መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
30. የቤተክርስቲያን ጥሪዎች


“30. የቤተክርስቲያን ጥሪዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“30. የቤተክርስቲያን ጥሪዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ሰዎች ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ አንስተው

30.

የቤተክርስቲያን ጥሪዎች

30.0

መግቢያ

አባላት ለእግዚአብሔር ልጆች አገልግሎት በመስጠት እግዚአብሔርን በማገልገል የሚገኘው ደስታ እንዲሰማቸው ጥሪዎች እድሎችን ይሰጧቸዋል (ሞዛያ 2፥17ን ይመልከቱ)። ጥሪዎች አባላት እምነታቸውን እንዲያሳድጉ እንዲሁም ወደ ጌታ እንዲቀርቡ ይረዳሉ።

በቤተክርስቲያን ውስጥ ማንኛውንም ጥሪ መፈለግ ተገቢ አይደለም (ማርቆስ 10፥42–45ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥34-37ን ይመልከቱ)። እንዲሁም የቤተክርስቲያኗ አባላት ከአንዱ ጥሪ ወደ ሌላው “አያድጉም”። በተሰጠ ጥሪ በታማኝነት ማገልገል ከጥሪው ምንነት የበለጠ አስፈላጊ ነው። ጌታ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የሚያገለግሉ ሁሉ የሚያሳዩትን ቁርጠኝነት ያከብራል።

30.1

ማን እንደሚጠራ መወሰን

30.1.1

አጠቃላይ መመሪያዎች

በቤተክርስቲያን የሚያገለግሉ በእግዚአብሔር የተጠሩ ናቸው (ዕብራውያን 5፥4ን፤ የእምነት አንቀጾች 1፥5ን ይመልከቱ)። መሪዎች ማንን መጥራት እንዳለባቸው ለመወሰን የመንፈስን መመሪያ ይሻሉ (በተጨማሪም 4.2.6ን ይመልከቱ)። በተጨማሪም የሚከተሉትን ግምት ውስጥ ያስገባሉ፦

  • የአባሉን ብቁነት (በቃለ መጠይቅ እንደተወሰነው)።

  • አባሉ ሌሎችን ለመባረክ ያሉት ወይም ሊያዳብራቸው የሚችላቸው ስጦታዎች እና ችሎታዎች።

  • ጤንነቱን እና ስራውን ጨምሮ የአባሉን የግል ሁኔታ።

  • ጥሪው በአባሉ ትዳር እና ቤተሰብ ላይ ሊያሳድረው የሚችለው ተፅእኖ።

አባላት በቤተክርስቲያኗ በማገልገል ለሚከፍሉት መስዋዕትነት ይባረካሉ። ሆኖም አንድ ጥሪ በአባላት እና በቤተሰቦቻቸው ላይ አላስፈላጊ ጫና መፍጠር የለበትም። እንዲሁም ጥሪው አባላት የሥራ ኃላፊነቶቻቸውን መወጣትን አስቸጋሪ ሊያደርግባቸው አይገባም።

በአጠቃላይ እያንዳንዱ አባል አገልጋይ ወንድም ወይም እህት በመሆን ከማገልገል በተጨማሪ ጥሪ የሚሠጠው በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ጥሪ ብቻ እንዲያገለግል ነው።

መሪዎቹ ትዳር ለመሰረተ/ች አባል ጥሪን ሲያሳውቁ የትዳር ጓደኛው/ዋ ስለጥሪው እንደሚያውቅ/ቁ እና እንደሚደግፍ/ምትደግፍ ያረጋግጣሉ። መሪዎች ለአንድ ወጣት ወንድ ወይም ለአንዲት ወጣት ሴት ጥሪን ከማሳወቃቸው በፊት ከወላጆቹ/ቿ ወይም ከአሳዳጊዎቹ/ቿ ፈቃድ ያገኛሉ።

ኤጲስ ቆጶሱ ጥሪውን ከማድረጉ በፊት የግለሰቡ የአባልነት መዝገብ ማብራሪያ ወይም መደበኛ የአባልነት እገዳዎች የሌለው መሆኑን ለማረጋገጥ በጥንቃቄ ይመረምረዋል።

