“25. የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራ በአጥቢያ እና በካስማ፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።
“25. የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራ በአጥቢያ እና በካስማ፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
25.
የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ በአጥቢያ እና በካስማ
25.0
መግቢያ
የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራ ቤተሰብን ለዘለዓለም የማጣመር እና የማተም መንገድ ነው (ማቴዎስ 16፥19ን ይመልከቱ)። ይህ ሥራ የሚከተሉትን ያካትታል፦
-
የራሳችንን የቤተመቅደስ ሥርዓት ስንፈፅም ቃል ኪዳኖችን መግባት (ኢሳይያስ 55፥3ን፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–23 ይመልከቱ)።
-
ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን መግባት ይችሉ ዘንድ በሞት የተለዩንን ቅድመ ዓያቶቻችንን ማግኘት እና በቤተመቅደስ ውስጥ ለእነርሱ ስርዓቶችን መፈጸም (ሚልክያስ 4፥5–6፤ 1 ቆሮንቶስ 15፥29ን፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥15–18 ይመልከቱ)።
-
የሚቻል ሲሆን እግዚአብሔርን ለማምለክ እና ሥርዓቶችን ለልጆቹ ለመፈጸም ዘወትር ወደ ቤተመቅደስ መሄድ (ሉቃስ 24፥52–53፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥13–14 ይመልከቱ)።
ተጨማሪ መረጃዎች በሚከተሉት ይገኛሉ፣ “ቤተመቅደሶች” እና “የቤተሰብ ታሪክ” ( topics.ChurchofJesusChrist.orgየወንጌል አርዕስቶች፣)።
25.1
በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ የአባላትና የመሪዎች ተሳትፎ
የቤተክርስቲያኗ አባላት ቤተሰቦቻቸውን ለዘለአለም በማጣመር የመርዳት እድል እና ሃላፊነት አለባቸው። የቤተመቅደስ ሥርዓትን ሲፈፅሙ ቃል ኪዳኖችን ለመግባት ይዘጋጃሉ እንዲሁም እነዚህን ቃል ኪዳኖች ለመፈጸም ይጥራሉ።
የቤተክርስቲያኗ አባላት የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን ያልተቀበሉ በሞት የተለዩ ዘመዶችን እንያገኙ ይበረታታሉ። ከዚያም አባላት ለእነዚያ ዘመዶች የውክልና ሥርዓቶቹን ይፈፅማሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥18 ይመልከቱ)። በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ፣ የሞቱ ሰዎች ለእነሱ በውክልና የተደረጉላቸውን ሥርዓቶች ለመቀበል ወይም ላለመቀበል መምረጥ ይችላሉ።
25.1.1
በቤተመቅደስ የመሳተፍ የግል ኃላፊነት
አባላት መቼ እና በምን ያህል የጊዜ ድግግሞሽ በቤተመቅደስ ውስጥ እንደሚያመልኩ ራሳቸው ይወስናሉ። መሪዎች ለቤተመቅደስ ተሳትፎ የተቀመጡ ድርሻዎችን ወይም የሪፖርት ማቅረቢያ ስርዓቶችን አያዘጋጁም።
25.2
የቤተመቅደስን እና የቤተሰብ ታሪክ ስራን በአጥቢያ ውስጥ ማደራጀት
25.2.1
የኤጲስ ቆጶስ አመራር
ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያውን የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ጥረቶችን ሲመራ የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮችን ያስተባብራል። እነዚህ መሪዎች በየወቅቱ በጋራ ይመክራሉ።
በተጨማሪም ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያው የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራን የሚመለከቱ የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፦
25.2.2
የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች
የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራን የቀን ተቀን ጥረቶች ይመራሉ (8.2.4ን እና 9.2.4ን ይመልከቱ)። በኤጲስ ቆጶስ አስተባባሪነት እነዚህን ጥረቶች ከአጥቢያው ምክር ቤት ጋር ለመምራት አብረው ይሰራሉ።
እነዚህ መሪዎች የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉባቸው፦
-
አባላት የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን ለመቀበል እንዲዘጋጁ እና የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖቸን እንዲገቡ መርዳት።
-
ሁኔታቸው በፈቀደላቸው ጊዜ ሁሉ አባላት ደጋግመው በቤተመቅደስ እንዲሳተፉ ማበረታታት።
-
አባላት ስለ ቅድመ አያቶቻቸው እንዲያውቁ እና እነርሱን ወክለው የቤተመቅደስ ስርዓቶችን እንዲያከናውኑ ማበረታታት።
-
የአጥቢያውን የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ መሪ ሥራን መምራት። ይህ መሪ ካልተጠራ፣ ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባላት አንዱ ይህንን ሥራ ተክቶ ይሠራል (25.2.3ን ይመልከቱ)።
የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት በአጥቢያው ያለውን የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ በመምራት እንዲረዱ እያንዳንዳቸው ከአመራር አባላቶቻቸው አንድ አንድ ይመድባሉ። እነዚህ ሁለት የአመራር አባላት አብረው ይሰራሉ። ሳምንታዊ የአጥቢያው የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ማስተባበሪያ የጋራ ስብሰባዎችን ይሳተፋሉ (25.2.7ን ይመልከቱ)።
