“32. ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ አባልነት ምክር ቤት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።
“32. ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ አባልነት ምክር ቤት፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
32.
ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ አባልነት ምክር ቤት
32.0
መግቢያ
አብዛኛው ንስሃ መግባት የሚፈጸመው በግለሰብ፣ በእግዚአብሔር እና ኃጢያቱን በፈጸመው ሰው በተጎዱት መካከል ነው። ሆኖም አንዳንዴ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዘደንት የቤተክርስቲያኗ አባላት ንስሃ ለመግባት የሚያደርጉትን ጥረት ማገዝ ይኖርበታል።
አባላት ንስሃ እንዲገቡ በሚረዱበት ጊዜ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዘደንቶች አፍቃሪ እና ተንከባካቢ ናቸው። ግለሰቦች የተሻሉ ሰዎች እንዲሆኑ በመደገፍ ፊታቸውን ከኃጢያት ዘወር እንዲያደርጉ እና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ የረዳቸውን የአዳኝን ምሳሌ ይከተላሉ (ማቴዎስ 9፥10–13፤ ዮሐንስ 8፥3–11 ተመልከቱ)።
32.1
ንስሃ መግባት እና ይቅርታ
የምህረት እቅዱ ይከናወን ዘንድ፣ የሰማይ አባት አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ለኃጢያታችን ክፍያ እንዲፈፅም ላከው (አልማ 42፥15 ይመልከቱ)። ኢየሱስም የፍትህ ህግ ለኃጢያታችን እንዲከፈል የሚፈልገውን ቅጣት ተቀብሏል። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥15–19 ይመልከቱ፤ በተጨማሪም አልማ 42፥24–25 ይመልከቱ)። በዚህ መስዋዕት አማካኝነት አብ እና ልጁ ለእኛ ያላቸውን ማለቂያ የሌለው ፍቅራቸውን አሳይተዋል (ዮሐንስ 3፥16ን ይመልከቱ)።
“በንስሃ እምነት[ን]” ስንለማመድ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ምህረትን በመስጠት የሰማይ አባት ይቅር ይለናል (አልማ 34፥15፤ በተጨማሪም አልማ 42፥13ን ይመልከቱ)። ስንነጻ እና ይቅር ስንባል፣ በመጨረሻ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ እንችላለን (ኢሳይያስ 1፥18ን፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42ን ይመልከቱ)።
ንስሃ መግባት ማለት ባህርይን ከመለወጥ በላይ ነው። ለኃጢያት ያለንን ዝንባሌ መተው እንዲሁም ወደ ሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መመለስ ማለት ነው። ልብን እና አዕምሮን ወደመለወጥ ይመራል (ሞዛያ 5፥2፤ አልማ 5፥12–14፤ ሔላማን 15፥7 ተመልከቱ)። በንስሃ አማካኝነት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የታረቅን አዲስ ሰዎች እንሆናለን (2 ቆሮንቶስ 5፥17–18፤ ሞዛያ 27፥25–26ን ይመልከቱ)።
ንስሐ የመግባት እድል የሰማይ አባት በልጁ ስጦታ አማካኝነት ከሰጠን የላቁ በረከቶች መካከል አንዱ ነው።
32.2
የቤተክርስቲያኗ አባልነትን መገደብ ወይም ከአባልነት የማስወገድ አላማዎች
ሰው ከባድ ኃጢያት ከሰራ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ እርሱ ወይም እርሷ ንስሃ እንዲገባ/እንድትገባ ይረዳል። እንደ ሂደቱ ክፍል፣ ለተወሰነ ጊዜ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶችን መገደብ ሊያስፈልገው ይችላል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ለተወሰነ ጊዜ አንድን ሰው ከአባልነት ማገድ ሊያስፈልገው ይችላል።
