“ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡን በጥቅም ላይ ማዋል፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]
“ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡን በጥቅም ላይ ማዋል፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡን በጥቅም ላይ ማዋል
ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ ክፍሎች ከGeneral Handbook: Serving in The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints [አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል] ከሚለው ሙሉ መፅሐፍ ውስጥ የተሰባሰቡ በጣም አስፈላጊ መመሪያዎች ናቸው። ለሚከተሉት ዓይነት መሪዎች የታሰበ ነው፦
-
ሙሉው የመመሪያ መፅሐፍ በሚመርጡት ቋንቋ ገና ማግኘት ለማይችሉ
-
ከተጨመቀው General Handbook [አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ]እትም ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ።
ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው የምዕራፍ፣ የክፍል እና የንዑስ ክፍል የቁጥር አከፋፈል በሙሉው General Handbook [አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ]ውስጥ ካለው የቁጥር አከፋፈል ጋር ይጣጣማል። ይህም በመካከላቸው ከአንዱ ወደሌላው ማጣቀስን እና ማነጻጸርን ቀላል ያደርገዋል።
ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ ውስጥ ያለው የቁጥሮች አከፋፈል አንዳንድ ጊዜ በሙሉው የመመሪያ መፅሐፍ ውስጥ ያሉትን የክፍሎች ወይም የንዑስ ክፍሎች ቁጥሮች ይዘልላል። ይህም የሆነው ይህ የተጨመቀ መመሪያ መፅሐፍ ከሙሉው የመመሪያ መጽሀፍ ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ይዘት ብቻ ስለሚይዝ ነው።
ምንም እንኳን ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ ብዙ መሪዎች ደጋግመው ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ቢሆንም፣ መሪዎች መልስ የማያገኙበት ወይም ሙሉ ለሙሉ መልስ የማይሰጣቸው አንዳንድ ጥያቄዎች ሊኖሯቸው ይችላል። እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች፣ መሪዎች ሊጠቀሙበት በሚችሉት ቋንቋ የተዘጋጀ ከሆነ፣ ከሙሉው የአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ ሊያጣቅሱ ይችላሉ። መሪዎች ከቅርብ የበላይ ባለስልጣን ጋር ሊመክሩም ይችላሉ።
ለልጆቹ በሚደረግ የደህንነት እና በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ዉስጥ ከእርሱ ጋር ስትቀላቀሉት እግዘአብሔር ይባርካችሁ።
ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን