“አሁን ክርስቶስ ተነስቷል፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ መስከረም 2023 (እ.አ.አ)።
ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ መስከረም 2023 (እ.አ.አ)
አሁን ክርስቶስ ተነስቷል
ሐዋርያውጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ያስተማረውን እወቁ።
አሁን ክርስቶስ ከሙታን መካከል ተነስቷል
ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞተ፣ ተቀበረ እናም በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ።
ላንቀላፉት በኩራት
በኩራት ለሚለውን እዚህ ጋር የተጠቀሙት የግሪክ ቃል የዓመቱ የመጀመሪያ ሰብል ማለት ነው። በቅድሚያ የሚሰበሰበው ነው—ገና ከሚመጡት ከብዙዎቹ መጀመሪያው ነው።
ላንቀላፉት የሚለው ሐረግ “ለሞቱት” ማለት ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ለማድረግ የመጀመሪያው ነበር፣ እና ከትንሳኤውም በኋላ፣ ሁሉም ሰዎች ይነሳሉ።
ሞት በሰው በኩል መጣ
ይህ የሚናገረው ስለ አዳም ነው። የእርሱ ውድቀት ትርጉም ወደ ዓለም የሚመጡ ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ ማለት ነው። (ሙሴ 4ን ተመልከቱ።)
ሁሉ በክርስቶስ ህያዋን ይሆናሉ
በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ምክንያት ሁሉም ሰዎች ከሞት ይነሳሉ። ይህ ማለት የኖረ ወይም የሚኖር ሁሉ ከሞት ይነሳል ማለት ነው። መንፈሳችን ከአካላችን ጋር ይገናኛል፣ እናም ሰውነታችን ፍጹም እና የማይሞት ይሆናል። (አልማ 11፥43–45 ተመልከቱ።)
© 2023 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የ Monthly For the Strength of Youth Message, September 2023. ትርጉም። Language. 19047 506