ሰውን ከአባልነት ማገድ ወይም ማስወገድ ቅጣትን ያለመ አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ተግባራት ሰው ንስሃ እንዲገባ እና የልብ ለውጥ እንዲያደርግ ለመርዳት አስፈላጊ ናቸው። እንዲሁም ሰው የእርሱን ወይም የእርሷን ቃል ኪዳን ለማደስ እና ለመጠበቅ በመንፈሳዊ የሚዘጋጅበት/የምትዘጋጅበትን ጊዜ ይሰጣሉ።
የአባልነት ገደቦች ወይም ከአባልነት የማስወገድ ሶስቱ አላማዎች የሚከተሉት ናቸው።
32.2.1
የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል
የመጀመሪያው አላማ የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ መርዳት ነው። አንዳንድ ጊዜ ሰው አካላዊ ወይም መንፈሳዊ ስጋት ሊሆን ይችላል። ሌላን ለመጉዳት ሆን ብሎ የሚደረግ ወንጀለኛ ባህሪ፣ አካላዊ ጉዳት፣ ፆታዊ ጥቃት፣ የዕፅ ሱሰኝነት፣ ማጭበርበር እና ክህደት ይህ ሊከሰት ከሚችልባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ ናቸው። በሚያገኘው መነሳሳት፣ ሰው በእነዚህ እና በሌሎች ከባድ መንገዶች ስጋት ሲፈጥር፣ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዘደንት የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እርምጃ ይወስዳል (አልማ 5፥59–60ን ይመልከቱ)።
32.2.2
ሰው በንስሃ አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ሃይል አንዲያገኝ እርዳታ መስጠት
ሁለተኛው ዓላማ ሰው በንስሃ አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ሃይል አንዲያገኝ መርዳት ነው። በዚህ ሂደት፣ እርሱ ወይም እርሷ እንደገና ንጹህ ለመሆን እና ሁሉንም የእግዚአብሔር በረከቶች ለመቀበል ብቁ ሊሆን/ልትሆን ይችላል/ትችላለች።
32.2.3
የቤተክርስቲያኗን ሀቀኝነት መጠበቅ
ሶስተኛው ዓላማ የቤተክርስቲያኗን ሀቀኝነት ለመጠበቅ ነው። ምግባሩ ወይም ምግባሯ ቤተክርስቲያንን በእጅጉ የሚጎዳ ከሆነ፣ ሰውን ከቤተክርስቲያኗ አባልነት መገደብ ወይም ማስወገድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል (አልማ 39፥11ን ተመልከቱ)። እነዚህን በማስተካከል እንጂ፣ ከባድ ኃጢያቶችን መደበቅ ወይም ማሳነስ የቤተክርስቲያን ሀቀኝነትን አይጠበቅም።
32.3
የእሥራኤል ዳኞች ሚና
ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች የእስራኤል ዳኛዎች እንዲሆኑ ይጠራሉ እንዲሁም ይለያሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥72–74 ይመልከቱ)። የቤተክርስቲያኗ አባላት ንስሐ እንዲገቡ በመርዳት ረገድ ጌታን ለመወከል የክህነት ቁልፎች አሏቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1ን፤ 107፥16–18ን ይመልከቱ)።
አብዛኛውን ጊዜ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዳንቶች በግል ምክር አማካኝነት ንስሃ መግባትን ያግዛሉ። ይህ እገዛ መደበኛ ባልሆነ ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶችን መገደብን ሊያካትት ይችላል።
ለአንዳንድ ከባድ ኃጢያቶች፣ መሪዎች የአባልነት ሸንጎ በማካሄድ ንስሃ መግባትን ይደግፋሉ (32.6ን ይመልከቱ)። ይህ እገዛ መደበኛ በሆነ ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶችን መገደብን ወይም ከቤተክርስቲያኗ አባልነት መወገድን ሊያካትት ይችላል።
ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚደንቶች አባላት ንስሃ እንዲገቡ በሚረዱበት ጊዜ አፍቃሪ እና ተንከባካቢ ናቸው። አዳኙ ስታመነዝር ከተያዘችው ሴት ጋር ያደረገው ግንኙነት መመሪያ ነው (ዮሐንስ 8፥3–11 ይመልከቱ)። ኃጢያትዋ ይቅር ተብሎላታል ባይልም፣ አልኮነናትም። ከዚያ ይልቅ “ከአሁን ጀምሮ ደግማ ኃጢያት እንዳትሰራ”—ንስሃ አንድትገባ እና ህይወቷን እንድትቀይር—ነገራት።