30.1.2

ለአዲስ አባላት የሚሰጡ ጥሪዎች

የማገልገል እድሎች አባላት በመንፈሳዊ እንዲያድጉ ይረዳሉ።

የአጥቢያ መሪዎች፣ አዲስ አባላት ከተጠመቁ እና ማረጋገጫ ከተቀበሉ በኋላ ወዲያውኑ እንዲያገለግሉ እድሎችን ይሰጧቸዋል።

30.1.3

አባላት ላልሆኑ የሚሰጡ ጥሪዎች

የቤተክርስቲያኗ አባል ያልሆኑ ሰዎች እንደ ኦርጋን ተጫዋች፣ የመዝሙር መሪዎች፣ ወይም አክቲቪቲዎችን በማቀድ እንደ መርዳት ባሉ አንዳንድ የስራ መደቦች ላይ ጥሪ ሊሰጣቸው ይችላል። ሆኖም እንደ አስተማሪዎች፣ እንደ ቡድን ወይም ድርጅት አመራር አባላት ወይም እንደ የመጀመሪያ ክፍል የመዝሙር መሪዎች በመሆን መጠራት የለባቸውም።

30.1.4

ሚስጥራዊነት

ጥሪዎች እና ስንብቶች የተቀደሱ ናቸው። በዚህ ምክንያት መሪዎች ስለታቀዱ ጥሪዎች እና ስንብቶች ያላቸውን መረጃ በሚስጥር ይይዛሉ።

30.1.5

ጥሪዎችን በጥቆማ ማቅረብ እና ፈቃዶች

የጥሪዎች ቻርት ለእያንዳንዱ ጥሪ ማን በጥቆማ እንደሚያቀርብ እና ማን ፈቃድ እንደሚሠጥ ያመለክታል ( 30.8ን ይመልከቱ)።

ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች እያንዳንዱ የቀረበ ጥቆማ በጸሎት መንፈስ የቀረበ መሆኑን በመገንዘብ በጥንቃቄ ግምት ውስጥ ያስገቡታል። የኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ አመራር ማንን መጥራት እንዳለባቸው ለማወቅ መነሳሳትን የመቀበል የመጨረሻ ሃላፊነት አለባቸው።

30.2

ጥሪን መስጠት

ለማገልገል ጥሪን መቀበል ለአንድ አባል ትርጉም ያለው መንፈሳዊ ተሞክሮ መሆን አለበት።

አንድ መሪ አንድን ጥሪ ሲያሳውቅ ከጌታ የመጣ እንደሆነ ያስረዳል።

እንዲሁም መሪው፦

  • የጥሪውን ዓላማ፣ አስፈላጊነት እና ኃላፊነቶች ያብራራል።

  • አንድ አባል ጥሪውን ያከናውን ዘንድ የጌታን መንፈስ እንዲፈልግ ያበረታታል።

  • አባሉን/ሏን ጌታ እንደሚረዳው/ት እና በታማኝነት ሲያገለግለው/ስታለግለው እንደሚባርከው/ካት ምስክርነቱን ይሰጣል።

  • ጥሪውን የተመለከተ ስልጠና እና ድጋፍ ማን እንደሚሰጠው ለአባሉ ይነግራል።

  • እሱ ወይም እሷ ሊሳተፉባቸው ስለሚገባቸው ስብሰባዎች እና ስላሉት ማናቸውም ግብዓቶች ለአባሉ/ሏ ያሳውቃል።

30.3

ለአባላት ጥሪዎች ድጋፍ መስጠት

በአብዛኞቹ የቤተክርስቲያን የስራ መደቦች የሚጠሩ፣ ማገልገል ከመጀመራቸው በፊት ድጋፍ ለማግኘት መቅረብ አለባቸው ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥1342፥11ን ይመልከቱ)።

የድጋፍ አሰጣጡን የሚያካሂደው ግለሰብ በመጀመሪያ ከስራ መደቡ ማን እንደተሰናበተ ያስታውቃል (የሚመለከተው ከሆነ)። አባላት ግለሰቡ ለሰጠው አገልግሎት ምስጋና እንዲያቀርቡ ይጋብዛል (30.6ን ይመልከቱ)።

