መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
17. ወንጌልን ማስተማር


“17. ወንጌልን ማስተማር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“17. ወንጌልን ማስተማር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

እናት ወንድ ልጇን ስታስተምር

17.

ወንጌልን ማስተማር

ሰዎች በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያጠናክሩ ለመርዳት ወንጌልን እናስተምራለን።

17.1

የክርስቶስ መሰል ማስተማር መርሆዎች

ወላጆች፣ አስተማሪዎች እና መሪዎች ወንጌልን በሚያስተምሩበት ጊዜ ከሁሉ የላቀ አስተማሪ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ ይከተላሉ።

መሪዎች የሚከተሉትን የክርስቶስን መሰል የማስተማር መርሆዎች በድርጅቶቻቸው ላሉ አስተማሪዎች ያጋራሉ። እነዚህ መርሆዎች በTeaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር] ውስጥ በበለጠ ዝርዝር ተብራርተዋል።

3:45

17.1.1

የምታስተምሯቸውን ውደዱ

አዳኙ የሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ የፍቅሩ መገለጫ ናቸው( 2 ኔፊ 26፥24ይመልከቱ)።

3:20

17.1.2

በመንፈስ አስተምሩ

አስተማሪዎች ለማስተማር ሲዘጋጁ እና በሚያስተምሩበት ጊዜ የመንፈስን ምሪት ይሻሉ እንዲሁም በየቀኑ ተጽዕኖው እንዲሰማቸው ብቁ ለመሆን ጥረት ያደርጋሉ።

3:47

17.1.3

ትምህርቱን አስተምሩ

የአዳኙን ምሳሌ በመከተል፣ አስተማሪዎች አስፈላጊ በሆኑት የወንጌል የሚያድኑ እውነቶች ላይ ያተኩራሉ። ቅዱሳት መጻህፍትን፣ የኋለኛው ቀን ነቢያት ቃሎችን እና የተፈቀዱ የቤተክርስቲያኗ የስርዓተ ትምህርት መርጃዎችን በመጠቀም ያስተምራሉ።

3:33

17.1.4

በትጋት መማርን ጋብዙ

አባላት ለራሳቸው ትምህርት ሃላፊነት እንዲወስዱ አስተማሪዎች ያበረታታሉ።

17.2

ቤትን ያማከለ የወንጌል መማር ማስተማር

የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አስተማሪዎች ቤትን ያማከለ የወንጌል መማር ማስተማርን ያበረታታሉ እንዲሁም ይደግፋሉ።

መሪዎች እና አስተማሪዎች፣ ወንጌልን እንዴት እንደሚያጠኑ እና እንደሚያስተምሩ የራሳቸውን መነሳሳት ይፈልጉ ዘንድ አባላትን ያበረታታሉ። ዋነኞቹ የመረጃ ምንጮቻቸው ቅዱሳት መጻህፍት እና የአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶች ናቸው።

3:35

17.3

የመሪዎች ኃላፊነቶች

  • ወንጌሉን በመማር እና በአዳኙ መንገድ በማስተማር ምሳሌ ማስቀመጥ።

  • በድርጅቶቻቸው የሚያስተምሩት ትምህርት እምነትን የሚገነባ እንዲሁም ትምህርቱ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ።

  • በድርጅቶቻቸው ውስጥ ላሉ መምህራን የማያቋርጥ ድጋፍ መስጠት።

17.4

የአስተማሪ ምክር ቤት ስብሰባዎች

በአስተማሪዎች ምክር ቤት ስብሰባዎች፣ አስተማሪዎች ስለክርስቶስ መሰል ማስተማር መርሆዎች በጋራ ይመክራሉ። በተጨማሪም የወንጌል መማር ማስተማርን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻልም ይመክራሉ። Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]ን እንደ ግብዓት ይጠቀማሉ።

የአስተማሪ ምክር ቤት ስብሰባዎች የሚካሄዱት በየሩብ ዓመቱ እሁድ በሚደረጉት የ50 ደቂቃዎቹ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ወቅት ነው።

6:7