መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
20. አክቲቪቲዎች


“20. አክቲቪቲዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“20. አክቲቪቲዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ወጣት ሴት ውሃ የሚረጭ ሽጉጥ ይዛ

20.

አክቲቪቲዎች

20.1

ዓላማዎች

የቤተክርስቲያን አክቲቪቲዎች የቤተክርስቲያን አባላትን እና ሌሎችን “ከቅዱሳን ጋር ባላገሮች” በማድረግ ያሰባስባሉ(ኤፌሶን 2፥19)። የአክቲቪቲዎች ዓላማዎች የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦

  • በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን መገንባት።

  • ማዝናናት እና አንድነትን ማበረታታት።

  • የግል እድገት ዕድሎችን መፍጠር።

  • ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን ማጠናከር።

  • አባላት በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ውስጥ እንዲሳተፉ መርዳት ( 1.2ይመልከቱ)።

20.2

አክቲቪቲዎችን ማቀድ

መሪዎች አክቲቪቲዎችን ከማቀዳቸው በፊት የአባላትን መንፈሳዊ እና ሥጋዊ ፍላጎቶች ግምት ውስጥ ያስገባሉ። መሪዎች የትኛው አክቲቪቲ እነዚያን ፍላጎቶች ለማሟላት እንደሚረዳ ሲወስኑ የመንፈስን መመሪያ ይሻሉ።

20.2.1

አክቲቪቲዎችን የማቀድ ኃላፊነት

የአጥቢያ አክቲቪቲዎች የአካባቢ ፍላጎቶችን መሰረት በማድረግ ከሚከተሉት በማንኛቸውም መንገዶች ሊታቀዱ ይችላሉ፦

  • የአጥቢያው ምክር ቤት ዕቅዱን በበላይነት ሊመራው ይችላል።

  • የአጥቢያ ምክር ቤቱ አንድ ወይም ከአንድ በላይ አክቲቪቲዎችን ለማቀድ የሚረዱ የተለዩ ድርጅቶችን ሊመድብ ይችላል።

  • አስፈላጊ ሲሆን እና በቂ አባሎች ሲኖሩ የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የአጥቢያ አክቲቪቲዎች ኮሚቴ ሊያዋቅር ይችላል።

ስለወጣቶች አክቲቪቲዎች ዕቅድ መረጃ ለማግኘት፣ 10.2.1.3 እና 11.2.1.3ይመልከቱ።

20.2.2

ሁሉም እንዲሳተፉ መጋበዝ

አክቲቪቲዎችን የሚያቅዱ፣ ሁሉንም በተለይ አዳዲስ አባላትን፣ ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑትን አባላት፣ ወጣቶችን፣ ያላገቡ ጎልማሶችን፣ አካል ጉዳተኞችን እና የሌሎችን ኃይማኖት ተከታዮችን ማካተት አለባቸው፡፡

አክቲቪቲዎች በመሪዎች እና በአባላት ላይ አላስፈላጊ ጫና መፍጠር የለባቸውም።

20.2.3

መስፈርቶች

የቤተክርስቲያን አክቲቪቲዎች የሚያነሳሱ እና “ምግባረ መልካም፣ የሚያስደስ[ቱ] ወይም መልካም የሚነገርላቸው ወይም ምስጋና“ (የእምነት አንቀጾች 1፥13) በማምጣት ላይ የሚያተኩሩ መሆን አለባቸው። አክቲቪቲዎቸ የቤተክርስቲያን ትምህርቶችን የሚቃረኑ ነገሮችን ማካተት የለባቸውም።

20.2.6

ለአክቲቪቲዎች ገንዘብ መመደብ

ብዙዎቹ አክቲቪቲዎች ቀላል እንዲሁም አነስተኛ ወይም ምንም ወጪ የማይጠይቁ መሆን አለባቸው። ማናኛቸውም ወጪዎች በኤጲስ ቆጶስ ወይም ከካስማ አመራሩ መፈቀድ አለባቸው፡፡

አባላት በአክቲቪቲዎች ላይ ለመሳተፍ አብዛኛውን ጊዜ መክፈል አይኖርባቸውም። ለአክቲቪቲዎች ገንዘብ የመመደብ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች 20.6ይመልከቱ።