እነዚህ መሪዎች “ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢያተኛ በሰማይ ደስታ [እንደሚሆን]” ያስተምራሉ (ሉቃስ 15፥7)። እነርሱም ታጋሽ፣ ደጋፊ እና አዎንታዊ ናቸው። እነርሱም ተስፋን ያነሳሳሉ። በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕትነት ምክንያት ሁሉም ንስሃ መግባት እና ንጹህ መሆን እንደሚችሉ ያስተምራሉ እንዲሁም ይመሰክራሉ።
ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዘደንቶች እያንዳንዱ ሰው ንስሃ በሚገባበት እንዴት ለመርዳት እንደሚችሉ ለማወቅ ከመንፈስ መመሪያን ይሻሉ። በጣም ከባድ ለሆኑት ኃጢያቶች ብቻ ነው መሪዎቿ ምን ዓይነት እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸው የተቀመጠ መስፈርት ቤተክርስቲያኗ ያላት (32.6ን ይመልከቱ)። ሁለት ሁኔታዎች ተመሳሳይ አይደሉም። መሪዎች የሚሰጡት ምክር እና የሚያመቻቹት ንስሃ የመግባት ሂደት በመንፈስ የተነሳሳ መሆን አለበት እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሰው የተለየ ሊሆን ይችላል።
32.4
መናዘዝ፣ ሚስጥራዊነት እና ለመንግስት ባለስልጣናት ማሳወቅ
32.4.1
መናዘዝ
ንስሃ መግባት ለሰማይ አባት ኃጢያት መናዘዝን ይጠይቃል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሏል “በዚህም ሰው ለኃጢያቶቹ ንስሀ እንደገባ ታውቃላችሁ—እነሆ፣ ይናዘዛቸዋል እናም ይተዋቸዋልም“ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥43ን፤ በተጨማሪም ሞዛያ 26፥29ን ይመልከቱ)።
የቤተክርስቲያኗ አባላት ከባድ ኃጢያት በሚሰሩበት ጊዜ፣ ንስሃቸው ለኤጲስ ቆጶሳት እና ለካስማ ፕሬዘደንቶች መናዘዝን ያካትታል። ከዚያም እነርሱን በመወከል የንስሐ ወንጌልን ቁልፎች መጠቀም ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1ን፤ 84፥26–27፤ 107፥18፣ 20ን ይመልከቱ)። ይህም በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ኃይል እንዲፈውሱ እና ወደ ወንጌል መንገድ እንዲመለሱ ይረዳቸዋል።
የመናዘዝ አላማ አባላት በመለወጥ እና በመፈወስ ሙሉ በሙሉ የጌታን እርዳታ ይፈልጉ ዘንድ ሸክማቸውን ከላያቸው እንዲያወርዱ ማበረታታት ነው። “የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ“ ማዳበር በኑዛዜ ይታገዛል (2 ኔፊ 2፥7)። በፈቃደኝነት የሚደረግ ኑዛዜ ሰው ንስሃ መግባት እንደሚፈልግ ያሳያል።
አባል በሚናዘዝበት ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በ32.8 ውስጥ የተቀመጠውን ምክር የመስጠት መመሪያ ይከተላል። አባሉን ንስሐ ለመግባት ስለሚረዳው ተስማሚ ጊዜና ቦታ መመሪያ ለማግኘት በጸሎት መንፈስ ይጠይቃል። የአባልነት ምክር ቤት በዚህ ሊረዳ ይችል እንደሆነም ግምት ያስገባል። የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲ የአባልነት ምክር ቤት መጠራት እንደሚያስፈልግ የሚያመለክት ከሆነ፣ ይህንን ያብራራል (32.6ን ይመልከቱ)።
አንዳንድ ጊዜ አባል የትዳር ጓደኛን ወይም ሌላ አዋቂን ጎድቶ ሊሆን ይችላል። እንደ ንስሐ አካል፣ እርሱ ወይም እርሷ አብዛኛውን ጊዜ ለዚያ ሰው መናዘዝ እና ይቅርታ መጠየቅ አለበት/አለባት። አንድ ወጣት ከባድ ኃጢያት ከሰራ/ች ከአርሱ ወይም ከእርሷ ወላጆች ጋር እንዲማከር/እንድትማከር ይበረታታል/ትበረታታለች።
32.4.4
ሚስጥራዊነት
