“24. ሚስዮናዊን በጥቆማ ማቅረብ እና አገልግሎት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።
“24. ሚስዮናዊን በጥቆማ ማቅረብ እና አገልግሎት፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
24.
ሚስዮናዊን በጥቆማ ማቅረብ እና አገልግሎት
24.0
መግቢያ
በጥንት ጊዜ ጌታ “አህዛብን ሁሉ በአብ፤ በወልድ፤ እናም በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቁ” እስራኤልን የመሰብሰብን ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር (ማቴዎስ 28፥19፤ በተጨማሪም ቁጥር 20ን ይመልከቱ)። ጌታ ያንን ትዕዛዝ በዚህ በኋለኛው ቀን አድሷል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 39፥11፤ 68፥6–8፤ 112፥28–30 ይመልከቱ)።
ሚስዮናዊ በመሆን ጌታን ማገልገል የተቀደሰ ሃላፊነት ነው። ለግለሰቡ እና እርሱ ወይም እርሷ ለምታገለግላቸው ዘለአለማዊ በረከቶችን ያመጣል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥14–16)።
ጌታ እያንዳንዱ ብቁ የሆነ ወጣት ወንድ በሚስዮን ለማገልገል እንዲዘጋጅ እና እንዲያገለግል ይጠይቃል።
እንዲሁም ብቁ የሆኑ፣ ማገልገል የሚችሉ ወጣት ሴቶች በሚስዮን ለማገልገል ከፈለጉ ጌታ ይቀበላቸዋል።
አረጋዊ ሚስዮናውያንም ያስፈልጋሉ እንዲሁም ለማገልገል እንዲዘጋጁ ይበረታታሉ።
24.1
የአገልግሎት ጥሪ
ሚስዮናውያን ጌታን ይወክላሉ ስለዚህ ተገቢ ሥልጣን ባላቸው መጠራት አለባቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥11ን፤ የእምነት አንቀጾች 1፥5ን ይመልከቱ)። በሚስዮን ለማገልገል ጥሪ የሚቀርበው በአጠቃላይ በቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት ነው። ለአረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናውያን ጥሪው በካስማ ፕሬዚዳንቱ በኩል ይቀርባል።
24.2
የሚስዮናውያን ምደባ
እንደሚስዮናዊ የማገልገል ጥሪ የተለየ የሥራ ምደባን ያካትታል። እነዚህ ሥራዎች በስፋት ይለያያሉ።
24.2.1
ወጣት የወንጌል አስተማሪ ሚስዮናውያን
አብዛኞቹ ወጣት ሚስዮናውያን ከአገራቸው ርቀው ወንጌልን እንዲያስተምሩ የሥራ ምደባ ይሰጣቸዋል። እነዚህ የሥራ ምደባዎች የሚሰጡት ሐዋርያት በሚቀበሉት መገለጥ አማካኝነት ነው። እነዚህ ሚስዮናውያን በሚስዮን ፕሬዚዳንት አመራር ስር ያገለግላሉ።
24.2.2
ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናውያን
አንዳንድ ወጣት ሚስዮናውያን በአገራቸው እየኖሩ በቤተክርስቲያን እና በማህበረሰብ ውስጥ እንዲያገለግሉ ይመደባሉ። እነዚህ የሥራ ምደባዎች ለሐዋርያት በመገለጥ ይሰጣሉ እና ከዚያም ሁኔታቸው ለአገልግሎት ሚስዮን በጣም ተስማሚ ለሆኑ እጩዎች ይሰጣሉ (24.3.3ን ይመልከቱ)።
24.2.3
አረጋዊ ሚስዮናውያን
ሁሉም አረጋዊ ሚስዮናውያን የሚያስተምሯቸውን ሰዎች እንዲፈልጉና ለጥምቀት እንዲዘጋጁ እንዲረዷቸው ይበረታታሉ። አረጋዊ ሚስዮናውያን የሚከተሉትን እንዲረዱ ሊመደቡም ይችላሉ፦
-