20.4

የወጣቶች ጉባኤ

በዓመቱ ከጥር ጀምሮ 14 ዓመት የሚሆናቸው ወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች በወጣቶች ጉባኤዎች ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። አብዛኛውን ጊዜ የወጣቶች ጉባኤዎች በአጥቢያ ወይም በካስማ ደረጃ የሚካሄዱት በዓመት አንድ ጊዜ ነው። ብዙ ካስማዎችን አካቶ ወይም በዋና አካባቢ ደረጃ ሊካሄድም ይችላል። ወጣቶች በኤፍኤስዋይ ጉባኤ እንዲካፈሉ በተመደቡበት አመት፣ ካስማዎች እና አጥቢያዎች የወጣቶች ጉባኤዎችን ማድረግ የለባቸውም።

የአጥቢያ የወጣቶች ጉባኤዎች በኤጲስ ቆጶሱ አመራር ስር በአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ይታቀዳል እንዲሁም ይካሄዳል ( 29.2.6ይመልከቱ)። ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያ የወጣቶች ጉባኤ ዕቅዶችን በተመለከተ ከካስማ አመራር ፈቃድ ያገኛል።

መሪዎች እና ወጣቶች አንድን የወጣቶች ጉባኤ በሚያቅዱበት ጊዜ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉትን ፖሊሲዎች እንዲሁም የሚከተሉትን መመሪያዎች ማክበር አለባቸው።

  • የቤተክርስቲያኗ ዓመታዊ የወጣቶች ጭብጥ የጉባኤው ጭብጥ በመሆን ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

  • ከጭብጡ ጋር አብረው የሚሄዱ አክቲቪቲዎችን አቅዱ።

  • ሁሉንም ተናጋሪዎች እና አክቲቪቲዎች በተመለከተ ከኤጲስ ቆጶስ አመራሩ ወይንም ከካስማ አመራሩ ፈቃድ አግኙ።

  • በሁሉም ጊዜ በቂ የጎልማሶች ክትትል መኖሩን አረጋግጡ ( 20.7.1ይመልከቱ)።

20.5

አክቲቪቲዎችን የመምረጥ እና የማቀድ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች

20.5.1

የንግድ ወይም የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች

ለማንኛውም የንግድ ወይም የፖለቲካ ዓላማ አክቲቪቲዎች አይፈቀዱም ( 35.5.2ይመልከቱ)።

20.5.2

ውዝዋዜ እና ሙዚቃ

ሁሉም ውዝዋዜዎች፣ አለባበሶች፣ አጋጌጥ፣ የመብራት አጠቃቀም፣ የውዝዋዜ ስልቶች፣ የዘፈን ግጥሞች እና ሙዚቃዎች የጌታ መንፈስ ሊገኝ የሚችልበትን ሁኔታ ለመፍጠር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ አለባቸው።

20.5.3

የሰኞ ምሽቶች

አባላት ሰኞ ወይም በሌላ ጊዜ የቤተሰብ አክቲቪቲዎችን እንዲያደርጉ ይበረታታሉ። ሰኞ ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ምንም ዓይነት የቤተክርስቲያን አክቲቪቲዎች፣ ስብሰባዎች ወይም የጥምቀት ስርዓቶች መከናወን የለባቸውም።

20.5.5

የአዳር አክቲቪቲዎች

የወጣት ወንዶች እና የወጣት ሴቶች የተዋሃዱ ቡድኖች የቤተክርስቲያን የአዳር አክቲቪቲዎች በኤጲስ ቆጶሱ እና በካስማ ፕሬዚዳንቱ መፈቀድ አለባቸው። ያላገቡ ወንድ እና ሴት አባላት ለሚያደርጓቸው አክቲቪቲዎችም ተመሳሳይ ነው።

