2023 (እ.አ.አ)
ሙታን በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ
ታህሳስ 2023 (እ.አ.አ)


“ሙታን በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ታህሳስ 2023 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ታህሳስ 2023 (እ.አ.አ)

ሙታን በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ

ዮሃንስ በራዕዩ ስለ መጨረሻው ፍርድ አይቷል።

ኢየሱስ ክርስቶስ

ሊገዛ እና ሊነግሥ ተመልሶ ይመጣል፣ በሜሪ ሳውር

ሙታንም፣ ታናናሾችና ታላላቆች፣ በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ሃይል ሰዎችን ሁሉ ለፍርድ ወደ እግዚአብሔር ፊት ያመጣል (አልማ 11፥42–4433፥2240፥21ሔላማን 14፥15–17ሞርሞን 9፥13–14 ተመልከቱ)።

መጽሐፎቹ ተከፍተው ነበር

እነዚህ መጻሕፍት ሰዎች የቃል ኪዳኑን መንገድ ለመከተል በምድር ላይ ስላደረጉት ነገር በምድር ላይ የተቀመጡ መዝገቦችን ይወክላሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥7 ተመልከቱ)።

የህይወት መፅሐፍ

“በአንድ መንገድ፣ የሕይወት መጽሐፍ የአንድ ግለሠብ አጠቃላይ ሀሳቦች እና ድርጊቶች—የህይወቱ መዝገብ ነው። ነገር ግን፣ ቅዱሳት መጻህፍት ለታማኞች ስማቸው እና የጽድቅ ሥራቸውን የሚገልጹ ዘገባዎችን የያዘ ሰማያዊ መዝገብ እንደተቀመጠ በተጨማሪም ይጠቁማሉ” (የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ “የህይወት መዝገብ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org)።

መዳኘት

የመጨረሻው ፍርድ የሚመጣው ሰዎች ከሞት ከተነሱ በኋላ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የእያንዳንዱ ሰው ዳኛ ይሆናል። ይህ ፍርድ እያንዳንዱ ሰው የሚያገኘውን ዘለአለማዊ ክብር ይወስናል። (የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ “ፍርድ፣ የመጨረሻው፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org፤ አልማ 41፥3–5ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥26–32 ተመልከቱ።)

በስራቸው መሰረት

እያንዳንዱ ሰው በስራው እና በፍላጎቱ መሰረት ይፈረድበታል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137፥9 ተመልከቱ)። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በማክበር አለማክበራቸው እንዲሁም በዚህ ህይወት ውስጥ ከተቀበሉት ከየትኛውም ብርሃን እና እውነት ጋር በሚስማማ መንገድ በመኖር አለመኖራቸው መሰረት ይፈረድባቸዋል።