ኤጲስ ቆጶሳት፣ የካስማ ፕሬዳንንቶች፣ እና አማካሪዎቻቸው የተሰጧቸውን ሚስጥራዊ መረጃዎች ሁሉ የመጠበቅ የተቀደሰ ሃላፊነት አለባቸው። ይህ መረጃ ከቃለ መጠይቅ፣ ከማማከር እና ከኑዛዜዎች ውስጥ ሊገኝ ይችላል። በአባልነት ምክር ቤት ውስጥ የሚሳተፉ ሁሉ ተመሳሳይ ምስጢር የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው። ሚስጥራዊነት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም አባላት የሚያጋሩት ነገር በሚስጥር የሚያዝ ካልሆነ ኃጢያቶችን ላይናዘዙ ወይም መመሪያ ላይፈልጉ ይችላሉ። መተማመንን ማፍረስ የአባላትን እምነት ይሸረሽራል እንዲሁም በመሪዎቻቸው ላይ እምነት እንዲያጡ ያደርጋቸዋል።
ሚስጥራዊ ኃላፊነቱን በጠበቀ መልኩ፣ አንድ ኤጲስ ቆጶስ፣ የካስማ ፕሬዚዳንት ወይም አማካሪዎቻቸው እነዚህን መረጃዎች በሚከተለው መልኩ ብቻ ሊያጋሩ ይችላሉ፦
-
የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድን ወይም ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ ከአባሉ የካስማ ፕሬዚዳንት፣ የሚስዮን ፕሬዚዳንት ወይም ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር መነጋገር ያስፈልጋቸዋል።
-
የአባልነት ውሳኔዎችን ወይም ሌሎች አሳሳቢ ጉዳዮችን በመጠባበቅ ላይ እያሉ ግለሰቡ ወደ አዲስ አጥቢያ ከተዛወረ (ወይም የክህነት መሪው ከጥሪው ከለቀቀ)።
-
አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዘደንት ከአጥቢያው ወይም ከካስማው ውጭ የሚኖር የቤተክርስቲያኗ አባል በከባድ ኃጢያት ውስጥ ተሳታፊ ሊሆን እንደሚችል ያወቀ ከሆነ።
-
የአባልነት ምክር ቤት በሚካሄድበት ወቅት መረጃን መግለፅ አስፈላጊ ነው።
-
አንድ አባል፣ መሪው መረጃን ለተወሰኑ ሰዎች እንዲያካፍል ፍቃድ ለመስጠት ከመረጠ።
-
የአባልነት ምክር ቤት ውሳኔን አስመልክቶ የተወሰነ መረጃን ማካፈል አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
መሪዎችን የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ህጉን ለማክበር እንዲችሉ ለመርዳት እንዲቻል ቤተክርስቲያኗ በሰለጠኑ ባለሙያዎች እርዳታ ትሰጣለች። ይህንን መመሪያ ለማግኘት፣ መሪዎች አገልግሎቱ ባለበት ቦታ የቤተክርስቲያኗን የጥቃት እርዳታ መስጫ የስልክ መስመር ወዲያውኑ ይደውላሉ (38.6.2.1ን ይመልከቱ)። አገልግሎቱ የማይገኝ ከሆነ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በዋና አካባቢው ቢሮ የሚገኘውን የአካባቢውን የህግ አማካሪ ያነጋግራል።
አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት መጀመሪያ እንደዚህ አይነት መመሪያ ሳያስፈልገው ሚስጥራዊ መረጃን መግለፅ የሚኖርበት በአንድ ሁኔታ ውስጥ ብቻ ነው። ይህም ለህይወት አስጊ የሆኑ ጥቃቶችን ወይም ከባድ ጉዳቶችን ለመከላከል ሲባል መረጃን መግለፅ አስፈላጊ ሲሆን እና መመሪያ ለመጠየቅ ጊዜ ከሌለው ነው። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሌሎችን የመጠበቅ ግዴታ ሚስጥራዊ ከመሆን ግዴታ የበለጠ አስፈላጊ ነው። መሪዎች የመንግሥት ባለስልጣናትን በአስቸኳይ ማነጋገር አለባቸው።
32.6
የኃጢያቱ ክብደት እና የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲ
የኃጢያት ክብደት (1) የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና (2) አንድ ሰው ንስሐ እንዲገባ የሚረዳውን ሁኔታ ለመወሰን ጠቃሚ የሆነ ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ነገር ነው። ጌታ “ኃጢያትን በዝቅተኛ ደረጃ መመልከት አይቻለኝም” ብሏል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥31ን፤ በተጨማሪም ሞዛያ 26፥29ን) ይመልከቱ)። አገልጋዮቹ የከባድ ኃጢያት ማስረጃዎችን ችላ ማለት አይገባቸውም።
