መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
23. ወንጌልን ማካፈል እንዲሁም አዲስ እና እንደገና የተመለሱ አባላትን ማጠናከር


“23. ወንጌልን ማካፈል እንዲሁም አዲስ እና እንደገና የተመለሱ አባላትን ማጠናከር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ (2023)(እ.አ.አ)።

“23. ወንጌልን ማካፈል እንዲሁም አዲስ እና እንደገና የተመለሱ አባላትን ማጠናከር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ሰዎች ሥልክ እየተመለከቱ

23.

ወንጌልን ማካፈል እንዲሁም አዲስ እና እንደገና የተመለሱ አባላትን ማጠናከር

23.0

መግቢያ

ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ አካል ነው (1.2 በዚህ መመሪያ መፅሐፍ ውስጥ፤ ማቴዎስ 28፥19–20 ን ይመልከቱ)። ይህም የሚከተሉትን ይጨምራል፦

  • በሚስዮናዊ ስራ መሳተፍ እና ሚስዮናዊ በመሆን ማገልገል።

  • አዲስ እና እንደገና የተመለሱ የቤተክርስቲያን አባላት በቃል ኪዳኑ መንገድ እንዲገፉ መርዳት።

23.1

ወንጌልን አካፍሉ

14:36

23.1.1

ፍቅር

ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር የምናሳይበት አንዱ መንገድ ልጆቹን መውደድ እና ማገልገል ነው (ማቴዎስ 22፥36–3925፥40ን ይመልከቱ)። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳደረገው ለመውደድ እና ለማገለልገል እንጥራለን። ይህ ፍቅር ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ ዘሮች እና ባህሎች ጋር እንድንረዳ ያነሳሳናል (ሃዋርያት 10፥342 ኔፊ 26፥33 ን ይመልከቱ)።

23.1.2

አካፍሉ

እግዚአብሔርን እና ልጆቹን ስለምንወድ፣ የሰጠንን በረከቶች ለማካፈል እና እስራኤልን ለመሰብሰብ ለመርዳት መፈለጋችን ተፈጥሯዊ ነው (ዮሐንስ 13፥34–35 ን ይመልከቱ)። እኛ የሚሰማንን ደስታ ሰዎች እንዲሰማቸው ለመርዳት እንፈልጋለን (አልማ 36፥24ን ይመልከቱ)። ስለአዳኙ እና በህይወታችን ስላለው ተፅእኖ በግልፅ እንናገራለን (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥2 ይመልከቱ)። እነዚህን ነገሮች እንደግል፣ የበይነመረብ እና ሌሎች ግንኙነቶች አካል አድርገን በተለመደ እና ተፈጥሯዊ በሆኑ መንገዶች እናጋራለን።

23.1.3

ጋብዙ

ሌሎችን በሚከተሉት እንዴት መጋበዝ እንደምንችል እናውቅ ዘንድ መነሳሳት እና ምሪት ለማግኘት እንጸልያለን፦

  • በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በወንጌሉ እና በቤተክርስቲያኑ አማካኝነት የሚገኙትን በረከቶች ኑ እና (ዮሐንስ 1፥37–39፣ 45–46 ይመልከቱ)።

  • ኑ እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች በማገልገል አግዙን።

  • ኑ እና በዳግም የተመለሰችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አካል ሁኑ።

1:17
1:3
1:39

አብዛኛውን ጊዜ መጋበዝ ማለት በቀላሉ ቤተሰባችንን፣ ጓደኞቻችንን እና ጎረቤቶቻችንን እያደረግን ባለነው ነገር ውስጥ ማካተት ማለት ነው።

23.2

አዲስ አባላትን አጠናክሩ

እያንዳንዱ አዲስ አባል ጓደኛ፣ የማገልገል እድል እና መንፈሳዊ ምግብ ይፈልጋል። እንደ ቤተክርስቲያኗ አባልነታችን፣ ለአዳዲስ አባላት ፍቅራችንን እና ድጋፋችንን እንሰጣቸዋለን (ሞዛያ 18፥8–10 ን ይመልከቱ)። የቤተክርስቲያኗ አካል እንደሆኑ እንዲሰማቸው እንረዳቸዋለን። በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ወደፊት እንዲገፉ እና በጥልቀት “ወደጌታ የተለወጡ“ እንዲሆኑ እንረዳቸዋለን (አልማ 23፥6)።

