“26. የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 እ.አ.አ)]።
“26. የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
26.
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ
26.0
መግቢያ
ቤተመቅደስ መግባት የተቀደሰ ዕድል ነው። በቤተመቅደስ አቅራቢያ ባይኖሩም ሁሉም አባላት ብቁ እንዲሆኑ እና የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ እንዲኖራቸው የአጥቢያ እና የካስማ መሪዎች ያበረታታሉ።
የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ ወደ ቤተመቅደስ የሚገቡ ሁሉ ይህን ለማድረግ ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የተቻላቸውን ጥረት ያደርጋሉ (መዝሙረ ዳዊት 24፥3–5ን ይመልከቱ)።
ቤተመቅደስ ለመግባት አባላት የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል።
አንድ ኤጲስ ቆጶስ በዚህ ምዕራፍ ያልተመለሱ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን የተመለከቱ ጥያቄዎች ካሉት ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ጋር ይመክራል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ ጥያቄዎቹን በመያዝ የቀዳሚ አመራርን ሊያነጋግር ይችላል።
26.1
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ዓይነቶች
ሶስት የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ዓይነቶች አሉ።
-
የቤተመቅደስ ቡራኬ ላልተቀበሉ አባላት የሚሰጥ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ እነዚህ መታወቂያዎች የሚሰጡት ከወላጆቻቸው ጋር ለሚታተሙ ወይም የውክልና ጥምቀት እና ማረጋገጫዎችን ለመቀበል ለተፈቀደላቸው አባላት ነው። በLeader and Clerk Resources (LCR) በኩል ይሰጣሉ። ለተጨማሪ መረጃ 26.4ን ይመልከቱ።
-
በህይወት ላሉ ለሚደረጉ ሥርዓቶች የሚሰጥ የቤተመቅደስ መግቢያ ፦ እነዚህ መታወቂያዎች የራሳቸውን ቡራኬ ለሚቀበሉ ወይም ከትዳር ጓደኛቸው ጋር ለሚታተሙ አባላት ነው። በህይወት ላሉ ለሚደረጉ ሥርዓቶች የሚሰጠው መታወቂያ ቡራኬ ለተቀበሉ ከሚሰጠው ከመደበኛው የቤተመቅደስ መታወቂያ(ከዚህ በታች ተብራርቷል) ጋር ይያያዛል።
-
የቤተመቅደስ ቡራኬ ለተቀበሉ አባላት የሚሰጥ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ እነዚህ መታወቂያዎች ቀደም ብለው የቤተመቅደስ ቡራኬ ለተቀበሉ አባላት የሚሰጥ ነው። በLCR [ኤልሲአር] በኩል ይሰጣሉ። አንድ አባል ለሞቱ በሚደረጉ በሁሉም የቤተመቅደስ ሥርዓቶች ላይ እንዲሳተፍ ፈቃድ ይሰጣሉ። በተጨማሪም አንድ የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ አባል በህይወት ካሉ ወይም ከሞቱ ወላጆች ወይም ልጆች ጋር ሲታተምም ያገለግላሉ። ለተጨማሪ መረጃ 26.3ን ይመልከቱ።
26.2
ለቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ጥበቃ ማድረግ
26.2.1
የክህነት መሪዎች ለቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ጥበቃ ሲያደርጉ
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ መፅሃፎችን እንዲይዙ ስልጣን የተሰጣቸው የክህነት መሪዎች በጥንቃቄ ጥበቃ ሊያደርጉላቸው ይገባል።
በተጨማሪም የክህነት መሪዎች ያልተፈቀደላቸው ግለሰቦች በLCR[ኤልሲአር] ውስጥ የሚገኘውን የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ መረጃ ማግኘት አለመቻላቸውን ያረጋግጣሉ።
26.2.3
የጠፉ ወይም የተሰረቁ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያዎች
አባላት መታወቂያው ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ፣ በተቻለ ፍጥነት እንዲያሳውቁት ኤጲስ ቆጶሱ ይጠይቃቸዋል። እርሱ፣ የተመደበ አማካሪ ወይም ጸሃፊ በተቻለው ፍጥነት መታወቂያውን ለመጠቀም የማይቻል ለማድረግ LCR[ኤልሲአር] ይጠቀማሉ። ይህን የማድረጊያ ዘዴ ከሌለ መታወቂያው ይሰረዝ ዘንድ ኤጲስ ቆጶሱ የቤተመቅደሱን ቢሮ ያነጋግራል።
