አጠቃላይ ጉባኤ
በኋለኞቹ ቀናት ውስጥ ጀግናዊ ደቀመዝሙርነት
የሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:18

በኋለኞቹ ቀናት ውስጥ ጀግናዊ ደቀመዝሙርነት

በዚ በመጨረሻው ሰአት የጌታን ብርሀን ከፍ አርገን ስንይዝ በራሳችን እንተማመን ፣ ያዘንን አንሁን ፣ ጀግና፣ አይናፋር አንሁን፣ ታማኝ፣ ፈሪ አንሁን፡፡

ነጻ ምርጫ ለእያንዳንዱ ልጆቹን የተሰጠ የእግዚአብሔር የከበረ ስጦታ ነው፡፡1 እናም እኛ ሁሉን ሰው በሚማልደው አማካኝነት ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ፣ ወይም እንደዲያብሎስ ምርኮና ሀይል ምርኮንና ሞትን ለመምረጥ ነፃ ናቸው።”2 እግዚአብሄር ጥሩ እንድንሰራ አያስገድደንም ፤ ሴጣንም እርኩሰት እንድንፈጽም ሊያስገድደን አይችልም ፡፡3 ሟችነት በእግዚአብሔር እና በተቃዋሚ መካከል ያለ ፉክክር ነው ብለው የተወሰኑ ሰዎች ቢያስቡም፣ ከአዳኙ በወጣ አንድ ቃል “ሴጣን ዝም ይላል እንዲሁም ይጠፋል። … እና (የኛ) ጥንካሬ ነው የሚፈተነው የእግዚአብሄር አይደለም፡፡”4

በስተመጨረሻ የእድሜ ልክ ምርጫዎቻችን የዘሩትን እናጭዳለን፡፡5 ስለዚህ የሀሳቦቻችን፣ ፍላጎቶቻችን፣ ቃላቶቻችን፣ እና ስራዎቻችን አጠቃላይ ድምር ለአዳኛችን፣ ለተመረጡ አገልጋዮቹ ፣ እና ዳግም ለተመለሰው ቤተክርስቲያኑ ስላለን ፍቅር ምን ይናገራሉ? ከአለም ሙገሳ ወይም በማህበራዊ ድህረገጽ ከምናገኘው የላይክ ብዛት ይልቅ የጥምቀታችን፣ የክህነታችን፣ እና የቤተመቅደስ ቃልኪዳኖቻችን ይበልጡብናል? ለጌታና ለትእዛዛቶቹ ያለን ፍቅር ለሌላ ለማንኛውም ነገር ወይም በዚ ህይወት ውስጥ ላለ ለማንኛውም ሰው ካለን ፍቅር ጠንካራ ነው?

ጠላቱና ተከታዮቹ ሁሌም የክርስቶስንና የነብያቶቹን ስራ ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ የእግዚአብሄር ትእዛዛት፤ ሙሉ በሙሉም እንኳን ባይተዉም፤ በብዙዎች እዚህ አለም ላይ ባሉ ትርጉም አልባ ነው ተብሎ ተስተባብሎአል፡፡ “የማይመቹ” እውነታዎችን የሚያሰተምሩ የእግዚአብሄር መልእክተኞች ብዙ ጊዜ ችላ ይባላሉ፡፡ አዳኙ እራሱ እንኳን “በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ”ተብሏል6 ፤ የህዝብ ስሜትን በመረበሽና በመከፋፈል ተከሷል፡፡ ደካማና ተመሳጣሪ ነፍሶች “እንዴት አድርገው በነገር እንዲያደምጡት ተማከሩ”7 እና የሱ የቀድሞ ክርስቲያኖች “ወገን” ፤ “በየስፍራው ሁሉ ይቃወማሉ፡፡”8

