ምዕራፍ ፱
ኔፊ በሁለት የተካፈሉ መዝገቦችን ሰራ—እያንዳንዳቸው የኔፊ ሰሌዳዎች ይባላሉ—ትልልቆቹ ሰሌዳዎች አለማዊውን ታሪክ ይዘዋል፤ ትንንሾቹም ቅዱሳን ነገሮችን። ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እና አባቴ በልሙኤል ሸለቆ፣ ውስጥ በድንኳን ሲኖር፣ እነዚህን ነገሮች ሁሉና፣ በእነዚህ ሰሌዳዎች ላይ ሊፃፉ የማይችሉትን፣ ብዙ ትላልቅ ነገሮችን አየ፣ እንዲሁም ሰማ፣ ተናገረም።
፪ እናም አሁን፣ እነዚህን ሰሌዳዎች በተመለከተ እንደተናገርኩት፣ እነሆ እነርሱ የህዝቤን ታሪክ በሙሉ የፃፍኩባቸው ሰሌዳዎች አይደሉም፤ የእኔን ህዝቦች ታሪክ በሙሉ የፃፍኩባቸው ሰሌዳዎች ኔፊ የሚል ስም ሰጥቻቸዋለሁ፤ ስለዚህ፣ እነርሱ በእኔ ስም የኔፊ ሰሌዳዎች ተብለው ይጠራሉ፤ እናም እነዚህ ሰሌዳዎች ደግሞ የኔፊ ሰሌዳዎች ተብለው ይጠራሉ።
፫ ሆኖም፣ እኔ ለተለየ ዓላማ ስለህዝቦቼ አገልግሎት ታሪክ በእነዚህ ሰሌዳዎች በመቅረፅ እንድፅፍ ከጌታ ትዕዛዝ ተቀብያለሁ።
፬ በሌሎቹም ሰሌዳዎች ላይ የንጉሶቹን የንግስ ታሪክ፣ እናም የጦርነትና የእኔ ህዝቦች ፀብ መቀረፅ አለበት፤ ስለዚህ እነዚህ ሰሌዳዎች በይበልጥ ስለአገልግሎት የሚቀረጹበት፤ እናም ሌሎች ሰሌዳዎች ስለንጉሶቹ ንግስና የእኔ ህዝቦች ፀብና ጦርነቶች የሚቀረጹበት ናቸው።
፭ ስለዚህ ጌታ እነዚህ ሰሌዳዎች ለብልህ ዓላማው እንድሰራው አዘዘኝ፣ ይህንም አላማ እኔ አላውቀውም።
፮ ነገር ግን ጌታ ሁሉንም ነገሮች ከመጀመሪያ ጀምሮ ያውቃል፤ ስለዚህ፣ ሁሉንም የእርሱን ስራዎች በሰው ልጆች መካከል ለመፈፀም መንገድ ያዘጋጃል፤ እነሆም፣ የእርሱ ቃላት በሙሉ የሚያሟላበት ሁሉም ኃይል አለው። እናም ይህ ነው። አሜን።