ስልጣን ያለው የክህነት አመራር አንድን ሰው ለድጋፍ ሲያቀርበው/ባት እንዲቆም/እንድትቆም ይጋብዘዋል/ዛታል። ከዚያም መሪው እንደሚከተሉት ያሉትን ቃላት ይጠቀማል፦

“[ሥም] እንደ [የሥራ መደብ] ሆኖ ተጠርቷል/ታለች። [እርሷን ወይም እርሱን] የሚደግፉ እጃቸውን በማውጣት ማሳየት ይችላሉ። [ለአፍታ ማቆም።] የሚቃወሙ ካሉ በተመሳሳይ ማሳየት ይችላሉ። [ለአፍታ ማቆም።]”

በጥሩ አቋም ላይ ያለ አባል ጥሪውን ከተቃወመ/ች፣ የበላይ መሪው ወይም ሌላ የተመደበ የክህነት መሪ ከስብሰባው በኋላ በግል ከእሱ ወይም ከእርሷጋር ይገናኛል።

30.4

አባላትን በጥሪዎች እንዲያገለግሉ መለየት

ለተጨማሪ መረጃ 18.11 ይመልከቱ።

30.6

አባላትን ከጥሪዎች ማሰናበት

አንድ ፕሬዚዳንት ወይም ኤጲስ ቆጶስ ሲሰናበት አማካሪዎቹም ወዲያውኑ ይሰናበታሉ።

ሥንብትን ማሳወቅ አንድ መሪ ምስጋናውን ለመግለፅ እና በአባሉ አገልግሎት ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ እንደነበረ እውቅና ለመስጠት ጠቃሚ አጋጣሚ ነው። የአባሉ መሰናበት በይፋ ከመገለጹ በፊት እሱን ወይም እሷን ለማሳወቅ መሪው ከአባሉ/ሏ ጋር በግል ይገናኛል። ስለሥንብቱ ከመነገሩ በፊት ማወቅ ለሚያስፈልጋቸው ብቻ ይነገራቸዋል።

ስልጣን ያለው የክህነት መሪ ግለሰቡ ድጋፍ በተሰጠው ቦታ ሥንብቱን ያስታውቃል። መሪው እንደሚከተሉት ያሉትን ቃላት ሊጠቀም ይችላል፦

“[ሥም] ከ[የሥራ መደብ] ተሰናብቷል/ታለች። [እርሱ ወይም እርሷ] ለሰጠው/ችው አገልግሎት ምስጋና ማቅረብ የሚፈልጉ እጃቸውን በማውጣት ማሳየት ይችላሉ።

መሪው የሚቃወም ሰው እንዳለ አይጠይቅም።

30.8

የጥሪዎች ቻርት

30.8.1

የአጥቢያ ጥሪዎች

ጥሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የተፈቀደው በ

ድጋፍ የተሰጠው በ

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ጥሪዎች

ኤጲስ ቆጶስ

በጥቆማ የቀረበው በ

የካስማ ፕሬዚዳንት LCR [ኤልሲአር]በመጠቀም

የተፈቀደው በ

ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ከቀዳሚ አመራር ፈቃድ በማግኘት በካስማ ፕሬዚዳንት

ጥሪዎች

የኤጲስ ቆጶስ አመራር አማካሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

ኤጲስ ቆጶስ

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ ፕሬዚዳንት ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

የአጥቢያ ጸሃፊዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ ፕሬዚዳንት ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ ወይም ከፍተኛ አማካሪ

ጥሪዎች

የአጥቢያ ዋና ጸሃፊ

በጥቆማ የቀረበው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ ፕሬዚዳንት ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ ወይም ከፍተኛ አማካሪ

ጥሪዎች

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት

በጥቆማ የቀረበው በ

የካስማ አመራር (ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር በመመካከር)

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ ፕሬዚዳንት

ጥሪዎች

የሽማግሌዎች ቡድን አመራር አማካሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት (ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር በመመካከር)