አዳኙና የቀድሞ ተከታዮቹ ከባድ ውስጣዊና ውጪያዊ ቅራኔ ደርሶባቸዋል ፤ እና እኛም ተመሳሳይ ነገር ያጋጥመናል፡፡ ዛሬ ከአለማዊያን አንዳንዴ ጥቂት የእውን እና ምናባዊ የጥላቻ ጣቶች ሳይቀሰርብን በቆራጥነት እምነታችንን መኖር የማይቻል ሊሆን ትንሽ ነው የቀረው፡፡ በእርግጠኝነት አዳኙን መከተል ሽልማት አለው ፤ ነገር ግን አንዳንዴ አይን በሚጣልባቸው ፤ እግዚአብሄር በጣም ስለሚወደን ትንሽዬ ሀጢአትን ያሳልፋል በሚለው የተሳሳተ እምነት በክርስቶስ ላይ እምነትን፣ ታዛዥነትን፣ እና ንስሀን በሚተኩት፤ “ብሉ፣ ጠጡ፣ እናም ተደሰቱ ”9 ሚለውን ፍልስፍና በሚያራምዱ እንያዛለን፡፡

“(በእራሱ) ድምጽ ሆነ (በአገልጋዮቹ) ድምጽ” ፣ በመናገር፡10 ስለኛ ቀናት አዳኙ “ህይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሱበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን …እንደገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ” እና ብዙዎች “እውነትን ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፣ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ” ብሎ አልተናገረም?11 “የሰውም ስርአት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል” አላለም?12 “ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሱ እኔ አቃለው” ብሎ አላስጠነቀቀንም?13 “ (ክፉው) መልካም (መልካሙ) ክፉ ተብሎ እንደሚጠራ”14 ቀድሞ አላየም እና “ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶቹ (እንደሚሆኑበት )”?15

ስለዚህ እኛስ? መሸበር ወይም መፍራት አለብን? ሀይማኖታችንን በዋና መነጸር አሻግሮ ማሳያ ጥልቀት መኖር አለብን? በእርግጥ የለብንም! በክርስቶስ እምነት የሰዎችን ዘለፋ አትፍሩ፣ ወይም ስድባቸውንም አትፍሩ፡፡16 አዳኙ ከላይ ሆኖ እና ሊመሩን በህይወት ያሉ ነቢያቶች እያሉ “ማን ይቃወመናል?”17 በዚ በመጨረሻው ሰአት የጌታን ብርሀን ከፍ አርገን ስንይዝ በራሳችን እንተማመን ፣ ያዘንን አንሁን ፣ ጀግና፣ አይናፋር አንሁን፣ ታማኝ፣ ፈሪ አንሁን፡፡18

“አዳኙ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለው፡፡ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ ደግሞ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እክደዋለው፡፡”19

በማስከተልም አንዳንዶች ያለትእዛዝ የሚመጣን እግዚአብሄር ቢፈልጉም ፣ በኤልደር ዲ. ታድ ክሪስቶፈርሰን “ምንም የማይጠይቅ እግዚአብሄር ከሌለ እግዚአብሄር ጋር እኩል ነው” የሚል ቃል በድፍረት እንመስክር፡፡20

አንዳንዶች የሚከተሉትን ትእዛዛት መምረጥ ቢፈልጉም፣ “ከእግዚአብሄር አንደበት ከሚወጣው በእያንዳንዱ ቃል እንድትኖሩ” የሚለውን የአዳኙን ግብዣ በደስታ እንቀበል፡፡ እና ከእግዚአብሔር አንደበት ከሚመጣው በእያንዳንዱ ቃል እንድትኖሩ ዘንድ፣ ክፉን ሁሉ እንድትተዉና በጥሩ ነገሮች ላይ እንድትጸኑ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።21

አንዳንዶች ጌታና ቤተክርስቲያኑ “ልባችን የፈቀደውን” ለማድረግ እንደሚከለክሉ ቢያምኑም፣ 22 በጀግንነት “ክፉውን ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል” ብለን እናውጅ23 ምክንያቱም “እግዚአብሄር ትክክል አይደለም ብሎ ያወጀውን ብዙ ህዝብ ትክክል ማድረግ አይችልም፡፡”24

