መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
21. አገልግሎት


“21. “አገልግሎት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 [እ.አ.አ)]።

“21. አገልግሎት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ሰዎች ድንጋይ እያነሱ

21.

አገልግሎት

21.0

መግቢያ

አገልግሎት ማለት አዳኙ እንዳደረገው ሌሎችን ማገልገል ማለት ነው( ማቴዎስ 20፥26–28 ን ይመልከቱ)።

ጌታ ሁሉም የእርሱ ቤተክርስቲያን አባላት እንዲህ አይነት እንክብካቤ እንዲያገኙ ይሻል። በዚህ ምክንያት ለእያንዳንዱ አባል ቤተሰብ የክህነት ተሸካሚዎች የሆኑ የአገልግሎት ወንድሞች ተመድበዋል። ለእያንዳንዷ ጎልማሳ እህት የአገልግሎት እህቶች ተመድበዋል።

21.1

የአገልግሎት እህቶች እና ወንድሞች ኃላፊነቶች

የአገልግሎት እህቶች እና ወንድሞች ለተመደቡላቸው ግለሰቦች እና ቤተሰቦች የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉባቸው፦

  • በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያጠነክሩ መርዳት።

  • ሥርዓቶች ሲቀበሉ ከአግዚአብሔር ጋር የተቀደሱ ቃል ኪዳኖችን ለመግባት እና ለመጠበቅ እንዲዘጋጁ መርዳት።

  • ፍላጎቶችን ለይቶ ማወቅ እንዲሁም የክርስቶስ ዓይነት ፍቅርን፣ እንክብካቤን እና አገልግሎትን መስጠት።

  • በመንፈሳዊ እና በስጋዊ ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑ መርዳት።

21.2

አገልግሎትን ማደራጀት

21.2.1

የሥራ ምደባ ማዘጋጀት

የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች የአገልግሎት ወንድሞች እና እህቶች የሥራ ምደባን በጸሎት መንፈስ ያስባሉ። በተለምዶ ሁለት ወንድሞችን ወይም ሁለት እህቶችን ጓደኞች አድርገው ይመድባሉ። የአገልግሎት ጓደኞችን እና የስራ ምደባዎችን በተመለከተ ከኤጲስ ቆጶሱ ፈቃድ ይሻሉ።

ያገቡ ጥንዶች አንድን ግለሰብ ወይም ቤተሰብ አብረው እንዲያገለግሉ ሊመደቡ ይችላሉ።

የአገልግሎት ወንድሞች እና እህቶች ይህ እንደ ጥሪ አይሰጣቸውም፣ ለድጋፍ ድምጽ አይቀርቡም ወይም ለአገልግሎት አይለዩም።

21.2.2

የወጣቶች የአገልግሎት የስራ ምደባ

አንዲት ወጣት ሴት ፈቃደኛ ከሆነች እና የምትችል ከሆነ ለአንድ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህት የአገልግሎት ጓደኛ ሆና ማገልገል ትችላለች። ዕድሜዋ 14 ዓመት በሚሞላት ዓመት ማገልገል ልትጀምር ትችላለች።

2:30

አንድ ወጣት ወንድ በዲያቆን፣ በአስተማሪ ወይም በካህን ክፍል ሲሾም ለአንድ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ የአገልግሎት ጓደኛ በመሆን ያገለግላል።

21.3

የአገልግሎት ቃለ መጠይቅ

2:34

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንቱ እና አማካሪዎቹ የአገልግሎት ወንድሞችን ቃለ መጠይቅ ያደርጋሉ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንቷ የአገልግሎት እህቶችን ቃለ መጠይቅ ታደርጋለች።

እነዚህ ቃለ መጠይቆች ቢያንስ በሩብ ዓመት አንዴ ይደረጋሉ።

ዓላማቸውም እነዚህ ናቸው፦

  • ስለተመደቡ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች ጥንካሬዎች፣ ፍላጎቶች እና ችግሮች መማከር።

  • አስፈላጊ ከሆነ ግለሰቦች ሥርዓቶችን ለመቀበል እንዲዘጋጁ መርዳት የሚቻልባቸውን መንገዶች መወያየት።

  • የሽማግሌዎች ቡድን፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣ የአጥቢያ ምክር ቤት እና ሌሎች እንዴት እርዳታ ለመስጠት እንደሚችሉ ማሰብ።

  • የአገልግሎት ወንድሞችን እና እህቶችን ማስተማር እና ማበረታታት።

21.4

የአገልግሎት ጥረቶችን ማስተባበር

2:49

የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና የሽማግሌዎች ቡድን አመራሮች ቢያንስ በሩብ ዓመት አንዴ ይሰበሰባሉ። በአገልግሎት ቃለ መጠይቅ ወቅት የተማሯቸውን ነገሮች ይገመግማሉ (21.3ን ይመልከቱ)። እንዲሁም የአገልግሎት የስራ ምደባዎችን ያስተባብራሉ።

አነስተኛ ንቁ ተሳታፊ አባላት ባሏቸው ክፍሎች፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና የሽማግሌዎች ቡድን አመራሮች ለአንዳንድ አባላት የአገልግሎት እህቶችን እና የአገልግሎት ወንድሞችን ላለመመደብ ሊወስኑ ይችላሉ።