25.2.3
የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ መሪ
የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ መሪን ስለመጥራት ለመወሰን ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ጋር ይመክራል። ይህ ግለሰብ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ መሆን አለበት።
የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራ መሪው የሽማግሌዎች ቡድን አመራርን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራርን በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ሥራ ኃላፊነቶቻቸው ያግዛል። በተጨማሪም የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፦
-
የአጥቢያው የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ማስተባበሪያ የጋራ ስብሰባዎችን መምራት (25.2.7ን ይመልከቱ)።
-
የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ አማካሪዎችን ማሰልጠን። የአባላትን የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራ ለመርዳት ጥረቶቻቸውን ማስተባበር።
-
ወንጌልን የሚማሩትን፣ አዳዲስ አባላትን እና እንደገና የተመለሱ አባላትን በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ ላይ እንዲሳተፉ ለመርዳት ከአጥቢያው የሚስዮን መሪ እና ከሚስዮናውያን ጋር መስራት።
25.2.4
የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ አማካሪዎች
የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ አማካሪዎች በአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ መሪ ወይም ይህንን ሥራ በሚሠራው የሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባል አመራር ስር በመሆን ያገለግላሉ። የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ እነዚህን አባላት እንዲያገለግሉ ይጠራል። ጎልማሶች እና ወጣቶች ሊጠሩ ይችላሉ።
አማካሪዎች የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉባቸው፦
-
አባላት ቅድመ አያቶቻቸውን የማወቅ እና እነርሱን ወክለው የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን የማከናወን በረከቶችን እንዲያገኙ መርዳት።
-
አባላት የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን ለመቀበል እንዲዘጋጁ እና የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖቸን እንዲገቡ መርዳት።
-
በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ማስተባበሪያ የጋራ ስብሰባዎች መሳተፍ (25.2.7ን ይመልከቱ)።
25.2.7
የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ማስተባበሪያ የጋራ ስብሰባ
አጭር መደበኛ ያልሆኑ የአጥቢያ የቤተመቅደስና የቤተሰብ ታሪክ ማስተባበሪያ ስብሰባዎች በየወቅቱ ይካሄዳሉ። የአጥቢያ የቤተመቅደስና የቤተሰብ ታሪክ መሪ የተጠራ ከሆነ እነዚህን ስብሰባዎች ይመራል። አለበለዚያ፣ ይህንን ሥራ ተክቶ የሚሰራው ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባላት አንዱ ይመራል።
ሌሎች የተጋበዙ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
-
የተመደቡ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና የሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባላት።
-
አንድ የክህነት ቡድን ረዳት።
-
በዕድሜ ታላቅ የሆኑ ወጣት ሴቶች ክፍል አመራር አባል።
-
የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ አማካሪዎች።
የእነዚህ ስብሰባዎች ዓላማ፦
-
በሚጠየቅበት ጊዜ የተወሰኑ የአጥቢያ አባላትን በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ እንዴት መርዳት እንደሚቻል ማቀድ።
ይህ ስብሰባ በርቀት ወይም በአካል በመገኘት ሊደረግ ይችላል። የስልክ ጥሪዎችን፣ አጭር የፅሁፍ መልዕክትን እና ኢሜሎችን ጨምሮ ማስተባበሪያ ስብሰባዎች በሌላ መንገዶችም ሊደረጉ ይችላሉ።
25.2.8
የቤተመቅደስ ዝግጅት ትምህርት
በኤጲስ ቆጶሱ በሚሰጥ መመሪያ መሰረት፣ አባላት የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን በመቀበል ቃል ኪዳኖችን እንዲገቡ ለመርዳት የቤተመቅደስ ዝግጅት ትምህርት ሊያደራጅ ይችላል። እነዚህ ትምህርቶች ከመደበኛ የእሁድ ስብሰባዎች ውጭ ለአባላት በሚመች ጊዜ ይሠጣሉ። በስብሰባ አዳራሾች ወይም በመኖሪያ ቤት ሊደረጉ ይችላሉ።
ትምህርቱን ለማደራጀት የሚጠቅሙ ትምህርቶች እና መመሪያዎች በEndowed from on High፥ Temple Preparation Seminar Teacher’s Manual [ከላይ መንፈሳዊ ስጦታን የተቀበለ፦ ለቤተመቅደስ የመዘጋጃ ትምህርታዊ ጉባኤ የአስተማሪው የትምህርት መመሪያ] ውስጥ ይገኛሉ። ተሳታፊዎች የPreparing to Enter the Holy Temple [ወደ ቅዱስ ቤተመቅደስ ለመግባት መዘጋጀት] ቅጂዎች ይሰጧቸዋል። ለግል ጥናት እና የትምህርት መርጃዎች የሚከተለውን ይመልከቱ temples.ChurchofJesusChrist.org.