“አስታውስ…የእግዚአብሄር ትዛዛት እንዴት ጥብቅ (ሆኖም ነጻ አውጪ) እንደሆኑ አስታውስ፡፡”25 በግልጽ እነሱን ማሰተማር አንዳንዴ እንደ አለመቻቻልነት ድርጊት ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ ስለዚህ ከኛ የተለየ እምነት ያለውን የእግዚአብሄር ልጅ የሚቻል ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ እንደሆነ በአክብሮት እናሳያቸው፡፡

ከጌታ ፍቃድ ጋር የማይሄዱ እምነቶችን እና ድርጊቶችን ሳንደግፍ ሌሎችን መቀበልና ማክበር እንችላለን፡፡ እወነትን በመስማማትና በማህበራዊ ተወዳጅነት መሰዊያ ላይ መሰዋት አያስፈልግም፡፡

ጺዮንና ባቢሎን አይስማሙም፡፡ “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፡፡”26 “ሁላችንም ስለ ምን ጌታ ሆይ ሆይ ትሉኛላችሁ የምለውንም አታደርጉም ?” ሚለውን የአዳኙን ዘልቆ የሚገባ ጥያቄ እናስታውስ፡፡27

ለጌታ ያለንን ፍቅር በልባዊ፣ በበጎ ፍቃድ ታዛዥነት እናሳይ፡፡

በደቀመዝሙርነታችሁና በአለም መሀል እንደተያዛችሁ ከተሰማችሁ፣ አፍቃሪው አዳኛችሁ “ግብዣን ልኳል፣ የምህረት ክንድ (ወደ እናንተ) ተዘርግቶአልና ፣ እናም እንዲህ ይላል፤ ንስሀ ግቡ እኔም እቀበላችኋለው፡፡”28

ፕሬዘዳንት ረስልኤም.ኔልሰን እየሱስ ክርስቶስ “እጅግ ታላቅ ስራውን አሁን አሁን እና ተመልሶ በሚመጣበት መካከል ያከናውናል” ብለው አስተምረዋል፡፡29 እንዲሁም ደግሞ “የእግዚአብሄርን መንገድ የሚመርጡ በመከራ ይጸናሉ” በለው አስተምረዋል፡፡30 “ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነ(ን) ስለተቆጠ(ርን)”31 እኛ “ድምጹ ከሌሎች ድምጾች በላይ ቅድሚያውን እንድይዝ (ስንፈቅድለት)” አንዳንዴ እጣፋንታችን ሊሆን ይችላል፡፡32

“በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብጹህ ነው”ብሏል አዳኙ፡፡33 ሌላ ቦታ “ህግህን ለሚወዱ ብዙ ሰላም ነው፤ (ምንም) እንቅፋትም የለባቸውም”ተብሎ እንማራለን፡፡34 ምንም! ስለዚህ ራሳችንን እንጠይቅ “ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ስር (የለኝም) በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው እሰናከላለው?”35 በእየሱስ ክርስቶስ አለትና በአገልጋዮቹ ላይ በጽናት ተገንብቻለው?

የሞራል አንጻራዊያን እውነታ በማህበረሰብ የተፈጠረ ብቻ ነው፣ ከምንም ጋር ያልተያያዘ እራሱን የቻለ የተቀመጠ ሞራል የለም፡፡ በእውነት እያሉ ያሉት ሀጢአት የለም ነው፤36 “ማንም ሰው ያደርገው የነበረው ሁሉ ወንጀል አይደለም”37 ጠላት በኩራት ደራሲነቱን ሚቀናጅበት ፍልስፍና ነው ይህ፡፡ የበግ ልብስ ለብሰው ሁሌ ከሚቀጥሩ እና “ብዙ ጊዜ (የራሳቸውን) የባህሪ ጉድለት በእውቀት ገደባቸውን ለመሸፈን ከሚጠቀሙ ”ተኩላዎች እራሳችንን እንጠብቅ፡፡38

የእወነት የክርስቶስ ጀግና ደቀመዝሙር መሆን ከፈለግን መንገድ እናገኛለን፡፡ ካልሆነ ጠላት የሚስቡ አማራጮችን ያቀርብልናል፡፡ ግን እንደ ታማኝ ደቀመዝሙሮች “ለእምነቶቻችን ይቅርታ መጠየቅ ወይም እውነት እንደሆነ ከምናውቀው ነገር ወደ ኋላ ማለት የለብንም፡፡”39