በቤተክርስቲያን የመሰብሰቢያ አዳራሾች ወይም በመሰብሰቢያ አዳራሾች ግቢ ውስጥ የአዳር አክቲቪቲዎችን ማድረግ አይፈቀድም።

20.5.8

የሰንበት ቀን አከባበር

እሁድ ዕለት ምንም የቤተክርስቲያን ካምፖችን፣ የስፖርት ዝግጅቶችን ወይም የመዝናኛ ዝግጅቶችን ለማድረግ መርሃግብር አይያዝም። እንዲሁም የወጣት ቡድኖች እና ሌሎች በእሁድ ወደ ካምፖች ወይም ወደ ወጣት ጉባኤዎች መጓዝ ወይም ከዚያ መመለስ የለባቸውም።

20.5.10

የቤተመቅደስ ጉብኝት

የቤተመቅደስ ጉብኝቶች በተመደበው የቤተመቅደስ አውራጃ ውስጥ በአጥቢያ ወይም በካስማ ደረጃ የተደራጁ ናቸው።

20.6

ለአክቲቪቲዎች ገንዘብ የመመደብ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች

20.6.1

በአጥቢያ ወይም በካስማ የበጀት ገንዘብ የሚሸፈኑ አክቲቪቲዎች

20.6.2ሥር ለተጠቀሱት ሊሆኑ ከሚችሉ ልዩ ሁኔታዎች በስተቀር፣ የአጥቢያ ወይም የካስማ የበጀት ገንዘብ የአክቲቪቲዎችን ወጪ ለመሸፈን ጥቅም ላይ መዋል አለበት።

20.6.2

የወጣቶች ካምፕ ወጪን መሸፈን

የአጥቢያው ወይም የካስማው በጀት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አክቲቪቲዎች በቂ ገንዘብ ከሌለው፣ መሪዎች ተሳታፊዎች ክፍያውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲሸፍኑ ሊጠይቋቸው ይችላሉ፦

  • አንድ ትልቅ ዓመታዊ የአሮናዊ ክህነት ካምፕ ወይም ተመሳሳይ አክቲቪቲ።

  • አንድ ትልቅ ዓመታዊ የወጣት ሴቶች ካምፕወይም ተመሳሳይ አክቲቪቲ።

  • ዕድሜያቸው ከ8 እስከ 11 ለሆኑ የመጀመሪየያ ክፍል ልጆች አንድ ዓመታዊ የቀን ካምፕ ወይም ተመሳሳይ አክቲቪቲ።

ለዓመታዊ ካምፕ ወይም ለጉዞዎች የሚደረጉ ወጪዎች ከመጠን በላይ መሆን የለባቸውም። የግለሰብ የገንዘብ እጥረት ማንኛውንም አባል ከመሳተፍ ሊያግደው አይገባም።

20.6.3

የኤፍኤስዋይ ጉባኤዎች ወጪን መሸፈን

ወጣቶች በለወጣቶች ጥንካሬ (ኤፍኤስዋይ) ጉባኤዎች ላይ ለመሳተፍ ገንዘብ እንዲያዋጡ ሊጠየቁ ይችላሉ። ወጪው አንድን ወጣት ከመሳተፍ የሚያግደው ከሆነ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ክፍያውን በሙሉ ወይም በከፊል ለመሸፈን የአጥቢያ በጀት ገንዘብን ሊጠቀም ይችላል 20.6.5 FSY.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ

.።

የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች

ለካስማ እና ለአጥቢያ አክቲቪቲዎች የሚደረጉ ወጪዎች ብዙውን ጊዜ የሚሸፈኑት በበጀት ገንዘብ ነው። ሆኖም አንድ የካስማ ፕሬዚዳንት ወይም ኤጲስ ቆጶስ በእያንዳንዱ ዓመት ለሚከተሉት አአላማዎች ብቻ የሚውል አንድ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል።

  • 20.6.2ሥር ለተዘረዘሩት አክቲቪቲዎች ክፍያ በመሸፈን ድጋፍ ለማድረግ።

  • ክፍሉ ለዓመታዊ ካምፖች የሚያስፈልገውን መሳሪያ በመግዛት ለመርዳት።

20.7

የአክቲቪቲዎች የደህንነት ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች

20.7.1

የጎልማሶች ቁጥጥር

ወጣቶች ወይም ልጆች በሚካፈሉባቸው በሁሉም የቤተክርስቲያን አክቲቪቲዎች ቢያንስ ሁለት አዋቂዎች መገኘት አለባቸው። እንደ ቡድኑ የትልቀነት መጠን፣ ለአክቲቪቲው የሚያስፈልጉ የክህሎት ዓይነቶች ወይም ሌሎች ነገሮች ተጨማሪ ጎልማሶች ያስፈልጉ ይሆናል። ወላጆች እንዲረዱ ተጋብዘዋል።