26.2.4
የብቁነት መስፈርቶችን የማያሟሉ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያዎች ባለቤቶች
ኤጲስ ቆጶሱ፣ የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ያለው አባል የብቁነት መስፈርቶችን (26.3ን ይመልከቱ) እየኖረ እንዳልሆነ ካረጋገጠ አባሉ መታወቂያውን እንዲመልስ ይጠይቃል። መታወቂያውን ለመጠቀም የማይቻል ለማድረግ LCR [ኤልሲአር] ይጠቀማል። ይህን የማድረጊያ ዘዴ ከሌለ መታወቂያው ይሰረዝ ዘንድ ኤጲስ ቆጶሱ የቤተመቅደሱን ቢሮ ያነጋግራል።
26.3
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ የመስጠት አጠቃላይ መመሪያዎች
የክህነት መሪዎች መታወቂያ መስጠት ያለባቸው አባሉ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ከመለሰ ብቻ ነው።
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቆች በችኮላ የሚደረጉ መሆን የለባቸውም። በሚስጥር የሚደረጉ መሆን አለባቸው። ሆኖም፣ ቃለ መጠይቅ የሚደረግለት ግለሰብ ከፈለገ ሌላ አዋቂ ሰው እንዲገኝ ሊጋብዝ ይችላል።
የክህነት መሪዎች በቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ መፅሐፍ ውስጥ በተዘረዘሩት መስፈርቶች ላይ ምንም መጨመር የለባቸውም። እንዲሁም ማንኛውንም መስፈርቶች ማስወገድ የለባቸውም።
በካስማ ውስጥ፣ የካስማ አመራር አባል ወይም የካስማ ፀሐፊ የቤተመቅደስ መታወቂያው ከተሰጠ በኋላ በLCR [ኤልሲአር] ውስጥ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርገዋል። በአውራጃ ውስጥ፣ ከሚስዮን አመራር አባላት አንዱ ወይም የሚስዮን ጸሃፊ መታወቂያው ፈቃዱ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርገዋል። የውክልና ጥምቀት እና ማረጋገጫ መታወቂያዎች ተቀባይነት ያላቸው የሚሆኑት በአንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ወይም በቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት ሲታተሙ ነው።
26.3.1
የአጥቢያ እና የቅርንጫፍ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቅ
በአጥቢያ ውስጥ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቆችን ያደርጋል እንዲሁም ብቁ ለሆኑ መታወቂያውን ይሰጣል። በቅርንጫፍ ውስጥ፣ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቅ የሚያደርገው እና መታወቂያዎቹን የሚሰጠው የቅርንጫፍ ፕሬዘዳንቱ ብቻ ነው።
በአጥቢያ ውስጥ፣ ኤጲስ ቆጶሱ የሚከተሉትን አባላት ቃለ መጠይቅ ያደርጋል፦
ኤጲስ ቆጶሱ በሌለበት አስቸኳይ ጉዳዮች ከገጠሙ፣ ከአማካሪዎቹ አንዱ እነዚህን ቃለ መጠይቆች እንዲያደርግ ሊፈቅድ ይችላል።
ከላይ በተዘረዘሩት በማናቸውም ሁኔታዎች የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ከመስጠቱ በፊት፣ ኤጲስ ቆጶሱ የቤተክርስቲያን አባልነት የእገዳ ማስታወሻ አለመኖሩን ለማረጋገጥ የአባሉን መዝገብ ይመረምራል። የራሳቸውን የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ለሚቀበሉ ወይም ከትዳር ጓደኛቸው ጋር ለሚታተሙ አባላት የሚከተሉትን ያረጋግጣል፦
-
የአባሉ ጥምቀት እና ማረጋገጫ በአባልነት መዝገብ ላይ መመዝገቡን።
-
ወንድሞች የመልከ ጼዴቅ ክህነትን መቀበላቸውን።
ከኤጲስ ቆጶስ አመራር አባላት በአንዱ ወይም በቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ ቃለ መጠይቁ ከተደረገ በኋላ፣ ከካስማ አመራር አባላት አንዱ በካስማ ውስጥ የሚኖሩ አባላትን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። ከሚስዮን አመራር አባላት አንዱ በአውራጃው ውስጥ ለሚኖሩ አባለት ሁለተኛውን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። ከቀዳሚ አመራር ፈቃድ ካልተሰጠው በስተቀር፣ የአውራጃ ፕሬዚዳንት የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቅ አያደርግም።
26.3.2
ራቅ ባሉ ቦታዎች የሚኖሩ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቅ
አንዳንድ አባላት ከካስማ ወይም ከሚስዮን አመራር አባል ጋር ለመገናኘት ብዙ የጉዞ ወጪ በሚጠይቁ ወይም በጣም አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ይኖራሉ። በእነዚህ ሁኔታዎች አንድ የቤተመቅደስ ፕሬዚዳንት ግለሰቡን ቃለ መጠይቅ ሊያደርገው እና መታወቂያው ላይ ሊፈርም ይችላል። ቃለ መጠይቁን ከማድረጉ በፊት ከካስማ ወይም ከሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ጋር ይወያያል። ኤጲስ ቆጶሱ፣ ፈቃድ የተሰጠው አማካሪ ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ አስቀድመው አባሉን ቃለ መጠይቅ ያደረጉት እና መታወቂያው ላይ የፈረሙለት መሆን አለበት።
26.4
የቤተመቅደስ ቡራኬ ላልተቀበሉ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ መስጠት
26.4.1
አጠቃላይ መመሪያዎች
የቤተመቅደስ ቡራኬ ላልተቀበሉ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ በሚከተለው ሁኔታ ይሰጣል፦
-
ዕድሜያቸው 11 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ፣ ለሞቱ ለመጠመቅ እና ማረጋገጫ ለመቀበል። (ወጣት ሴቶች እና የተሾሙ ወጣት ወንዶች 12 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለማግኘት ይችላሉ)።
-
ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት እስከ 20 ዓመት ለሆኑ፣ ከወላጆቻቸው ጋር ለመታተም። ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት በታች የሆኑ ከወላጆቻቸው ጋር ለመታተም የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ አያስፈልጋቸውም (26.4.4ን ይመልከቱ)።
-
ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት እስከ 20 ዓመት ለሆኑ፣ በህይወት ያሉ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው፣ ከእንጀራ እናት ወይም አባት የተገኙ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው፣ ወይም በግማሽ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው የሆኑ ሲታተሙ ለመመልከት።
ከዚህ ቀደም የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበሉ አባላት በዚህ ክፍል ውስጥ ከተገለጹት መታወቂያዎች ማንኛቸውም ውስጥ አንዳቸውም አይሰጧቸውም።
የክህነት ስልጣንን ለመሸከም እድሜው የደረሰ ወንድ አባል የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ከመቀበሉ በፊት ወደ ክህነት ክፍል መሾም ይኖርበታል።
26.4.2
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን አዲስ ለተጠመቁ አባላት መስጠት
ተገቢ ዕድሜ ላይ የደረሱ አዳዲስ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ በማግኘት የውክልና ጥምቀቶችን ማድረግ እና ማረጋገጫዎችን መቀበል ብቻ እንዲችሉ ኤጲስ ቆጶሱ ቃለ መጠይቅ ያደርጋቸዋል። አባላቱ ማረጋገጫ ከተቀበሉ በኋላ ወዲያውኑ፣ በተለምዶ በሳምንት ውስጥ፣ ይህንን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል (26.4.1ን ይመልከቱ)። ለወንድሞች፣ ይህ ቃለ መጠይቅ የአሮናዊ ክህነትን ለመቀበል የሚደረገው ቃለ መጠይቁ አካል ሊሆን ይችላል።
26.4.3
በውክልና ለመጠመቅ እና ማረጋገጫ ለማግኘት ብቻ የሚሆን የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ
በውክልና ለመጠመቅ እና ማረጋገጫ ለማግኘት የተሰጡ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያዎች ለዚያ ዓላማ ብቻ መዋል ይኖርባቸዋል።
26.4.4
በህይወት ያሉ ልጆችን ከወላጆቻቸው ጋር ለማተም የሚሆን የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ
ዕድሜያቸው 21 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ አባላት ከወላጆቸቻቸው ጋር ሊታተሙ ወይም መታተምን መመልከት የሚችሉት (1) የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበሉ ከሆኑ እና (2) የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ካላቸው ብቻ ነው።
26.5
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያዎችን በልዩ ሁኔታዎች ውስጥ መስጠት
26.5.1
የራሳቸውን የቤተመቅደስ ቡራኬ የሚቀበሉ አባላት
የራሳቸውን የቤተመቅደስ ቡራኬ ለመቀበል የሚፈልጉ ብቁ አባላት የሚከተሉትን ሁኔታዎች ካሟሉ መቀበል ይችላሉ፦
-
ቢያንስ 18 ዓመት ሲሞላቸው።
-
የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ ወይም ተመጣጣኝ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወይም በአሁኑ ሰዓት እየተማሩ ያልሆኑ።
-
ማረጋገጫቸውን ከተቀበሉ አንድ ድፍን ዓመት ያለፋቸው።
-
በመላ ሕይወታቸው የተቀደሱ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን የመቀበል እና የማክበር ፍላጎት የሚሰማቸው።
በተጨማሪም፣ አንድ ሰው የራሱን የቤተመቅደስ ቡራኬ ከመቀበሉ በፊት የመልከ ጼዴቅ ክህነት ሊኖረው ይገባል። የራሳቸውን የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ ለመቀበል ስለሚዘጋጁ አባላት መረጃ ለማግኘት 25.2.8ን ይመልከቱ። የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታን ማን መቀበል እንደሚችል መረጃ ለማግኘት 27.2.1ን ይመልከቱ።
26.5.3
ከአገር ርቆ ከሚሰጥ አገልግሎት የሚመለሱ ወጣት ሚስዮናውያን
የሚሲዮን ፕሬዚዳንቱ፣ ሚስዮናዊው ወደ አገሩ ከሚመለስበት ቀን ጀምሮ በሶስት ወራት አገልግሎቱ እንዲያበቃ አድርጎ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያው ላይ ቀኑን በመሙላት መሥራት እንዲጀምር ያደርገዋል።
በአገልግሎት ማብቂያው የመጨረሻ ሶስት ወር አካባቢ አዲስ የቤተመቅደስ መግቢያ ለመስጠት ኤጲስ ቆጶሱ ተመላሽ ሚስዮናውያንን ቃለ መጠይቅ ያደርጋቸዋል።
26.5.4
ራሳቸውን በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገልጹ ግለሰቦች
ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበ አማካሪ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ቃለ መጠይቅ ከማድረጉ በፊት ከቀድሞው ኤጲስ ቆጰስ ጋር ግንኙነት ያደርጋል።
26.5.7
ራሳቸውን በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገለጹ ግለሰቦች
የካስማ ፕሬዚዳንቱ እያንዳንዱን ሁኔታዎች በጥንቃቄ እና በክርስቶስ መሰል ፍቅር ለማየት ከዋና አካባቢው አመራር ጋር መምከር አለበት (38.6.23ን ይመልከቱ)።
26.5.8
ከባድ ኃጢያት የፈጸሙ አባላት
ከባድ ኃጢያት የፈጸመ/ች አባል ንስሃ እስኪገባ/ክትገባ ድረስ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ አያገኝም/አታገኝም (32.6ን ይመልከቱ)።
26.5.9
ከቤተክርስቲያን ከመወገድ ወይም በገዛ ፈቃድ ከቤተክርስቲያን ከመውጣት በኋላ ወደ ቤተክርስቲያኗ በድጋሚ የተቀላቀሉ አባላት
26.5.9.1
ከዚህ በፊት የቤተመቅደስ የመንፈስ ሥጦታ ያልተቀበሉ አባላት
እነዚህ አባላት በጥምቀት እና ማረጋገጫ እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ከተመለሱበት ቀን ጀምሮ እስከ አንድ ሙሉ አመት ድረስ የራሳቸውን የቤተመቅደስ ስጦታ መቀበል እንዲችሉ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያዎች ሊሰጣቸው አይችልም።
26.5.9.2
ከዚህ በፊት የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበሉ አባላት
ከዚህ በፊት የቤተመቅደስ ቡራኬ ተቀብለው የነበሩ አባላት የበፊቱ የቤተመቅደስ በረከቶቻቸው በበረከቶች ዳግም መመለስ ስርዓት በኩል እስኪመለሱ ድረስ ማንኛውንም የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ለመቀበል አይችሉም