አባላትን እንዲሁም የዋና አካባቢ እና የቅርብ አካባቢ መሪዎችን።
-
የቤተክርስቲያን መምሪያዎችን እና ፋሲሊቲዎችን።
-
የእርዳታ ድርጅቶች።
አረጋዊ ሚስዮናውያን እኩል ሰዓት እንዲሠሩ፣ ሁሉንም ተመሳሳይ ተግባራት እንዲያከናውኑ ወይም ከወጣት ሚስዮናውያን የሚጠበቁትን እንዲያሟሉ አይጠየቁም።
ለአረጋዊ ሚስዮናውያን የስራ ምደባዎች የሚሰጡት ሐዋርያት በሚቀበሉት መገለጥ አማካኝነት ነው። እጩዎች ለስራ ያላቸውን ምርጫ ሊገልጹ ይችላሉ፣ ነገር ግን ማንኛውንም የስራ ምደባ ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
24.2.4
አረጋውያን የአገልግሎት ሚስዮናውያን
በአገራቸው አጥቢያ ወይም ካስማ ውስጥ ካሉ ጥሪዎች በተጨማሪ፣ አባላት አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናውያን በመሆን ጌታን ማገልገል ይችላሉ። እነዚህ ሚስዮናውያን በቤተክርስቲያን መምሪያዎች፣ ፋሲሊቲዎች እና ሚስዮኖች ጠቃሚ አገልግሎት ይሰጣሉ (24.7.1 ይመልከቱ)። በአገራቸው ይኖራሉ።
አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናውያን የሚጠሩት በካስማ ፕሬዚዳንቱ ነው። በእርሱ አመራር ስር ያገለግላሉ። በእያንዳንዱ ሳምንት የሚያገለግሉበት ሰዓት በአቅማቸው፣ በአካባቢያቸው ባሉት የአገልግሎት እድሎች እና ከዋና አካባቢው አመራር በሚሰጥ መመሪያ ላይ የተመሰረተ ነው።
24.2.5
የሚስዮናውያን ምደባዎች ማጠቃለያ
የሚከተለው ሰንጠረዥ የሚስዮናዊ የሥራ ምደባ አይነቶችን አጠቃልሎ ያሳያል።
ወጣት አስተማሪ ሚስዮናዊ |
ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናዊ |
አረጋዊ ሚስዮናዊ |
አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናዊ | |
---|---|---|---|---|
የሚጠራው | ወጣት አስተማሪ ሚስዮናዊ በቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት | ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናዊ በቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት | አረጋዊ ሚስዮናዊ በቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት | አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናዊ የካስማ ፕሬዚዳንት |
የስራ ምደባውን የሚሰጠው | ወጣት አስተማሪ ሚስዮናዊ በሐዋርያ | ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናዊ በሐዋርያ | አረጋዊ ሚስዮናዊ በሐዋርያ | አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናዊ የካስማ ፕሬዚዳንት |
ለአገልግሎት የሚለየው | ወጣት አስተማሪ ሚስዮናዊ የካስማ ፕሬዚዳንት | ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናዊ የካስማ ፕሬዚዳንት | አረጋዊ ሚስዮናዊ የካስማ ፕሬዚዳንት | አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናዊ የካስማ ፕሬዚዳንት ወይም አማካሪ |
