“31. ከአባላት ጋር የሚደረጉ ቃለ መጠይቆች እና ሌሎች ስብሰባዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።
“31. ከአባላት ጋር የሚደረጉ ቃለ መጠይቆች እና ሌሎች ስብሰባዎች፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
31.
ከአባላት ጋር የሚደረጉ ቃለ መጠይቆች እና ሌሎች ስብሰባዎች
31.0
መግቢያ
ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ ሌሎችን አንድ በአንድ አገልግሏል (ለምሳሌ፣ ዮሃንስ 4፥5–26፤ 3 ኔፊ 17፥21)። ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች ይወዳል። እነርሱን በግለሰብ ደረጃ ይረዳቸዋል።
ይህ ምዕራፍ ከግለሰብ ጋር አንድ ለአንድ ለመገናኘት እድሎች ያላቸውን መሪዎች ሁሉ ሊረዳቸው ይችላል።
31.1
መሪ መርሆች
31.1.1
በመንፈስ ተዘጋጁ
በጸሎት፣ በቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና በቅድስና በመኖር ራሳችሁን በመንፈስ አዘጋጁ። የመንፈስ ቅዱስን ሹክሹክታ አድምጡ።
31.1.2
አባሉ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማው እርዱ
አባላት ለቃለ መጠይቅ ወይም ለግል ችግራቸው እርዳታ ለማግኘት ወደ እናንተ ሲመጡ፣ ብዙ ጊዜ ከሁሉም በላይ የሚፈልጉት የሰማይ አባት እንደሚወዳቸው ማወቅን ነው።
ቅዱሳት መጻህፍት እና የኋለኛው ቀን ነቢያት ቃል መንፈስን ይጋብዛሉ እንዲሁም ንጹህ ትምህርትን ያስተምራሉ። ለመውቀስ፣ ለማስገደድ ወይም ለማስፈራራት ሳይሆን ለማነሳሳት ተጠቀሙባቸው (ሉቃስ 9፥56 ይመልከቱ)።
31.1.3
አባሉ የአዳኙን ኃይል መጠቀም እንዲችል እርዱ
አበላት ወደእርሱ እንዲመለሱ አበረታቱ። ኃይሉን ለማጠናከር፣ ለማፅናናት እና ለማዳን መጠቀም እንዲችሉ እርዷቸው።
31.1.4
አባሉ ምቾት እና ደህንነት እንዲሰማው እርዱ
በቃለ መጠይቅ ወይም በስብሰባ ወቅት ሁልጊዜ ሌላ ሰው እንዲገኝ ለአባሉ ምርጫ ስጡ። የተቃራኒ ጾታ ካለው ሰው፣ ከልጅ ወይም ከወጣት ጋር ስትሰበሰቡ ወላጅ ወይም ሌላ ትልቅ ሰው መኖሩን አረጋግጡ። ስብሰባውን በሚካፈለው አባል ምርጫዎች ላይ በመመስረት እርሱ ወይም እርሷ ስብሰባውን መቀላቀል ወይም ከክፍል ውጭ መጠበቅ ይችላል/ትችላለች።
የትዳር አጋራችሁን ወይም ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎችን ጨምሮ፣ አባሉ ካልፈቀደ በስተቀር ሚስጥራዊ መረጃን ለማንም ጋር አታካፍሉ።
31.1.5
በመንፈስ የተነሳሱ ጥያቄዎችን ጠይቁ እንዲሁም በጥንቃቄ አድምጡ
ከአንድ አባል ጋር ስትሰበሰቡ የእርሱን ወይም የእርሷን ሁኔታ ለመገንዘብ የሚረዷችሁን ጥያቄዎች ጠይቁ።
አባሉ በሚናገርበት ጊዜ በጥንቃቄ እንዲሁም በትኩረት አዳምጡ።
31.1.6
እራስን መቻልን አበረታቱ
ለአባላቶቻችሁ ካላችሁ ፍቅር የተነሳ ለችግሮቻቸው ወዲያውኑ መፍትሄ ለመስጠት ትፈልጋላችሁ። ሆኖም የራሳቸውን መፍትሄ እንዲፈልጉ እና የራሳቸውን ውሳኔ እንዲወስኑ በመርዳት የበለጠ ትባርኳችኋላችሁ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 9፥8ን ይመልከቱ)።
