መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
19. መዝሙር


“19. “መዝሙር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“19. መዝሙር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ሴት እና ልጅ ፒያኖ እየተጫወቱ

19.

መዝሙር

19.1

የመዝሙር ዓላማ በቤተክርስቲያኗ

የተቀደሰ መዝሙር በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን ያሳድጋል። መንፈስን ይጋብዛል እንዲሁም ትምህርትን ያስተምራል። የአክብሮትን ስሜት ይፈጥራል፣ አባላትን አንድ ያደርጋል እንዲሁም የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን ለማምለክ መንገድን ይፈጥራል።

19.2

መዝሙር በቤት ውስጥ

ግለሰቦች እና ቤተሰቦች በመንፈሳዊ የሚያነሳሱ መዝሙሮችን በዕለት ተዕለት ኑሯቸው እንዲጠቀሙ ጌታ በነቢያቱ በኩል አበረታቷቸዋል።

የቤተክርስቲያኗ መዝሙር ቅጂዎች ከሚከተሉት ምንጮች ይገኛሉ፦

19.3

መዝሙር በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች

19.3.1

ለቤተክርስቲያን ስብሰባዎች መዝሙርን ማቀድ

የአጥቢያ እና የካስማ የመዝሙር አስተባባሪዎች ለአምልኮ መዝሙሮችን ለማቀድ ከክህነት መሪዎች ጋር ይሰራሉ። በስብሰባዎች ላይ የአምልኮ ስሜትን የሚያሳድግ መዝሙርን ይመርጣሉ።

19.3.2

መዝሙር በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ

በቅዱስ ቁርባን ላይ የሚቀርቡት መዝሙሮች ሥብሰባው ሲከፈት እና ሲዘጋ የሚዘመሩ የህበረት መዝሙሮችን እንዲሁም ቅዱስ ቁርባኑ ከመሰጠቱ በፊት የሚዘመሩ መዝሙሮችን ያካትታሉ። የቅዱስ ቁርባን መዝሙሩ ስለቅዱስ ቁርባን ወይም ስለአዳኙ መስዋዕት የሚያወሳ መሆን አለበት።

አባላት ለስብሰባው እየተሰባሰቡ እያሉ የመግቢያ መዝሙር ሙዚቃ ይጫወታል። ከመዝጊያ ጸሎቱ በኋላ አባላት ከስብሰባው እየወጡ ሳሉ በመሳሪያ ብቻ የተቀናበሩ የመዝጊያ መዝሙር ሙዚቃ ይጫወታል።

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ በስብሰባው መካከል የሚዘመር ተጨማሪ የህብረት መዝሙርን ሊያካትትም ይችላል—ለምሳሌ በንግግር መልእክቶች መካከል።

19.3.3

መዝሙር በትምህርት ክፍሎች እና በሌሎች የአጥቢያ ስብሰባዎች

መሪዎች መዝሙሮችን እና ሌሎች የተቀደሱ ሙዚቃዎችን በመጠቀም ትምህርታቸውን እንዲያሳድጉ አስተማሪዎችን ያበረታታሉ።

19.3.6

የሙዚቃ መሳሪያዎች

የሙዚቃ መሳሪያዎች በተለምዶ በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ላይ ለመግቢያነት እና ለመዝጊያነት እንዲሁም ለመዝሙሮች ማጀቢያነት ጥቅም ላይ ይውላሉ። ኦርጋኖች እና ፒያኖዎች ካሉ እና አባላት ሊጫወቷቸው የሚችሉ ከሆነ መደበኛ መሳሪያዎች ናቸው። ኤጲስ ቆጶሳት የህብረት መዝሙሮችን ለማጀብ ሌሎች መሳሪያዎችን መጠቀምን ሊፈቅዱ ይችላሉ።

ፒያኖ፣ ኦርጋን ወይም ሌላ ማጀቢያ መሳሪያ ከሌለ ቅጂዎችን መጠቀም ይቻላል ( 19.2ይመልከቱ)።

19.3.7

መዘምራን

19.3.7.1

የአጥቢያ መዘምራን

በቂ አባላት ባሉበት ቦታ አጥቢያዎች በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ በመደበኛነት የሚዘምሩ መዘምራንን ማደራጀት ይችላሉ።

ከአጥቢያ መዘምራን በተጨማሪ ቤተሰቦች እንዲሁም የሴቶች፣ የወንዶች፣ የወጣቶች፣ ወይም የልጆች ቡድኖች በቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች ላይ እንዲዘምሩ ሊጋበዙ ይችላሉ።

19.4

የመዝሙር አመራር በአጥቢያ

19.4.1

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያው የመዝሙር ኃላፊነት አለበት። ይህንን ሃላፊነቱን ከአማካሪዎቹ ለአንዱ ሊሠጥ ይችላል።

19.4.2

የአጥቢያ የመዝሙር አስተባባሪ

የአጥቢያ የመዝሙር አስተባባሪው በኤጲስ ቆጶስ አመራር ሥር ያገለግላል። እርሱ ወይም እርሷ የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉባቸው፦

  • መዝሙርን በተመለከተ ለኤጲስ ቆጶስ አመራር እና ለሌሎች የአጥቢያ መሪዎች ዓቅም ይሆናል/ትሆናለች።

  • ለቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች የሚሆን መዝሙር ሲታቀድ ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ይሰራል/ትሰራለች ( 19.3.1 እና 19.3.2ይመልከቱ)።

  • በኤጲስ ቆጶስ ሲጠየቅ፣ በአጥቢያ የመዝሙር ጥሪዎች እንዲያገለግሉ አባላትን በጥቆማ ያቀርባል/ታቀርባለች። በእነዚህ ጥሪዎች ውስጥ የሚያገለግሉትን እንደ አስፈላጊነቱ ድጋፍ፣ ትምህርት እና ስልጠና በመስጠት ይረዳል/ትረዳለች።

19.4.3

ተጨማሪ ጥሪዎች

የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ አባላት በሚከተሉት ጥሪዎች እንዲያገለግሉ ሊጠራ ይችላል።

19.4.3.1

የአጥቢያ መዝሙር መሪ

የመዝሙር መሪው ሲጠየቅ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ እና በሌሎች የአጥቢያ ስብሰባዎች ላይ የሚዘመሩ የህብረት መዝሙሮችን ይመራል።

19.4.3.2

የአጥቢያ የመዝሙር አጃቢዎች

በተጠየቀው መሰረት የአጥቢያው የመዝሙር አጃቢ የመግቢያ እና የመዝጊያ መዝሙር እንዲሁም የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ እና የሌሎች የአጥቢያ ስብሰባዎች መዝሙሮችን በመሳሪያ ያጅባል።

19.7

ተጨማሪ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች

19.7.2

ለልምምድ፣ ለግል ስልጠና እና ዝግጅትን ለማቅረብ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን መጠቀም

ምክንያታዊ አማራጭ በማይኖርበት ጊዜ፣ የክህነት መሪዎች የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፒያኖዎችን እና ኦርጋኖችን ለልምምድ፣ ለሚከፈልበት የግል ትምህርት እንዲሁም የስብሰባ አዳራሹን የሚጠቀሙ የክፍሉ አባላትን ለሚያካትቱ ዝግጅቶች መፍቀድ ይችላሉ።