ከልጆች እና ከወጣቶች የሚሰሩ ሁሉ የልጆች እና የወጣቶች ጥበቃ ስልጠናን ማጠናቀቅ አለባቸው። 20.7.2 ProtectingChildren.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ

.።

በወጣቶች አክቲቪቲዎች ላይ ለመሳተፍ የተቀመጠ የእድሜ መስፈርት

ወጣቶች 12 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ በወላጆች ፈቃድ በአዳር ካምፕ መሳተፍ ይችላሉ። 14 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ በውዝዋዜዎች፣ በወጣቶች ጉባኤዎች፣ እና በኤፍኤስዋይ ጉባኤዎች መሳተፍ ይችላሉ።

20.7.4

የወላጅ ፈቃድ

ልጆች እና ወጣቶች ያለወላጆቻቸው ወይም ያለአሳዳጊዎቻቸው ፈቃድ በቤተክርስቲያኗ አክቲቪቲዎች ላይ መሳተፍ አይችሉም። የአዳር ቆይታን፣ ረጅም ጉዞን ወይም ከተለመዱት የበለጡ ስጋቶችን ለሚያካትቱ የቤተክርስቲያኗ አክቲቪቲዎች የፅሁፍ ፍቃድ አስፈላጊ ነው።

ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች የPermission and Medical Release form [ፈቃድ እና የህክምና ፈቃድ ቅፅን]በመፈረም ይህንን ፈቃዳቸውን ይሰጣሉ።

20.7.5

የጥቃት ሪፖርቶች

በቤተክርስቲያን አክቲቪቲ ወቅት የሚደርስ ማንኛውም ጥቃት ለህግ አካላት ሪፖርት መደረግ አለበት። በአፋጣኝ ኤጲስ ቆጶሱን ማነጋገር ያስፈልጋል። የአባላት መመሪያዎች በ38.6.2.7 ውስጥ ይገኛሉ። የኤጲስ ቆጶሳት መመሪያዎች በ38.6.2.1 ውስጥ ይገኛሉ።

20.7.6

የደህንነት ቅድመ ጥንቃቄዎች፣ ለአደጋ ምላሽ ሰጪነት እና ስለአደጋ ሪፖርት ማድረግ

20.7.6.1

የደህንነት ቅድመ ጥንቃቄዎች

መሪዎች እና ተሳታፊዎች አነስተኛ የጉዳት ወይም የህመም ስጋትን እውን ለማድረግ አክቲቪቲዎችን በጥንቃቄ ይገመግማሉ። አክቲቪቲዎች ሊያስከትሉ የሚችሉት አነስተኛ የንብረት ጉዳት ስጋትንም መሆን አለበት። መሪዎች በአክቲቪቲ ወቅት ደህንነትን ለማረጋገጥ ሁሉንም ጥረት ያደርጋሉ።

20.7.6.2

ለአደጋ ምላሽ ሰጪነት

በቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ወቅት በቤተክርስቲያኗ ንብረት ላይ ድንገተኛ አደጋ ወይም ጉዳት ከደረሰ መሪዎቹ የሚከተሉትን መተግበር የሚችሉትን መመሪያዎች ያከብራሉ፦

  • የመጀመሪያ እርዳታ ስጡ። አንድ ግለሰብ ተጨማሪ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልገው ከሆነ ወደ ድንገተኛ የህክምና አገልግሎቶች ደውሉ። በተጨማሪም ከወላጆች፣ ከአሳዳጊዎች ወይም ከሌሎች የቅርብ ዘመዶች እና ከኤጲስ ቆጶሱ ወይም ከካስማው ፕሬዚዳንት ጋር መገናኘት ያስፈልጋል።