23.3

እንደገና የተመለሱ አባላትን አጠናክሩ

አንዳንድ አባላት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ መሳተፍን ያቆማሉ። “ለእነዚህ አይነት” አዳኙ እንዲህ ብላል “ለማገልገል መቀጠል አለባችሁ፤ ምክንያቱም አንድ ቀን እንደሚለወጡና ንሰሃ እንደሚገቡ እናም በልባቸው ሙሉ አላማ ወደ እኔ እንደሚመጡ አታውቁምና፣ እናም እፈውሳቸዋለሁ፤ እናንተም ደህንነትን ወደ እነርሱ ለማምጣት መሳሪያ ትሆናላችሁ“(3 ኔፊ 18፥32)።

ሙሉ በሙሉ በመሳተፍ ላይ ያልሆኑ አባላት ከቤተክርስቲያኗ አባላት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ካላቸው የመመለስ ዕድላቸው ሰፊ ነው። እንደ አዳዲስ አባላት ሁሉ፣ እነርሱም ጓደኛ፣ የማገልገል እድል እና መንፈሳዊ ምግብ ያስፈልጋቸዋል።

23.4

የካስማ መሪዎች

23.4.1

የካስማ አመራር

የካስማ ፕሬዚዳንቱ በካስማው ውስጥ ወንጌልን የማካፈል እና እንደገና የተመለሱ አባላትን የማጠናከር ቁልፎች አሉት። እሱ እና አማካሪዎቹ እነዚህን ጥረቶች ለማሳካት አጠቃላይ መመሪያ ይሰጣሉ።

በካስማ እና በአጥቢያ መሪዎች እንዲሁም በሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን መካከል ያለውን ጥረት ለማስተባበር የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ጋር አብዛኛውን ጊዜ በየወሩ ይገናኛል።

23.4.3

ከፍተኛ አማካሪዎች

የካስማ አመራሩ የሽማግሌዎች ቡድን አመራሮችን እና የአጥቢያ የሚስዮን መሪዎችን እንዲያስተምሩ እና እንዲደግፉ ከፍተኛ አማካሪዎችን ሊመድብ ይችላል። አንድ ወይም ከአንድ በላይ ከፍተኛ አማካሪዎች እነዚህን ጥረቶች እንዲመሩ ሊመደቡ ይችላሉ። ሆኖም፣ ሁሉም ከፍተኛ አማካሪዎች ለተመደቡባቸው አጥቢያዎች እና ቡድኖች እነዚህ ሃላፊነቶች አሉባቸው።

23.4.4

የካስማ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር

በካስማ ፕሬዚዳንቱ አመራር፣ የካስማ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ወንጌልን ለማካፈል እና እንደገና የተመለሱ አባላትን ለማጠናከር ስለተሰጣቸው ሀላፊነቶች የአጥቢያ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮችን ያስተምራሉ እንዲሁም ይደግፋሉ።

23.5

የአጥቢያ መሪዎች

23.5.1

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ፣ ወንጌልን የማካፈል እና አዲስ እና እንደገና የተመለሱ አባላትን የማጠናከር የአጥቢያውን ጥረት በሚመሩበት ጊዜ ከሽማግሌዎች ቡድን እና ከሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች ጋር ይቀናጃል። እነዚህ መሪዎች በየወቅቱ በጋራ ይመክራሉ።

ኤጲስ ቆጶሱ እነዚህ ጥረቶች በአጥቢያ ምክር ቤት እና በአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ ውይይት እንደተደረገባቸው እና በቅንጅት እየተሰሩ መሆኑን ያረጋግጣል።

ኤጲስ ቆጶሱ ተገቢ ዕድሜ ላይ የደረሱ አዳዲስ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ በማግኘት የውክልና ጥምቀቶችን እንዲያደርጉ እና ማረጋገጫዎችን እንዲቀበሉ ቃለ መጠይቅ ያደርጋቸዋል 26.4.2 ን ይመልከቱ)። በተጨማሪም ተገቢ ዕድሜ ላይ የደረሱ ወንድሞች የአሮናዊ ክህነት እንዲቀበሉ ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። በተለምዶ እነዚህን ቃለ መጠይቆች የሚያደርገው አባሉ ማረጋገጫ በተቀበለ በአንድ ሳምንት ውስጥ ነው።

23.5.2

የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች

የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች ወንጌልን የማካፈልን እና እንደገና የተመለሱ እና አዲስ አባላትን የማጠናከርን የቀን ተቀን ጥረቶች ይመራሉ (8.2.3ን እና 9.2.3ን ይመልከቱ)።