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ ፕሬዚዳንት ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ ወይም ከፍተኛ አማካሪ

ጥሪዎች

ሌሎች የሽማግሌዎች ቡድን ጥሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የሽማግሌዎች ቡድን አመራር

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የሽማግሌዎች ቡድን አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

የአጥቢያ ድርጅቶች ፕሬዚዳንቶች

በጥቆማ የቀረበው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ

ጥሪዎች

የአጥቢያ ድርጅት አመራሮች አማካሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የድርጅት ፕሬዚዳንት

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

ሌሎች የሴቶች መረዳጃ ማህበር ጥሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

ሌሎች የአጥቢያ የወጣት ሴቶች፣ የመጀመሪያ ክፍል እና የሰንበት ትምህርት ቤት ጥሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የድርጅት አመራር

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

የአጥቢያ የሚስዮን መሪ (ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባላት አንዱ ይህንን ሥራ ተክቶ ሊሠራ ይችላል፤ እንደዚያ ከሆነ ተለይቶ መጠራት፣ ድጋፍ ማግኛት ወይም ለአገልግሎት መለየት አያስፈልገውም)

በጥቆማ የቀረበው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር (ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር እና ከሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ጋር በመመካከር)።

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

የአጥቢያ ሚስዮናውያን

በጥቆማ የቀረበው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር ወይም የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንቶች

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ መሪ (ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባላት አንዱ ይህንን ሥራ ተክቶ ሊሠራ ይችላል፤ እንደዚያ ከሆነ ተለይቶ መጠራት፣ ድጋፍ ማግኛት ወይም ለአገልግሎት መለየት አያስፈልገውም)።

በጥቆማ የቀረበው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር (ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር እና ከሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ጋር በመመካከር)።

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

የክህነት ቡድን ፕሬዚዳንት ረዳቶች

በጥቆማ የቀረበው በ

ኤጲስ ቆጶስ (እንደ ክህነት ቡድን ፕሬዚዳንት)

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የሽማግሌዎች ቡድን አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ

ጥሪዎች

የአስተማሪዎች እና የዲያቆናት ቡድን ፕሬዚዳንቶች

በጥቆማ የቀረበው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የሽማግሌዎች ቡድን አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በተመደበ አማካሪ ይጠራል፤ በኤጲስ ቆጶሱ ለአገልግሎት ይለያል

ጥሪዎች

የአስተማሪዎች እና የዲያቆናት ቡድን አመራሮች አማካሪዎች እና የሽማግሌዎች ቡድን ጸኃፊዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የሽማግሌዎች ቡድን አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

የወጣት ሴቶች ክፍል ፕሬዚዳንት

በጥቆማ የቀረበው በ

ኤጲስ ቆጶስ (ከወጣት ሴቶች አመራር ጋር በመመካር)።

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የትምህርት ክፍል አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

የወጣት ሴቶች የትምህርት ክፍል አመራሮች አማካሪዎች እና የትምህርት ክፍል ጸሃፊዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የትምህርት ክፍል ፕሬዚዳንት

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የትምህርት ክፍል አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

ሌሎች የአጥቢያ ጥሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

የተፈቀደው በ

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የአጥቢያ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ኤጲስ ቆጶስ ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

  1. ንቁ የቤተመቅደስ አታሚዎች በኤጲስ ቆጶስ አመራር ውስጥ ለማገልገል መጠራት የለባቸውም። አታሚዎች በቤተክርሰቲያኗ ፕሬዚዳንት አመራር ይጠራሉ።

30.8.2

የቅርንጫፍ ጥሪዎች

ጥሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የተፈቀደው በ

ድጋፍ የተሰጠው በ

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

ጥሪዎች

በቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት

በጥቆማ የቀረበው በ

የካስማ፣ የሚስዮን ወይም የአውራጃ አመራር

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት ወይም የሚስዮን አመራር

ድጋፍ የተሰጠው በ

የቅርንጫፍ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ ወይም የሚስዮን ፕሬዚዳንት (ወይም ከተመደበ የአውራጃ ፕሬዚዳንቱ)