31.1.7
ንስሃ ለመግባት የሚደረጉ ጥረቶችን ደግፉ
አንድ ሰው ከባድ ኃጢአቶችን እንዲፈታ የሚረዳው ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ብቻ ነው። ከእነዚህ አንዳንዶቹ በ32.6 ውስጥ ተዘርዝረዋል። አባሉ/ሏ ከእነዚህ ኃጢአቶች አንዱን የሰራ/ች ከሆነ/ች፣ እርሱ ወይም እርሷ ኤጲስ ቆጶሱን ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱን በአፋጣኝ ማግኘት አለባቸው።
31.1.8
ለጥቃት ተገቢውን ምላሽ ስጡ
በማንኛውም ዓይነት መልክ ያለ ጥቃትን መታገስ አይቻልም። የጥቃት ሪፖርቶችን በቁም ነገር ያዙ። አንድ ሰው ጥቃት እንደደረሰበት ካወቃችሁ፣ ጥቃቱን ለመንግስት ባለሥልጣናት አሳውቁ እንዲሁም ኤጲስ ቆጶሱን አማክሩ። ጥቃትን ሪፖርት ማድረጊያ እና ለጥቃት ምላሽ መስጫ መመሪያዎች በ 38.6.2ውስጥ ቀርበዋል።
31.2
ቃለ መጠይቆች
31.2.1
የቃለ መጠይቆች ዓላማዎች
በአጠቃላይ የቤተክርስቲያን መሪዎች አባላትን ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉት የሚከተሉትን ለመወሰን ነው፦
-
አንድን ሥርዓት ለመቀበል ወይም በዚያ ሥርዓት ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ስለመሆናቸው።
-
በቤተክርስቲያን ውስጥ በአንድ የሥራ መደብ ላይ መጠራት ካለባቸው።
31.2.2
የቃለ መጠይቆች ዓይነቶች
ቃለ መጠይቁን ማን ያደርጋል |
የቃለ መጠይቁ ዓላማ |
---|---|
ቃለ መጠይቁን ማን ያደርጋል ኤጲስ ቆጶስ ብቻ | የቃለ መጠይቁ ዓላማ
|
ቃለ መጠይቁን ማን ያደርጋል ኤጲስ ቆጶስ ወይም እርሱ የመደበው አማካሪ | የቃለ መጠይቁ ዓላማ
|
31.2.3
ጥምቀት እና የማረጋገጫ ቃለ መጠይቆች
31.2.3.1
በመዝገብ ላይ የሚገኙ ልጆች
ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያው መዝገብ ላይ የሚገኙ 8 ዓመት የሆናቸውን ልጆች የማጥመቅ የክህነት ቁልፎች አሉት። በዚህ ምክንያት ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበው አማካሪ ለሚከተሉት ሰዎች የጥምቀት እና የማረጋገጫ ቃለ መጠይቅ ያደርጋል፦
-
በመዝገብ ላይ ለሚገኙ አባል ለሆኑ 8 ዓመት ለሆናቸው ልጆች።
-
በመዝገብ የሚገኙ አባል ያልሆኑ ነገር ግን አባል የሆነ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ላላቸው 8 ዓመት ለሆናቸው ልጆች።
-
በአዕምሯዊ ውስንነት ምክንያት ጥምቀታቸው ለተራዘመ እድሜያቸው 9 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ በመዝገብ ውስጥ ያሉ አባላት።
በቃለ መጠይቁ ላይ የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ ልጁ የጥምቀቱን ዓላማ እንደተረዳ ያረጋግጣል (2 ኔፊ 31፥5–20ን ይመልከቱ)። በተጨማሪም ልጁ የጥምቀት ቃል ኪዳኑን እንደተረዳ እና በእርሱ ለመኖር ቁርጠኛ መሆኑን ያረጋግጣል (ሞዛያ 18፥8–10 ይመልከቱ)። የተወሰኑ ዝርዝር ጥያቄዎችን መጠቀም አያስፈልገውም። “ህጻናት [ልጆች] ንስሃ [ስለማያስፈልቸው]“ ይህ ለብቁነት የሚደረግ ቃለ መጠይቅ አይደለም (ሞሮኒ 8፥11)።