ለመዝጊያ ከኋላዬ ስለተቀመጡት 15 የእግዚአብሄር አገልጋዮች ልናገር፡፡ አለማዊያን “ባለራእዮቹን አትመልከቱ ይላሉ ፤ ነቢያቱንም አትንገሩን ይላሉ”፤40 ታማኞች “ከላይ በሚመጡም በረከቶችም፣ አዎን፣ እናም ጥቂት ባልሆኑ ትእዛዛት ፣ እናም በጊዜአቸውም ራእይና አክሊልን ይቀበላሉ፡፡”41

በማያስገርም ሁኔታ እነዚህ ሰዎች ነቢያቶች ሲያውጁ በእግዚአብሄር ቃል ላልተደሰቱት የመብረቅ ዘንግ ይሆናሉ አብዛኛውን ግዜ፡፡ “በመጽሀፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም” ወይም የሰው ፍቃድ ውጤት አለመሆኑን “ዳሩ ግን በእግዚአብሄር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው (አሁን ላይ እንደሚናገሩ)” ነብዩን የሚቃወሙ ሰዎች አይረዱም፡፡42

እንደ ጳውሎስ እኚህ የእግዚአብሄር ሰዎች “በጌታችን ምስክርነት (አያፍሩም)” እና የሱ “እስረኞች”43 ናቸው ማለትም የሚያስተምሩት አስተምሮት የነሱ ሳይሆን ነገር ግን የጠራቸው ነው፡፡ እንደ ጴጥሮስ እነሱም “ (ያዩትንና የሰሙትን) ከመናገር ዝም ማለት (አይችሉም)፡፡”44 የመጀመሪያዎቹ አመራሮችና አስራሁለቱ ጉባኤዎች እግዚአብሄርን እና ልጆቹን የሚወዱ እናም በእርሱም የሚወደዱ ጥሩ እና ታማን ሰዎች ናቸው፡፡ ቃሎቻቸውን ከጌታ ከራሱ አፍ እንደወጣ አድርገን “ (በ)ሁሉ ትእግስት እና እምነት መቀበል አለብን፡፡ ምክንያቱም ይህን ስታደርጉ የሲኦል ደጆችም (አያሸንፉንም)፤ አዎን እናም ጌታ አምላክ የጭለማን ሀይል (ከላያችን) ላይ ይገፋል፡፡”45

“ምንም የቆሸሸ እጅ ስራው ወደፊት እንዳይገፋ ሊያስቆም አይችልም”46 በአሸናፊነት ከእናንተ ወይም ከኔ ጋር ሆነም አልሆነም መዝመቱ አይቀርም ስለዚህ “የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ፡፡”47 ከታላቁ እና ከሰፊው ህንጻ በሚመጣው ጮክ ያለ የጠላት ድምጽ አትሸወዱ ወይም አትሸበሩ፡፡ የነሱ ተስፋ የቆረጠ ጩኸት በተሰበሩ ልቦችና በተዋረዱ ነፍሶች ላይ ጸጥ ካለው ከትንሹ ድምጽ የተረጋጋ ተጽእኖ ጋር በምንም አይወዳደርም፡፡

ክርስቶስ ህያው እንደሆነ፣ አዳኛችንና መዳኒታችን እንደሆነ እና “በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን” እንዳንሄድ ለማረጋገጥ በመጀመሪያዎቹ አመራሮችና በአስራ ሁለቱ ሀዋሪያት አባላቶች አማካኝነት ቤተክርስቲያኑን እንደሚመራ እመሰክራለው፡፡48

ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዳስተማሩት “እውነተኛ የእየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ብቻቸውን ለመቆም፣ ለመናገር፣ ከአለም ህዝቦች የተለዩ ለመሆን ፍቃደኞች ናቸው፡፡ ተስፋ ማይቆርጡ፣ ትጉ እና ደፋር ናቸው፡፡”49

ወንድሞችና እህቶች መልካም ለመሆን መልካም ቀን ነው! በተቀደሰው በእየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን፡፡