ከባድ ኃጢያቶች ሆን ተብሎ በእግዚአብሔር ህግጋት ላይ የሚፈጸም ትልቅ ወንጀል ነው። የከባድ ኃጢያት ምድቦች ከታች ተዘርዝረዋል።
-
የጠበኝነት ድርጊቶች እና ጥቃት
-
ወሲባዊ የስነምግባር ጉድለት
-
የማጭበርበር ድርጊቶች
-
እምነትን ማጉደል
-
አንዳንድ ሌሎች ተግባራት
የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ሲሆን ወይም ምናልባት አስፈላጊ ሲሆን
የኃጢያት አይነት |
የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው |
የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል |
---|---|---|
የኃጢያት አይነት የጠበኝነት ድርጊቶች እና ጥቃት | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል |
የኃጢያት አይነት ወሲባዊ የስነምግባር ጉድለት | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል
|
የኃጢያት አይነት የማጭበርበር ድርጊቶች | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል
|
የኃጢያት አይነት እምነትን ማጉደል | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል
|
የኃጢያት አይነት አንዳንድ ሌሎች ተግባራት | የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ ነው
| የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል
|
32.6.3
የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአባልነት ምክር ቤት ወይም ሌላ እርምጃ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ ከዋና አካባቢ አመራር ጋር የሚማከሩበት ጊዜ
አንዳንድ ጉዳዮች ተጨማሪ ጥንቃቄ እና መመሪያ ያስፈልጋቸዋል። እንዴት በተሻለ ሁኔታ መርዳት እንደሚቻል ለማወቅ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በዚህ ክፍል ውስጥ ስላሉት ሁኔታዎች ከዋና ካባቢ አመራር ጋር መማከር ይኖርበታል።
32.6.3.2
ክህደት
የክህደት ጉዳዮች ብዙውን ጊዜ ከአጥቢያው ወይም ከካስማው ወሰን ውጪ ተፅእኖ አላቸው። የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል በአፋጣኝ መፍትሄ ማግኘት አለባቸው።
የአንድ አባል ድርጊት ክህደትን ሊያመለክት እንደሚችል ከተሰማው ኤጲስ ቆጶሱ ከካስማ ፕሬዘደንቱ ጋር ይማከራል።
እዚህ ላይ ባለው አጠቃቀም፣ ክህደት ከሚከተሉት ውስጥ በአንዱ ውስጥ የሚሳተፍ አባልን ያመለክታል፦
-
በተደጋጋሚ ቤተክርስቲያኗን፣ ትምህርቶቿን፣ ፖሊሲዎቿን ወይም መሪዎቿን በግልፅ እንዲሁም ሆን ብሎ በገሃድ መቃወም
-
በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በካስማ ፕሬዚዳንቱ እርማት ከተሰጠው በኋላ የቤተክርስቲያኗ ትምህርት ያልሆነውን እንደ ቤተክርስቲያኗ ትምህርት በማስተማር መቀጠል
-
ሆን ብሎ የቤተክርስቲያኗን አባላት እምነት እና እንቅስቃሴ የማዳከም ስራ ልምድን ማሳየት
-
በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በካስማ ፕሬዚዳንቱ እርምት ከተሰጠው በኋላ የክህደት ኑፋቄ ትምህርቶችን መከተልን መቀጠል
-
በመደበኛነት ሌላ ቤተክርስቲያንን መቀላቀል እና አስተምህሮቶቹን ማስተዋወቅ
32.6.3.3
የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ መመዝበር
አንድ አባል የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ከመዘበረ ወይም የቤተክርስቲያኗን ውድ ንብረት ከሰረቀ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአባልነት ምክር ቤት ወይም ሌላ እርምጃ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ ከዋና አካባቢ አመራር ጋር ይማከራል።