መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
6.የካስማ አመራር


“6. የካስማ አመራር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]

“6. የካስማ አመራር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

አንድ መሪ ከቤተሰብ ጋር ሲነጋገር

6.

የካስማ መሪዎች

6.1

የካስማ ዓላማዎች

ኢሳይያስ የኋለኛይቱን ቀን ጽዮን እንደማትነቀል ካስማ ወይም ድንኳን አድርጎ ገልጿታል (ኢሳይያስ 33፥2054፥2ን ይመልከቱ)።

ጌታ ህዝቡን “በአንድ ላይ ለመሰብሰብ“ እና ከዓለም “መጠበቂያ እና …መሸሸጊያ“ ካስማን አቋቁሟል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥6)።

6.2

የካስማ አመራር

የካስማ ፕሬዚዳንቱ በካስማ ውስጥ ያሉትን የቤተክርስቲያኗን ስራ ለመምራት የሚያስችሉ የክህነት ቁልፎችን ይይዛል (3.4.1ን ይመልከቱ)። እርሱ እና አማካሪዎቹ የካስማውን አመራር ይመሰርታሉ። እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች እንዲሆኑ በመርዳት የካስማ አባላትን በፍቅር ይንከባከባሉ።

የካስማ ፕሬዚዳንቱ አራት ዋና ኃላፊነቶች አሉበት፦

  1. በካስማው ውስጥ ከፍተኛ ሊቀ ካህን ነው።

  2. በካስማው ውስጥ የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍከፍ የማድረግ ስራን ይመራል።

  3. እርሱም ዋና ዳኛ ነው።

  4. መዛግብትን፣ የገንዘብን እና ንብረቶቸን በበላይነት ይቆጣጠራል።

6.3

በአውራጃ ፕሬዚዳንቶች ስልጣን እና በካስማ ፕሬዚዳንቶች ስልጣን መካከል ያሉ ልዩነቶች

በእያንዳንዱ አባል አውራጃ፣ አንድ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ የአውራጃ ፕሬዚዳንት በመሆን ይጠራል። የሚከተሉት ልዩነቶች ቢኖሩም እንደካስማ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለግላል፦

  • የሊቀ ካህናት ቡድን ፕሬዚዳንት አይደለም። እንደዚህ ያሉት ቡድኖች የሚደራጁት በካስማዎች ውስጥ ብቻ ነው።

  • በሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ፣ የአውራጃ ፕሬዚዳንቱ አንድን ወንድም ሽማግሌ ሆኖ እንዲሾም ቃለ መጠይቅ ሊያደርግ ይችላል። አንድ የአውራጃ ፕሬዚዳንት ወይም በእርሱ አመራር ስር ያለ አንድ ሰውም (1) አንድን ወንድም ለድጋፍ ሊያቀርበው ይችላል እንዲሁም (2) ሹመቱን ሊሰጥ ይችላል (18.10.1.318.10.3 እና 18.10.4ን ይመልከቱ)። ሆኖም፣ የአውራጃ ፕሬዚዳንት ፓትርያርኮችን፣ ሊቀ ካህናትን ወይም ኤጲስ ቆጶሳትን ሊሾም አይችልም።

  • በሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ፣ የአውራጃ ፕሬዚዳንቱ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቶችን ሊለይ ይችላል (18.11ን ይመልከቱ)።

  • የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያንን አያሰናብትም።

  • የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቅ አያደርግም ወይም በቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ላይ አይፈርምም(26.3.1 ን ይመልከቱ)።

  • ከሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ ካልተሰጠው በስተቀር የአባልነት ምክር ቤትን አይሰበስብም።

6.5

ከፍተኛ ምክር ቤት

የካስማ አመራሩ የካስማውን ከፍተኛ ምክር ቤት ለመመስረት 12 ሊቀ ካህናትን ይጠራል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102፥1124፥131ን ይመልከቱ)።

6.5.1

የካስማ አመራርን መወከል

የካስማ አመራሩ በካስማው ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ አጥቢያ ከፍተኛ አማካሪ ይመድባል።

እንዲሁም የካስማ አመራሩ በካስማ ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ የሽማግሌዎች ቡድን ከፍተኛ አማካሪ ይመድባል።

የሚከተሉትን ሰዎች ስለቤተመቅደስ እና ስለቤተሰብ ታሪክ ስራ እንዲሁም ስለሚስዮናዊ ስራ ኃላፊነታቸውን ያስተምሩ ዘንድ ከፍተኛ አማካሪዎችን ሊመድብ ይችላል፦

  • የሽማግሌዎች ቡድን አመራሮች

  • የአጥቢያ የሚስዮን መሪዎች

  • የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ መሪዎች

6.7

የካስማ ድርጅቶች

የካስማ የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣ የወጣት ሴቶች፣ የመጀመሪያ ክፍል፣ የሰንበት ትምህርት ቤት እና የወጣት ወንዶች ድርጅቶች እያንዳንዳቸው በፕሬዚዳንት ይመራሉ። እነዚህ ፕሬዚዳንቶች በካስማ አመራር ስር ያገለግላሉ።

የእነዚህ መሪዎች ዋና ኃላፊነቶች የካስማ አመራሩን መርዳት እንዲሁም የአጥቢያ ድርጅት አመራሮችን ማስተማር እና መደገፍ ናቸው።

6.7.1

የካስማ የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣ የወጣት ሴቶች፣ የመጀመሪያ ክፍል እና የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች

የእነዚህ አመራሮች አባላት የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉባቸው፦

  • በካስማ ምክር ቤት ያገለግላሉ (ፕሬዚዳንቶች ብቻ)።

  • አዲስ የተጠሩ የአጥቢያ ድርጅት አመራሮችን አቅጣጫ ይሰጧቸዋል።

  • ቀጣይነት ያለው ድገፍ እና ምክር ይሰጣሉ። ፍላጎቶቻቸውን ያውቁ ዘንድ ከአጥቢያ ድርጅት አመራሮች ጋር በመደበኛነት ይገናኛሉ፣ ስለሚያገለግሏቸው አባላት ፍላጎቶች ይወያያሉ እንዲሁም ከካስማ አመራር የሚሰጣቸውን መረጃ ያሳውቃሉ።

  • በካስማ የአመራር ስብሰባዎች የጊዜ አጥቢያ ድርጅት አመራሮችን ያስተምራሉ (29.3.4 ን ይመልከቱ)።

6.7.2

የካስማ የወጣት ወንዶች አመራር

የካስማ የወጣት ወንዶች አመራሮች የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉባቸው፦

  • የኤጲስ ቆጶስ አመራሮች በአሮናዊ ክህነት ተሸካሚ ወንድሞች ላይ በሚኖራቸው ኃላፊነት የድጋፍ ምንጭ በመሆን ያገለግላሉ።

  • በካስማ የወጣቶች አመራር ኮሚቴ ውስጥ ያገለግላል (29.3.10ን ይመልከቱ)።

  • በካስማው አመራር ስር በመሆን የካስማ የአሮናዊ ክህነት አከቲቪቲዎችን እና ካምፖችን ያቅዳል እንዲሁም ያስተባብራል።