“ኔፊ ሕፃኑን ኢየሱስን አይቷል፣” ጓደኛ፣ ታህሳስ 2024 (እ.አ.አ) ገጽ 26–27።
ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ታህሳስ 2024 (እ.አ.አ)
ኔፊ ሕፃኑን ኢየሱስን አይቷል።
የኔፊ አባት ሌሂ ኢየሱስ ክርስቶስን በራእይ አየ። ኔፊም ይህንን ራዕይ ማየት ፈልጎ ነበር። ጸለየ እና አባቱ ያየውን ለማየት ጠየቀ።
መንፈስ ቅዱስ ለኔፊ ተመሳሳይ ራዕይን አሳይቶታል። ኔፊ ማርያም የምትባል ወጣት ሴት አየ። የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እንደምትሆን መንፈስ ቅዱስ ተናገረ።
ኔፊ ሕፃኑን ኢየሱስን ከማርያም ጋር አየ። መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ የሰማይ አባትን ልጆች ለመርዳት ወደ ምድር እንደሚመጣ ተናግሯል።
ኔፊ የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት አይቷል። ሰዎችን ሲያገለግልና ሲያስተምር አይቷል። ኔፊ ስለ አዳኙ ብዙ ነገሮችን ተማረ። ቅዱሳት መጻህፍትንም በማንበብ ስለ እርሱ መማር ትችላላችሁ።
© 2024 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, December 2024 ትርጉም። Amharic. 19350 506