31.2.3.2
የተለወጡ
የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ የተለወጡትን የማጥመቅ የክህነት ቁልፎች አሉት። በዚህ ምክንያት፣ አንድ የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ የሚከተሉትን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል፦
-
ተጠምቀው እና ማረጋገጫ ተቀብለው ለማያውቁ 9 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ሰዎች። የአዕምሮ ውስነንነት ላለባቸው የተቀመጡ የተለዩ ሁኔታዎችን በ31.2.3.1 ይመልከቱ።
-
ወላጆቻቸው የቤተክርስቲያኗ አባላት ያልሆኑ 8 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ልጆች።
-
ወላጆቻቸውም የሚጠመቁ እና ማረጋገጫ የሚቀበሉ 8 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ልጆች።
31.2.4
በአሮናዊ ክህነት ውስጥ በአንድ ክፍል ሹመትን ለመቀበል የሚደረጉ ቃለ መጠይቆች
ለተጨማሪ መረጃ፣ 18.10.2ን ይመልከቱ።
31.2.5
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለመቀበል የሚደረጉ ቃለ መጠይቆች
ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው። ቤተመቅደስ መግባት እና በዚያም በሥርዓቶች መሳተፍ የተቀደሰ ዕድል ነው። ይህ እድል ስልጣን የተሰጣቸው የክህነት መሪዎች በሚወሰኑት መሠረት በመንፈስ ለተዘጋጁ እና በጌታ መሥፈርቶች ለመኖር ለሚጥሩ የተሰጠ ነው።
ይህንን ውሳኔ ለማድረግ፣ የክህነት መሪዎች በLCR [በመሪ እና በጸሀፊ ምንጭ] ውስጥ ያሉትን ጥያቄዎች በመጠቀም አባሉን ቃለ መጠይቅ ያደርጋሉ (በ26.3 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይመልከቱ)።
31.2.6
በመልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ በአንድ ክፍል ሹመትን ለመቀበል የሚደረጉ ቃለ መጠይቆች
የካስማ ፕሬዚዳንቱ የመልከ ጼዴቅ ክህነትን የመስጠት የክህነት ቁልፎች አሉት። በተጨማሪም በሽማግሌ እና በሊቀ ካህን ክፍሎች ለመሾም የሚያስችል የክህነት ቁልፎች አሉት።
በካስማ አመራሩ ፈቃድ፣ ኤጲስ ቆጶሱ በMelchizedek Priesthood Ordination Record [መልከ ጼዴቅ ክህነት ሹመት መዝገብ] ውስጥ የተቀመጡትን ጥያቄዎች በመጠቀም አባሉን ቃለ መጠይቅ ያደርገዋል።
31.3
መሪዎች ከአባላት ጋር መገናኘት የሚችሉባቸው ሌሎች እድሎች
-
አባላት መንፈሳዊ መመሪያ ሲፈልጉ ወይም ከባድ የግል ችግሮች ሲያጋጥሟቸው አንድን የቤተክርስቲያን መሪ ለማግኘት ሊጠይቁ ይችላሉ።
-
ኤጲስ ቆጶሱ ወይም እርሱ የመደበው ሰው ሥጋዊ ፍላጎቶች ካላቸው አባላት ጋር ይገናኛል (22.6ን ይመልከቱ)።
-