25.4
የቤተሰብ ታሪክ ግብዓቶች
25.4.1
My Family: Stories That Bring Us Together [ቤተሰቤ፦ አንድ ላይ የሚያሰባስቡን ታሪኮች]
My Family: Stories That Bring Us Together [ቤተሰቤ፦ አንድ ላይ የሚያሰባስቡን ታሪኮች] ሰዎች ዘመዶችን እና ቅድመ አያቶችን እንዲያገኙ እና ታሪኮቻቸውን እንዲያሰባስቡ ይረዳል። ይህች መፅሔት አባላት የቤተሰብ ስሞችን ለቤተመቅደስ ሥርዓቶች ማዘጋጀት እንዲጀምሩ ልትረዳቸው ትችላለች።
ይህችን መፅሔት ከዚህ ማውረድ ይቻላል ChurchofJesusChrist.org. የወረቀት ቅጂዎች ከዚህ ሊታዘዙ ይችላሉ store.ChurchofJesusChrist.org።
25.4.2
FamilySearch.org እና FamilySearch Apps
FamilySearch.org የቤተክርስቲያኗ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራ ድረ ገፅ ነው። ተጠቃሚዎችን በሚከተሉት ሊረዳ ይችላል፦
-
የቤተሰብ ሃረግ ግንኙነቶችን እና ዝምድናዎችን ለመሥራት።
-
ቅድመ ዓያቶችን እና ታሪኮቻቸውን ለማግኘት።
-
የቤተሰብ ታሪኮችን፣ ፎቶግራፎችን እና ታሪኮችን አጋሩ እንዲሁም ጠብቃችሁ አቆዩ።
-
የቤተሰብ ሥሞችን ለቤተመቅደስ ሥርዓቶች ለማዘጋጀት።
የFamilySearch Tree app እና የFamilySearch Memories app ሰዎች በሞባይላቸው በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ሥራ እንዲሳተፉ ያስችላሉ።
25.5
የቤተመቅደስ ሰራተኞችን በጥቆማ ማቅረብ እና መጥራት
25.5.1
የቤተመቅደስ ሰራተኞችን በጥቆማ ማቅረብ
የቤተመቅደስ ሰራተኞች ሊሆኑ የሚችሉት በሚከተሉት መንገዶች ሊለዩ ይችላሉ፦
-
በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በሌላ አጥቢያ መሪ የተለየዩ አባላት
-
ኤጲስ ቆጶሱን ስለማገልገል የጠየቁ
-
በቤተመቅደስ ፕሬዚዳንቱ፣ በሜትረኑ ወይም በሌላ የቤተመቅደስ መሪ በጥቆማ የቀረቡ አባላት
-
ለሚስዮናዊ አገልግሎት እየተዘጋጁ ያሉ ወይም በቅርቡ በሚስዮን አገልግለው የተመለሱ አባላት (ምዕራፍ 24ን ይመልከቱ)።
በቤተመቅደስ ሊያገለግሉ የሚችሉ የቤተመቅደስ ሰራተኞች ስሞች Recommend Temple Worker [በቤተመቅደስ እንዲሰሩ የተጠቆሙ ሰራተኞች] በመጠቀም ይላካል። ይህንን መሳሪያ ኤጲስ ቆጶሳት፣ የካስማ ፕሬዚዳንቶች እና የቤተመቅደስ አመራሮች ሊያገኙት ይችላሉ።