የሚኖረው | ወጣት አስተማሪ ሚስዮናዊ ከአገር ርቆ | ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናዊ በአገር ውስጥ | አረጋዊ ሚስዮናዊ ከአገር ርቆ ወይም በአገር ውስጥ | አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናዊ በአገር ውስጥ |
የቤተክርስቲያን መሪው | ወጣት አስተማሪ ሚስዮናዊ የሚስዮን ፕሬዚዳንት ወይም የታሪካዊ ቦታዎች ፕሬዚዳንት | ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናዊ የካስማ ፕሬዚዳንት | አረጋዊ ሚስዮናዊ የሚስዮን፣ የቤተመቅደስ ወይም የታሪካዊ ቦታዎች ፕሬዚዳንት፤ ወይም የዋና አካባቢ ፕሬዚዳንት | አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናዊ የካስማ ፕሬዚዳንት |
ሪፖርት የሚያደርግለት አካል | ወጣት አስተማሪ ሚስዮናዊ የሚስዮን ፕሬዚዳንት ወይም የታሪካዊ ቦታዎች ፕሬዚዳንት | ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናዊ የአገልግሎት የሚስዮን መሪ | አረጋዊ ሚስዮናዊ የሚስዮን፣ የቤተመቅደስ ወይም የታሪካዊ ቦታዎች ፕሬዚዳንት፤ የዋና አካባቢ ፕሬዚዳንት፤ የጎብኚዎች ማዕከል ዳይሬክተር፤ ወይም የቤተክርስቲያን መምሪያ ወይም የፋሲሊቲዎች አስተዳዳሪ | አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናዊ የአገልግሎት የስራ ምደባ አስተዳዳሪ |
ሊሟላ የሚገባው የዕድሜ መስፈርት | ወጣት አስተማሪ ሚስዮናዊ 18–25 (ለወንዶች) | ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናዊ 18–25 (ለወንዶች) | አረጋዊ ሚስዮናዊ 40 እና ከአርባ በላይ ወይም ያላገባች እህት ከሆነች | አረጋዊ የአገልግሎት ሚስዮናዊ 26 ወይም ከዚያ በላይ |
24.3
በሚስዮን ለማገልገል መዘጋጀት እና ብቁ መሆን
ዕጩ ሚስዮናውያን ለጌታ እና ለልጆቹ ባላቸው ፍቅር ምክንያት በሚስዮን እንዲያገለግሉ ይበረታታሉ። የሚስዮናዊ ጥቆማ ማቅረቢያ የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎች የሚያውቁ መሆን አለባቸው።
24.3.1
ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መለወጥ
ዕጩ ሚስዮናውያን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እና በዳግም ወደተመለሰው ወንጌል የሚያደርጉትን መለወጥ ለማጠናከር ይጥራሉ።
24.3.2
የብቁነትን መስፈርቶች ማሟላት
ዕጩ ሚስዮናውያን የመንፈስ ቅዱስን ወዳጅነት ያገኙ ዘንድ ብቁ ለመሆን ይጥራሉ። ይህ ለውጤታማ የሚስዮናዊ አገልግሎት አስፈላጊ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥13–14 ይመልከቱ)።
24.3.2.1
ንስሀ መግባት
ንስሃ በክርስቶስ ማመንን፣ እውነተኛ ፍላጎት ማሳየትን እና ትዕዛዛትን ማክበርን ይጠይቃል። ኃጢያትን መናዘዝ እና መተውን ያካትታል። ከባድ ኃጢያቶችን ለኤጲስ ቆጶሱ ወይም ለካስማው ፕሬዚዳንት መናዘዝን ይጠይቃል፡፡
ንስሃ የሚገባ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና ፀጋ ይቅርታን ያገኛል እንዲሁም ንፁህ ይሆናል። ጌታ ኃጢያቱን ደግሞ አያስታውሰውም፡፡ (ኢሳይያስ 43፥25፤ ያዕቆብ 6፥5፤ አልማ 34፥15–17፤ ሄለማን 5፥10–11፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42–43። በተጨማሪም በዚህ መመሪያ መፅሐፍ ውስጥ 32.1ን ይመልከቱ።)
የካስማ ፕሬዚዳንቱ ዕጩ ሚስዮናዊውን/ዋን በጥቆማ ከማቅረቡ በፊት ለከባድ ኃጢአቱ/ቷ በፊቱ ንስሃ መግባት አለበት/ባት (32.6፤ በተጨማሪም 24.4.4 ን ይመልከቱ)። የንስሐ ሂደቱ ሰውዬው በፅድቅ አኗኗሩ ለኃጢያት ስርየት የክርስቶስን መንፈስ መቀበሉን ለማሳየት የሚያስፈልግ በቂ ጊዜን ያካትታል።
24.3.3
አካላዊ፣ አዕምሯዊ እና ስሜታዊ ጤና
የሚስዮናዊ ሥራ ፈታኝ ነው። ወጣት የወንጌል አስተማሪ ሚስዮናውያን ቁርጠኛ እንዲሁም በአካል፣ በአእምሮ እና በስሜት ሙሉ የሚስዮናዊ መርሃ ግብርን ለመስራት መቻል አለባቸው።
24.3.4
ገንዘቦች
24.3.4.1
ከአገራቸው ርቀው የሚያገለግሉ ወጣት ሚስዮናውያንን በገንዘብ መደገፍ
የአቅማቸውን ያህል የተዘጋጁ ወጣት ዕጩዎች በገንዘብ ሳቢያ ከማገልገል መዘግየት የለባቸውም። ለማዋጣት ቃል የገቡትን የሚጠበቀውን መዋጮ ለማሟላት፣ የገንዘብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከዘመድ አዝማድ እና ከጓደኞች ሊያገኙ ይችላሉ።
አሁንም የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በአጥቢያ ውስጥ ወይም በካስማ ውስጥ ያሉ አባላትን ለአጥቢያው የሚስዮናዊ ፈንድ እንዲያዋጡ ሊጠይቁ ይችላሉ።
የቤተክርስቲያኗ ክፍል በጀት እና የጾም በኩራት ጥቅም ላይ ሊውሉ አይችሉም።
ለማዋጣት ቃል የሚገባ ወርሃዊ መዋጮ ወጣት የወንጌል አስተማሪ ሚስዮናውያን እና ቤተሰቦቻቸው የሚስዮናዊ ፕሮግራም ወጪዎችን ለመሸፈን በየወሩ የተወሰነ ያዋጣሉ።
መዋጮዎቹ የሚደረጉት ለአጥቢያ የሚስዮናዊ ፈንድ ነው። ኤጲስ ቆጶሳት መዋጮዎቹ በየወሩ መደረጋቸውን ያረጋግጣሉ። በወር ከሚደረገው መጠን በላይ የሆነ ገንዘብ በቅድሚያ መዋጮ መደረግ የለበትም። አንድ ሚስዮናዊ አገልግሎቱን ሳይጨርስ ቀደም ብሎ ወደ ቤት ቢመለስ፣ አስቀድሞ የተዋጣውገንዘብ ሊመለስ አይችልም።
በመስክ የሚደረጉ ወጪዎች በየወሩ፣ ወጣት ሚስዮናውያን የምግብ፣ የመጓጓዣ እና የሌሎች የኑሮ ወጪዎችን ለመሸፈን ከሚስዮኑ ገንዘብ ይቀበላሉ። ይህ ገንዘብ የተቀደሰ ነው። ሚስዮናውያን፣ ከሚስዮን ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ብቻ ይጠቀሙባቸዋል። የግል ወጪን ለመሸፈን ጥቅም ላይ ማዋል፣ በቁጠባ መቀመጥ ወይንም ለቤተሰብ አባላት ወይም ለሌሎች መላክ አይገባቸውም። ሚስዮናውያን ያልተጠቀሙበትን ማንኛውንም ገንዘብ ለሚስዮኑ ይመልሳሉ።
ሚስዮናውያን ሌሎች ወጪዎችን ለመሸፈን የግል ገንዘባቸውን ይጠቀማሉ። እነዚህ የግል ወጪዎች አነስተኛ መሆን አለባቸው። (Missionary Standards for Disciples of Jesus Christ [ለኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የሚስዮናዊ መስፈርት]፣ 4.8ን ይመልከቱ)።
24.3.4.2
ከአገራቸው ርቀው የሚያገለግሉ አረጋዊ ሚስዮናውያንን በገንዘብ መደገፍ
ለማዋጣት ቃል የሚገባ ወርሃዊ መዋጮ ከአገራቸው ርቀው የሚያገለግሉ አረጋዊ ሚስዮናውያን ለሃገራቸው የአጥቢያ ሚስዮናዊ ፈንድ በየወሩ ያዋጣሉ። እነዚህ መዋጮዎች የቤት እና የመኪና ወጪዎችን ለመሸፈን ይረዳሉ።
ኤጲስ ቆጶሳት መዋጮዎቹ በየወሩ መደረጋቸውን ያረጋግጣሉ። በወር ከሚደረገው መጠን በላይ የሆነ ገንዘብ በቅድሚያ መዋጮ መደረግ የለበትም።
ተጨማሪ ወጪዎች የቤትና የመኪና ወጪዎችን ከሚሸፍነው ለማዋጣት ቃል ከሚገባ ወርሃዊ መዋጮ በተጨማሪ አረጋዊ ሚስዮናውያን ምግብን ጨምሮ ሌሎች ወጪዎችን በሙሉ መሸፈን አለባቸው።
24.3.4.3
በአገራቸው የሚያገለግሉ አረጋዊ ሚስዮናውያንን በገንዘብ መደገፍ
በአገራቸው የሚያገለግሉ ሚስዮናውያን ሁሉንም የገንዘብ ፍላጎቶቻቸውን ራሳቸው ማሟላት አለባቸው።
24.3.4.4
የህክምና መድህን ዋስትና እና ወጪዎች
ወጣት አስተማሪ ሚስዮናውያንን ጨምሮ ሁሉም ሚስዮናውያን ከተቻለ ያላቸውን የሕክምና መድህን ዋስትና እንዲኖራቸው በእጅጉ ይበረታታሉ።
በአገራቸው የሚያገለግሉ ሚስዮናውያን የራሳቸውን የህክምና ዋስትና እና ሌላ የዋስትና ሽፋን እንዲኖራቸው ያስፈልጋል። ከአገራቸው ርቀው የሚያገለግሉ አረጋዊ ሚስዮናውያንም የራሳቸውን የዋስትና ሽፋን ማግኘት አለባቸው። ከሀገራቸው ውጪ የሚያገለግሉ አረጋዊ ሚስዮናዊያን በSenior Service Medical Plan [የአረጋዊ አገልግሎት የህክምና እቅድ] በኩል ዋስትናን ሊያገኙ ይችላሉ።
24.3.5
የቤተሰብ አባላት እና መሪዎች ሚስዮናውያንን በማዘጋጀት ውስጥ ያላቸው ሚና
የቤተሰብ አባላት፣ ኤጲስ ቆጶሳት እና ሌሎች መሪዎች ወጣቶች በሚስዮን ለማገልገል እንዲዘጋጁ ይረዷቸዋል።
የቤተሰብ አባላት እና መሪዎች ሁሉም ዕጩ ሚስዮናውያን የሚከተሉትን እንዲያጠኑ ያበረታታሉ፦
-
መፅሐፈ ሞርሞንን እና ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትን።
-
ወንጌሌን ስበኩ።
-
Safeguards for Using Technology [ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ የሚደረግ ጥንቃቄ]።
የቤተሰብ አባላት እና መሪዎች ሁሉም ዕጩ ሚስዮናውያን የሚስዮን መስፈርቶችን ለመከተል ቁርጠኛ እንዲሆኑ ይረዳሉ። ዕጩ ሚስዮናውያን በሚስዮናዊ መስፈርቶች የመመሪያ መፅሐፍ ውስጥ ሊመደቡ ስለሚችሉበት የስራ ምደባ እንዲያጠኑ ይበረታታሉ፦
-
ለወጣት አስተማሪ ሚስዮናውያን፦ Missionary Standards for Disciples of Jesus Christ [ለኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የሚስዮናዊ መስፈርት]
24.4
ሚስዮናውያንን በጥቆማ ማቅረብ
24.4.1
የጤና ምርመራዎች
ሁሉም ዕጩዎች የጤና ዝግጁነታቸውን በህክምና ባለሙያዎች እንዲያስገመግሙ ይጠበቅባቸዋል።
24.4.2
ቃለ መጠይቆች እና በጥቆማ የማቅረቢያ ቅጾች
ኤጲስ ቆጶሱ እና የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከእያንዳንዱ ዕጩ ጋር ጥልቅ፣ መንፈሳዊ ዝግጅነትን የሚወስን እና የሚያንፅ ቃለ መጠይቅ ያደርጋሉ። missionary recommendation interview questions [የሚስዮናዊ ጥቆማ ማቅረቢያ የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎች] ይጠቀማሉ።