እያንዳንዱ የ11 ዓመት ልጅ ከመጀመሪያ ክፍል ወደ ዲያቆናት ቡድን ወይም ወደ ወጣት ሴቶች ክፍል ሲዘዋወር/ስትዘዋወር አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ከእርሱ/ሷ ጋር ይገናኛል።
31.3.1
ከወጣቶች ጋር መገናኘት
ኤጲስ ቆጶሱ ወይም ከአማካሪዎቹ አንዱ ከእያንዳንዱ ወጣት ጋር በዓመት ሁለቴ ይገናኛል። በእያንዳንዱ ዓመት ከሚደረጉት ከእነዚህ ስብሰባዎች ቢያንስ አንዱ ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር መሆን አለበት። ወጣቱ 16 ዓመት ከሚሞላው ዓመት ጀምሮ፣ በዓመቱ የሚደረጉት ሁለቱም ስብሰባዎች የሚቻል ከሆነ ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር መደረግ አለባቸው።
በተጨማሪም የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንቷ እያንዳንዷን ወጣት ሴት የማገልገል ኃላፊነት አለባት። ይህንንም ከወጣት ሴቶች ጋር አንድ ለአንድ በመገናኘት (ወይም ሌላ ጎልማሳ ባለበት) ማድረግ ትችላለች።
31.3.1.2
ውይይት የሚደረግባቸው ርዕሶች
በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት መገንባት እና እነርሱን እንዲከተላቸው ወጣቱን መርዳት ነው። እነዚህ ስብሰባዎች የሚያንጹ መንፈሳዊ ተሞክሮዎች መሆን አለባቸው።
31.3.2
ካላገቡ ወጣት ጎልማሶች ጋር መገናኘት
ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያው ላሉ ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች መንፈሳዊ እድገት ትልቅ ቦታ ይሰጣል። እርሱ ወይም የተመደበው አንድ አማካሪ ከእያንዳንዱ ያላገባ ወጣት ጎልማሳ ጋር ቢያንስ በዓመት አንዴ ይገናኛል።
31.3.3
ጥሪዎቻቸውን እና ኃላፊነቶቻቸውን በተመለከተ ለመወያየት ከአባላት ጋር መገናኘት
የካስማ አመራሮች፣ የኤጲስ ቆጶስ አመራሮች እና ሌሎች መሪዎች ስለጥሪያቸው ለእነርሱ ሪፖርት ከሚያደርጉ አባላት ጋር በግል ይገናኛሉ።
መሪው አባላቱ ለሚሰጡት አገልግሎት ምስጋናውን ይገልጻል እንዲሁም ማበረታቻ ይሰጣል።
31.3.6
በሙያው በሰለጠኑ ሰዎች ምክር እና ህክምና ማግኘት
የቤተክርስቲያን መሪዎች የተጠሩት በሙያው የሰለጠኑ አማካሪዎች እንዲሆኑ ወይም ህክምና እንዲሰጡ አይደለም። የሚሰጡት በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያጠነክር፣ የሚያፅናና እና የሚያድን ኃይል ላይ የሚያተኩር መንፈሳዊ ድጋፍ ነው። ከዚህ አስፈላጊ እና በመንፈስ የተነሳሳ እርዳታ በተጨማሪ፣ የሚገኝ ሲሆን አንዳንድ አባላት ከሙያዊ ምክር ሊጠቀሙ ይችላሉ።
31.4
ከአባላት ጋር በኮምፒተር የታገዘ የገፅ ለገፅ ግንኙነት ማድረግ
አብዛኛውን ጊዜ መሪዎች ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እና መንፈሳዊ እርዳታ ለመስጠት እንዲሁም ለማገልገል ከአባላት ጋር በአካል ይገናኛሉ። ሆኖም፣ እንደ ልዩ ሁኔታ፣ በአካል መገናኘት የማይቻል በሚሆንበት ጊዜ በኮምፒተር የታገዘ የገፅ ለገፅ ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ።