚያገለግሉ አማኝ ሴቶች እና ልጃገረዶች የጌታችንን በረከቶች እንማጸናለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።