መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
16. በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር


“በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ምስል
ጥንዶች እየጸለዩ

16

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር

የደህንነት እና በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ትኩረት የሚያደርገው በመለኮታዊ በተመደቡ አራት ኃላፊነቶች ላይ ነው ( 1.2ን ይመልከቱ)። ከእነዚህ የመጀመሪያው በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር ነው። የሚከተሉትን ስናደርግ ወንጌሉን እየኖርን ነው፦

  • በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን ስንለማመድ።

  • በየቀኑ ንስሃ ስንገባ።

  • የደህንነትን እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግን ሥርዓት በምንቀበልበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ስንገባ።

  • እነዚያን ቃል ኪዳኖች በመጠበቅ እስከ መጨረሻው ስንጸና።

ወንጌልን መኖር የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራን ሌሎች ገጽታዎች ያካትታል።

አትም