ጥሪዎች

የቅርንጫፍ አመራር አማካሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት ወይም የሚስዮን አመራር (ወይም በሚስዮን ፕሬዚዳንቱ፣ በአውራጃ አመራር ሲፈቀድ)

ድጋፍ የተሰጠው በ

የቅርንጫፍ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ፣ የሚስዮን ወይም የአውራጃ ፕሬዚዳንት ወይም አንድ የተመደበ አማካሪ

ጥሪዎች

የቅርንጫፍ ጸኃፊ፣ ረዳት ጸኃፊ እና ዋና ጸሃፊ

በጥቆማ የቀረበው በ

የቅርንጫፍ አመራሮች

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት ወይም የሚስዮን አመራር (ወይም በሚስዮን ፕሬዚዳንቱ፣ በአውራጃ አመራር ሲፈቀድ)

ድጋፍ የተሰጠው በ

የቅርንጫፍ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ ፕሬዚዳንት ወይም የተመደበ አማካሪ ወይም ከፍተኛ አማካሪ (በካስማ ውስጥ ላሉ ቅርንጫፎች)፤ የአውራጃ ፕሬዚዳንት ወይም እርሱ የመደበው የክህነት መሪ (በሚስዮኖች ውስጥ ላሉ ቅርንጫፎች)

ጥሪዎች

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት

በጥቆማ የቀረበው በ

የካስማ፣ የአውራጃ ወይም የሚስዮን አመራር (ከቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ ጋር በመመካከር)

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት ወይም የሚስዮን አመራር (ወይም በሚስዮን ፕሬዚዳንቱ፣ በአውራጃ አመራር ሲፈቀድ)

ድጋፍ የተሰጠው በ

የቅርንጫፍ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ ወይም የሚስዮን ፕሬዚዳንት (ወይም ከተመደበ የአውራጃ ፕሬዚዳንቱ)

ጥሪዎች

የሽማግሌዎች ቡድን አመራር አማካሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት (ከቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ ጋር በመመካከር)

የተፈቀደው በ

የካስማ አመራር እና ከፍተኛ ምክር ቤት ወይም የሚስዮን አመራር (ወይም በሚስዮን ፕሬዚዳንቱ፣ በአውራጃ አመራር ሲፈቀድ)

ድጋፍ የተሰጠው በ

የቅርንጫፍ አባላት

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

የካስማ ወይም የሚስዮን ፕሬዚዳንት ወይም የተመደበ አማካሪ ወይም ከፍተኛ አማካሪ (ወይም የአውራጃ ፕሬዚዳንቱ ወይም ከተመደበ ሌላ የክህነት መሪ )

ጥሪዎች

ሌሎች የአጥቢያ ጥሪዎች

በጥቆማ የቀረበው በ

30.8.1 ይመልከቱ፣ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት የሚለውን በኤጲስ ቆጰስ ቦታ እንዲሁም ቅርንጫፍ የሚለውን በአጥቢያቦታ ይተኩ።

የተፈቀደው በ

30.8.1 ይመልከቱ፣ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት የሚለውን በኤጲስ ቆጰስ ቦታ እንዲሁም ቅርንጫፍ የሚለውን በአጥቢያቦታ ይተኩ።

ድጋፍ የተሰጠው በ

30.8.1 ይመልከቱ፣ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት የሚለውን በኤጲስ ቆጰስ ቦታ እንዲሁም ቅርንጫፍ የሚለውን በአጥቢያቦታ ይተኩ።

የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በ

30.8.1 ይመልከቱ፣ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት የሚለውን በኤጲስ ቆጰስ ቦታ እንዲሁም ቅርንጫፍ የሚለውን በአጥቢያቦታ ይተኩ።

  1. ንቁ የቤተመቅደስ አታሚዎች በቅርንጫፍ አመራር ውስጥ ለማገልገል መጠራት የለባቸውም። አታሚዎች በቤተክርሰቲያኗ ፕሬዚዳንት አመራር ይጠራሉ።