  • አንድ ግለሰብ ከጠፋ ወይም ከሞተ ወዲያውኑ ለአካባቢው የህግ አካላት አሳውቁ።

  • ስሜታዊ ድጋፍ ስጡ።

  • ህጋዊ እርምጃን ከማበረታታትም ካለማበረታታትም ተቆጠቡ። ቤተክርስቲያኗን ወክላችሁ ቃል አትግቡ።

  • የምስክሮችን ስም፣ አድራሻቸውን፣ የተከሰተውን ነገር ዝርዝር መረጃ እና ፎቶግራፎች ሰብስባችሁ አስቀምጡ።

  • ስለአደጋው ሪፖርት አድርጉ (20.7.6.3ን ይመልከቱ)

20.7.6.3

ስለአደጋ ሪፖርት ማቅረብ

የሚከተሉት ሁኔታዎች በበይነመረብ በሚከተለው አድራሻ ሪፖርት መደረግ incidents.ChurchofJesusChrist.orgአለባቸው፦

  • በቤተክርስቲያኗ ንብረት ላይ ወይም በቤተክርስቲያን አክቲቪቲ ወቅት ድንገተኛ አደጋ ወይም ጉዳት ከደረሰ።

  • በቤተክርስቲያኗ አክቲቪቲ እየተሳተፈ የነበረ ግለሰብ ከጠፋ።

  • በግለሰብ፣ በህዝብ ወይም በቤተክርስቲያኗ ንብረት ላይ ጉዳት ከደረሰ።

  • ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መዛት ወይም ሊወሰድ እንደሚችል ሲጠበቅ።

አንድ ክስተት ከባድ ጉዳትን፣ ሞትን ወይም የሰው መጥፋትን ካስከተለ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም እርሱ የወከለው አባል በአፋጣኝ ለዋና አካባቢው ቢሮ ያሳውቃል።

20.7.6.4

ዋስትና እና ጥያቄዎች

በቤተክርስቲያኗ ዝግጅት ላይ ጉዳት ከደረሰ፣ መሪዎች Church Activity Medical Assistance [የቤተክርስቲያኗ የአክቲቪቲ የህክምና እርዳታ] ፕሮግራም ተግባራዊ የሚደረግ ስለመሆኑ ይወስናሉ።

በአንዳንድ ሁኔታዎች የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም ኤጲስ ቆጶሱ ስለደህንነት ጉዳዮች ወይም በቤተክርስቲያኗ ላይ ስለሚነሱ የይገባኛል ጉዳዮች ጥያቄዎች ሊኖሯቸው ይችላል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ (ወይም በእርሱ አመራር ስር ያለ አንድ ኤጲስ ቆጶስ) እንደነዚህ ያሉትን ጥያቄዎች ለ Risk Management Division [ሥጋት አስተዳደር ክፍል] ወይም ለዋና አካባቢው ቢሮ ያመለክታሉ።

20.7.7

ጉዞ

በቤተክርስቲያኗ አክቲቪቲዎች የሚደረግ ጉዞ በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በካስማ ፕሬዚዳንቱ መፈቀድ አለበት። ይህ ጉዞ በአባላት ላይ አስፈላጊ ያልሆነ ጫና መፍጠር የለበትም። ለአክቲቪቲዎች ሲባል ረዥም ርቀት መጓዝ አይበረታታም።

የቤተክርስቲያን ቡድኖች ረዥም ርቀት የሚጓዙ ከሆነ የሚቻል ሲሆን የንግድ መጓጓዣን መጠቀም አለባቸው። ፈቃድ የተሰጠውና በሌሎች ይዞታ ውስጥ በመሆን ለሚደርስ አደጋ የዋስትና ሽፋን ያለው ሊሆን ይገባል።

የቤተክርስቲያን ቡድኖች በግል ተሽከርካሪዎች ከተጓዙ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ደህንነቱ በተጠበቀ የአሰራር ሁኔታ ውስጥ መሆን አለበት። እያንዳንዱ ግለሰብ የመቀመጫ ቀበቶ ማሰር አለበት። እያንዳንዱ ሾፌር መንጃ ፈቃድ ያለው፣ ኃላፊነት የሚሰማው ጎልማሳ መሆን አለበት።