ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)
የክብር መንግስቶች
ከዋናው ጽሁፍ የወጣ አጭር ክፍል።
ዳግም በተመለሰችው በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በኩል የተገለጠው አስተምህሮት ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች—በዚህ ጊዜ በግምት ውስጥ ለመክተት ጥቂቶች ከሆኑት በስተቀር—በስተመጨረሻ ከሁሉም ታናሽ የሆነውንም በመመልከት “አዕምሮን ሁሉ [የሚያልፍ]” ከሆኑት ከሶስቱ የግርማ መንግስቶች ውስጥ ወደ አንዱ ደረጃ እንደሚገቡ ያስተምራል [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥89]። …
ዳግም ከተመለሰችው ቤተክርስቲያን ሌላ ልዩ ትምህርት እና ልምምድ፣ ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ላለው ከፍተኛ የክብር ደረጃ ብቁ የመሆንን የተቀደሰ እድል የሚያቀርቡ የተገለጡ ትእዛዛት እና ቃል ኪዳኖች ነው። ያ ከፍተኛ መድረሻ—በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ከፍ ከፍ መደረግ—የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ትኩረት ነው። …
… በ“ሰለስቲያል” ክብር ውስጥ ሶስት ደረጃዎች አሉ፣ ከእነሱም ከፍተኛው በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ከፍ ከፍ መደረግ ነው። …
በዘለአለማዊ እውነት ላይ የተመሰረተው የእግዚአብሔር እቅድ መሰረት ከፍ ከፍ መደረግ የሚቻለው በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ በወንድ እና በሴት መካከል ባለው ዘለአለማዊ ጋብቻ ጊዜ በተገቡ ቃል ኪዳኖች ታማኝ መሆንን በመቀጠል ነው፣ ይህም ጋብቻ በመጨረሻ ታማኞች ሁሉ የሚገኝ ይሆናል። …
የመጨረሻው ፍርድ የመልካም እና የክፋት ተግባራት ድምር፣ ወይም እኛ ያደረግነው፣ ግምገማ ብቻ አይደለም። የሃሳባችን እና የድርጊታችን የመጨረሻው ውጤት፣ ወይም ምን አይነት ሰው እንደሆንን፣ ላይ የተመሰረተ ነው ነው። በየመለወጥ ሂደት ውስጥ ለዘለአለማዊ ህይወት ብቁ እንሆናለን። …
በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው ምክንያት፣ በዚህ ህይወት ውስጥ ስንወድቅ፣ ንስሀ መግባት እና የሰማይ አባታችን ወደሚፈልገው ወደሚያመራው የቃል ኪዳን መንገድ መቀላቀል እንችላለን።
© 2023 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Liahona Message, November 2023 ትርጉም። Language. 19050 506