በተጨማሪም ኤጲስ ቆጶሱ እና የካስማ ፕሬዚዳንቱ ስለብቁነት እና ስለጤና ዝግጁነት መስፈርቶች በMissionary Online Recommendation System [ሚስዮናዊን በጥቆማ የማቅረብ የይነመረብ ደንብ] ውስጥ ይገመግማሉ። ኤጲስ ቆጶሱ እና የካስማ ፕሬዚዳንቱ ምንም የብቃት መመዘኛዎችን አይጨምሩም። የቃለ መጠይቁን ጥያቄዎችም አይለውጡም።
ኤጲስ ቆጶሱ እና የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ አንድ ዕጩ የብቁነት መስፈርቶችን ስለማሟላቱ ወይም ስለጤናው ዝግጁነት ጥርጣሬ ካላቸው፣ በጋራ እንዲሁም ከግለሰቡ ጋር ይመክራሉ። በወጣት ዕጩው ፈቃድ ከወላጆቹ ወይም ከወላጆቿ ጋርም ሊመክሩ ይችላሉ። ኤጲስ ቆጶሱ እና የካስማ ፕሬዚዳንቱ ግለሰቡ ለፈጸመው ከባድ ኃጢያት ንስሃ እስኪገባ ድረስ በጥቆማ አያቀርቡም (24.3.2.1ን ይመልከቱ)። በግለሰቡ አካላዊ፣ አዕምሯዊ ወይም ስሜታዊ ጤንነት ተመስርተው፣ የአገልግሎት ሚስዮናዊ በመሆን የሚመደብበትን እድል ሊወያዩ ይችላሉ።
ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በሌሉበት አስቸኳይ ጉዳዮች ከገጠሙ ከአማካሪዎቻቸው አንዱ እነዚህን ቃለ መጠይቆች እንዲያደርግ ሊፈቅዱ ይችላሉ።
በአውራጃዎች ውስጥ፣ የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ወይም የተመደበ አማካሪ ዕጩ ሚስዮናውያንን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል እንዲሁም በጥቆማ ያቀርባል። የአውራጃ ፕሬዚዳንቶች እነዚህን ቃለ መጠይቆች አያደርጉም።
24.4.4
የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ ሆነው ማገልገል የማይችሉ
አንዳንድ ጊዜ ለማገልገል የሚፈልግ አባል የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ በመሆን ጥሪ ላይሰጠው ይችላል። ይህም በጤና ችግሮች፣ የብቁነት መስፈርትን ባለማሟላት፣ ከህግ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ወይም በሌሎች ሁኔታዎች ምክንያት ሊሆን ይችላል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ እርሱን ወይም እርሷን በሙሉ ጊዜ የሚስዮናዊ አገልግሎት እንዳይሳተፍ/ትሳተፍ ሊያደርጉት/ጓት ይችላሉ።
24.5
የሚስዮን ጥሪን ከመቀበል በኋላ
አዲስ የተጠሩ ሚስዮናውያን ሚስዮናቸውን ከመጀመራቸው በፊት መፅሐፈ ሞርሞንን እንዲያነቡ ወይም በድጋሚ እንዲያነቡ ይበረታታሉ። “ራሳች[ንን ]፣ ሃሳባች[ን]ንና ድርጊታች[ን]ን [እንድናስተውል]“ የሰጠውን የንጉስ ቢንያምን ምክር ይከተላሉ (ሞዛያ 4፥30)።
24.5.1
የቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ እና የቤተመቅደስ አገልግሎት
አዲስ የተጠሩ ሚስዮናውያን የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ሥርዓትን ያልተቀበሉ ከሆነ፣ የሚቻል ከሆነ የሚስዮናዊ አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት መቀበል አለባቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 43፥15–16፤ 105፥33ን ይመልከቱ)። ያሉበት ሁኔታዎች አመቺ ከሆነ ይህ የአገልግሎት ሚስዮናውያንንም ይጨምራል።
የቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ የተቀበሉ አዲስ የተጠሩ ሚስዮናውያን እንደአግባቡ የሚስዮናዊነት አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት የቤተመቅደስ ሥርዓት ሰራተኞች ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ (25.5 ይመልከቱ)።
24.5.2
የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች
ኤጲስ ቆጶሱ አዲስ የተጠሩ ሚስዮናውያን የሚስዮን አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸው በፊት በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ ይጋብዛቸዋል። ይህ መደበኛ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ነው። ትኩረቱ በቅዱስ ቁርባኑ እና በአዳኙ ላይ መሆን አለበት።
24.5.3
ሚስዮናውያንን ለአገልግሎት መለየት
የአገሩ የካስማ ፕሬዚዳንት እያንዳንዱን ሚስዮናዊ በተቻለ መጠን የሚስዮን መጀመሪያ ቀኑ ሲቃረብ ለአገልግሎት ይለየዋል/ይለያታል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በሌሉበት ጊዜ አስቸኳይ ጉዳዮች ከገጠሙ፣ ከአማካሪዎቻቸው አንዱ ሚስዮናውያንን ለአገልግሎት ይለያል።
የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ወይም ከአማካሪዎቹ አንዱ በእርሱ ሚስዮን ውስጥ ካሉት አውራጃዎች የተጠሩ ሚስዮናውያንን ለአገልግሎት ይለያል። የአውራጃ ፕሬዚዳንቱ ሚስዮናውያንን ለአገልግሎት አይለይም።
ከአገሩ ርቆ የሚያገለግል አንድ ወንድም ለሚስዮናዊ አገልግሎት ከመለየቱ በፊት የመልከ ጼዴቅ ክህነት መቀበል መሆን አለበት። ከአገሩ ርቆ የሚያገለግል አንድ ወንድም ላለበት ሁኔታ ተገቢ ከሆነ ለሚስዮናዊ አገልግሎት ከመለየቱ በፊት የመልከ ጼዴቅ ክህነት መቀበል አለበት።
24.6
ከአገር ርቆ የሚሰጥ አገልግሎት
24.6.2
በተመደበበት የሚስዮን አካባቢ
24.6.2.5
ሌሎችን በገንዘብ ወይም በትምህርት ወይም በስደት ጉዳዮች ለመርዳት የሚቀርቡ ጥያቄዎች
ሚስዮናውያን እና ቤተሰቦቻቸው ሚስዮናውያኑ በሚያገለግሉበት ቦታ ለሚኖሩ የትምህርት ቤት ክፍያ የገንዘብ ድጋፍን ጨምሮ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የለባቸውም። በተጨማሪም ሚስዮናውያን እና ቤተሰቦቻቸው ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ ለሚፈልጉ ሰዎች ስፖንሰር መሆን የለባቸውም (38.8.19 ይመልከቱ)።
24.6.2.8
የአባልነት መዛግብት እና አስራት
የሚስዮናዊው የአገሩ አጥቢያ የአባልነት መዝገቡን ይይዛል። በተጨማሪም የአገሩ/ሯ አጥቢያ የአስራት ክፍያ ሁኔታውን/ዋን ይመዘግባል። ሚስዮናውያን ከሚስዮኑ ከሚያገኙት የድጋፍ ገንዘብ ላይ አሥራት አይከፍሉም። ሆኖም ማንኛውም አይነት የግል ገቢ ካላቸው አስራት ይከፍላሉ።
24.6.3
ከሚስዮን ወደ ትውልድ አገር መመለስ
24.6.3.1
በመጀመሪያ በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ከሚስዮን ወደ ትውልድ አገር መመለስ