እነዚህ መሪዎች የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉባቸው፦

  • አባላት የእግዚአብሔርን ልጆች እንዲወዱ፣ ወንጌልን እንዲያካፍሉ እና ሌሎች የአዳኙን በረከቶች ለመቀበል መነሳሳትን እንዲያገኙ መርዳት።

  • ለአዲስ እና እንደገና ለተመለሱ አባላት የአገልግሎት ወንድሞችን እና እህቶችን መመደብ (21.2.1ን ይመልከቱ)።

  • የአጥቢያውን የሚስዮን መሪ ሥራ መምራት።

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት እያንዳንዳቸውእነዚህን ጥረቶች የሚመሩ አንድ አንድ የአመራር አባል ይመድባሉ። እነዚህ ሁለት የአመራር አባላት አብረው ይሰራሉ። በሳምንታዊ ማስተባበሪያ የጋራ ስብሰባዎችን ይሳተፋሉ (23.5.7ን ይመልከቱ)።

23.5.3

የአጥቢያ የሚስዮን መሪ

የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የአጥቢያ የሚስዮን መሪን ስለመጥራት ለመወሰን ከካስማ ፕሬዘዳንቱ ጋር ይመክራል። ይህ ግለሰብ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ መሆን አለበት። ይህ መሪ ካልተጠራ ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባላት አንዱ ይህንን ሥራ ተክቶ ይሠራል።

የአጥቢያ የሚስዮን መሪው የሽማግሌዎች ቡድን አመራርን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራርን በሚስዮናዊ ኃላፊነቶቻቸው ያግዛል። በተጨማሪም የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፦

  • የአጥቢያ አባላትን፣ የመሪዎችን፣ የአጥቢያ ሚስዮናውያንን እና የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያንን ሥራ ያስተባብራል።

  • ሳምንታዊ ማስተባበሪያ ስብሰባዎችንም ይመራል (23.5.7ን ይመልከቱ)።

23.5.4

የአጥቢያ ሚስዮናውያን

የአጥቢያ ሚስዮናውያን በ23.1 ውስጥ እንደተገለጸው የአጥቢያ አባላት ወንጌልን የማካፈል ደስታን እንዲለማመዱ ይረዷቸዋል። በአጥቢያ የሚስዮን መሪው ወይም ይህንን ሥራ በሚሰራው የሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባል አመራር ሥር በመሆን ያገለግላሉ።

23.5.5

የአጥቢያ ምክር ቤት እና የአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት

ወንጌልን ስለማካፈል እንዲሁም አዲስ እና እንደገና የተመለሱ አባላትን ስለማጠናከር በየወቅቱ በአጥቢያ ስብሰባ ላይ ውይይት ሊደረግበት ይገባል። ኤጲስ ቆጶሱ፣ የአጥቢያ የሚስዮን መሪውን በአጥቢያ የምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ እንዲገኝ ሊጋብዝ ይችላል።

እንደሚከተሉት አይነት ቅጾች በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ሊረዷችሁ ይችላሉ፦

በአጥቢያው ስለሚገኙ ወጣቶች ፍላጎት ውይይት ሲደረግ፣ የአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ለአዲስ እና እንደገና ለተመለሱ አባላት እና ሚስዮናውያን ስለሚያስተምሯቸው ወጣቶች ልዩ ትኩረት ይሰጣል።

23.5.7

የማስተባበሪያ የጋራ ስብሰባ

ወንጌልን ለማካፈል እንዲሁም አዲስ እና እንደገና የተመለሱ አባላትን የማጠናከር ጥረቶችን ለማስተባበር አጫጭር መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች በየሳምንቱ ይካሄዳሉ። የአጥቢያ የሚስዮን መሪ የተጠራ ከሆነ፣ እነዚህን ስብሰባዎች ይመራል። አለበለዚያ፣ ይህንን ሥራ ተክቶ የሚሰራው ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባላት አንዱ ይመራል።

ሌሎች የተጋበዙ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የተመደቡ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና የሽማግሌዎች ቡድን አመራሮች።

  • የአጥቢያ ሚስዮናውያን።

  • ከክህነት ቡድን አማካሪዎች አንዱ (ወይም በአጥቢያው ውስጥ ካህናት ከሌሉ የአስተማሪዎች ወይም የዲያቆናት ቡድን ፕሬዚዳንት)።

  • በዕድሜ ታላቅ ከሆኑ ወጣት ሴቶች ክፍል አመራር አባል።

  • የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ሚስዮናውያን።

3:48