ሚስዮናውያን እና የቤተሰባቸው አባላት ለራሳቸው ሲሉ ቀደም ብለው እንዲሰናበቱ ወይም የአገልግሎት ማራዘሚያ እንዲደረግላቸው መጠየቅ የለባቸውም።
ወጣት ሚስዮናውያን ከሚስዮናቸው በቀጥታ ወደ አገራቸው መጓዝ አለባቸው። ማንኛውም ሌላ ጉዞ ሊፈቀድ የሚችለው ሚስዮናዊው ቢያንስ ከአንድ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ጋር ከሆነ ብቻ ነው።
ሚስዮናውያን ለካስማ ፕሬዚዳንታቸው ሪፖርት እስከሚያደርጉ ድረስ አይሰናበቱም። እስከዚያ ጊዜ ድረስ የሚስዮናዊ መስፈርቶችን ይከተላሉ።
24.6.3.2
በመጀመሪያ ከተያዘው መርሃ ግብር አስቀድሞ ከሚስዮን ወደ ትውልድ አገር መመለስ
አንዳንድ ሚስዮናውያን በጤና፣ በብቁነት ወይም በሌሎች ምክንያቶች አስቀድመው ይሰናበታሉ። ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች ለእነዚህ የተመለሱ ሚስዮናውያን ልዩ ድጋፍ ይሰጣሉ። መሪዎች ጤናን ለማግኘት ወይም ከተቻለ ወደ አገልግሎት ለመመለስ እንዲሰሩ ይረዷቸዋል።
24.7
የአገልግሎት ሚስዮኖች
24.7.1
የአገልግሎት ሚስዮናውያን ዕድሎችን መለየት
ኤጲስ ቆጶሱ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ እና የአገልግሎት ሚስዮናውያን በአከባቢው ያሉትን የማገልገል እድሎች ለመለየት በጋራ ይመክራሉ። ወጣት የአገልግሎት ሚስዮናውያንን በተመለከተ የአገልግሎት ሚስዮን መሪ እና የሚስዮናዊው ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በውይይቱ ላይ ይሳተፋሉ።
24.8
ከሚስዮናዊ አገልግሎት በኋላ
24.8.2
የሚስዮናዊ የስንብት ቃለ መጠይቅ
የካስማ ፕሬዚዳንቱ ሚስዮናውያንን ያሰናብታል እንዲሁም የመልቀቂያ ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። በአውራጃዎች ውስጥ፣ የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ወይም የተመደበው አማካሪ ሚስዮናውያንን ያሰናብታል።
የሚከተሉት መመሪያዎች ለቃለ መጠይቁ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
-
የዕድሜ ልክ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆነው እንዲቀጥሉ ማበረታታት።
-
በሚስዮናዊነት ያዳበሯቸውን መልካም ልማዶች እንዲያጎለብቱ መምከር።
-
የወጣት ሚስዮናውያን ትምህርትን እና ሥራን ጨምሮ ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ እና እንዲዘጋጁ አበረታቷቸው።
-
ሁልጊዜ ለቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ብቁ እንዲሆኑ አበረታቷቸው።
24.8.4
ጥሪዎች
መሪዎች በቅርብ ጊዜ ለተሰናበቱ ሚስዮናውያን የአገልግሎት ሥራ ምድቦችን እና ጥሪዎችን ወዲያውኑ ይሰጣሉ። ይህ እንደአግባቡ የቤተመቅደስ ሥርዓት ሰራተኞች ለመሆን ግምት ውስጥ መግባትን ያካትታል (25.5ን ይመልከቱ)።
24.9
ሚስዮናዊን በጥቆማ የማቅረቢያ ግብዓቶች እና አገልግሎት
24.9.2
ድረ ገጾች
-
MissionaryRecommendations.ChurchofJesusChrist.org (ለአካባቢ መሪዎች እና ለዕጩ ለሚስዮናውያን ብቻ)