ቅዱሳት መጻህፍት
፩ ኔፊ ፳፩


ምዕራፍ ፳፩

መሲሁ ለአህዛብ ብርሃን ይሆናል እንዲሁም እስረኞችን ያስለቅቃል—እስራኤልም በኋለኛው ቀናት በኃይል ትሰበሰባለች—ንጉሶችም የእነርሱ አሳዳጊ አባቶች ይሆናሉ። ኢሳይያስ ፵፱ን አነፃፀር። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንደገና፤ እናንተ የተገነጠላችሁና በህዝቦቼ እረኞች ኃጢያት የተነሳ ለቃችሁ እንድትወጡ የተደረጋችሁ የእስራኤል ቤት ሆይ ስሙ፤ አዎን እናንተ የተገነጠላችሁ ሁሉ፣ በስፋት የተበተናችሁ በሙሉ፣ ከእኔ ህዝቦች የሆንሽ የእስራኤል ቤት ሆይ። ደሴቶች ሆይ ስሙኝ፣ እናንተም በሩቅ ያላችሁ ህዝቦች አድምጡኝ፤ ጌታ ከማህፀን ጠርቶኛል፣ ከእናቴም ማህጸን ጀምሮ ስሜን አንስቶአል።

እናም እርሱ አፌን እንደተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፤ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፣ እንደተወለወለ ፍላፃም አድርጎኛል፤ በሰገባውም ውስጥ ሸሽጎኛል፤

እናም እርሱ እስራኤል ሆይ፣ አንተ አሽከሬ ነህ፣ በአንተም እከብራለሁ አለኝ።

ከዚያም እኔ በከንቱ ደከምኩ፣ ምንም ጥቅም ለሌለውና በከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ በእርግጥ ከጌታ ዘንድ ስራዬም በአምላኬ ዘንድ ነው አልሁ።

እናም አሁን ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ አሽከር እሆነው ዘንድ ከማህፀን ጀምሮ የሰራኝ ጌታ እንዲህ ይላል፣ እስራኤልን ባትሰበሰብም፣ ግን በጌታ ዐይን ተከባሪ እሆናለሁ፣ አምላኬም ጉልበቴ ይሆንልኛል።

እናም እንዲህ አለ፥ አንተ የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሳና ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመልስ አገልጋይ መሆንህ እጅግ ቀላል ነገር ነው። እስከምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአህዛብ ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።

ጌታ፣ የእስራኤል መድኃኒት፣ ቅዱሱ፣ ሰዎች ለሚንቁት፣ ህዝብ ለሚጠላው፣ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፥ ጌታ ታማኝ ስለሆነ ነገሥታት አይተው ይነሳሉ፣ መሳፍንትም ደግሞ ይሰግዳሉ።

ጌታ እንዲህ ይላል፥ በተወደደም ጊዜ ሰምቼሀለሁ፣ የባህር ደሴቶች ሆይ፣ እናም በደህንነት ቀንም ረድቼሃለሁ፤ እናም እጠብቅህማለሁ፣ ምድርን ታቀና ዘንድ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ አገልጋዬን እንደ ቃል ኪዳን አድርጌ ለህዝቡ እሰጥሀለሁ፤

ለእስረኞቹ፣ ውጡ፣ በጨለማም ለተቀመጡትም፣ ተገለጡ በላቸው። በመንገድም ላይ ይበላሉ፣ ማሰማርያቸውም በወና ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል።

አይራቡም፣ አይጠሙም፣ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጎዳቸውም፤ የሚራራላቸው ይመራቸዋል፣ እንዲሁም በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋል።

፲፩ እናም ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፣ ጎዳኖቼም ከፍ ይላሉ።

፲፪ ከእዚያም የእስራኤል ቤት ሆይ ተመልከቱ፣ እነዚህ ከሩቅ፣ እናም አቤቱ፣ ከሰሜን፣ ከምዕራብ እነዚህም ከሲኒም አገር ይመጣሉ።

፲፫ ምክንያቱም ጌታ ህዝቡን አፅናንቶአልና፣ በተሰቃዩትም ላይ ምህረትን ያደርጋልና ሰማያት ሆይ ዘምሩ፣ እናም ምድር ሆይ ተደሰቱ፣ በምስራቅ ያሉ ህዝቦችሽ ይቋቋማሉና፤ እናም ለመዘመር ተነሱ፣ ተራሮች ሆይ ከእንግዲህ አይቀጡምና።

፲፬ እነሆ ፅዮን ግን እንዲህ ብላለች፥ ጌታ ትቶኛል እናም ጌታዬ እረስቶኛል—ነገር ግን እርሱ እንዳልረሳ ያሳያል።

፲፭ በእውኑ ሴት ከማህፀንዋ ለተወለደው ወንድ ልጅ እስከማትራራ ድረስ የምታጠባውን ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነርሱ ይረሱ ይሆናል እኔ ግን አልረሳሽም

፲፮ እነሆ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፣ ግንቦችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።

፲፯ ልጆችሽ ያወደሙሽ ላይ ይፈጥናሉ፣ እናም ያጠፉሽ ከአንቺ ዘንድ ይወጣሉ።

፲፰ ዓይንሽን አንስተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፣ እናም እነሆ እነዚህ ሁሉ እራሳቸውን ሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። እኔ ህያው እንደሆንኩ፣ እነዚህን ሁሉ እንደጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፣ እንደሙሽራም ትጎናፀፊያቸዋለሽ፣ ይላል ጌታ።

፲፱ ባድማሽና ውድማሽ፣ ወናም የሆነው ምድርሽ፣ እናም የጥፋትሽ ምድር ከሚኖሩብሽ የተነሳ ዛሬ ጠባብ ትሆናለች፣ የዋጡሽም ይርቃሉና።

የመጀመሪያውን ካጣሽ በኋላ ያገኘሻቸው ልጆችሽ በጆሮሽ ስፍራ፥ በጣም ጠቦኛልና እንቀመጥ ዘንድ ቦታ አስፊልኝ ይላሉ።

፳፩ በዚያም ጊዜ አንቺም በልብሽ ትያለሽ፥ የወላድ መካን ሆኜና፣ እኔም ብቸኛ ሆኜ፣ ታስሬና ተቅበዝብዤ እያለሁ እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፣ እነዚህስ ወዴት ነበሩ?

፳፪ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ እነሆ እጄን ወደ አህዛብ አነሳለሁ፣ አርማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በክንዳቸው ያመጡአቸዋል፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ይሸከሟቸዋል።

፳፫ ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፣ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ፊቶቻቸውን ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፣ እና የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤ እኔንም የጠበቁ አያፍሩምና።

፳፬ በውኑ ብዝበዛ ከኃያል እጅ ይወሰዳልን? ወይስ ህጋዊ ምርኮኞች ያመልጣሉን?

፳፭ ጌታ ግን እንዲህ ይላል፣ በሃያላን የተማረኩም ይወሰዳሉ፣ የአሸባሪም አደን ይወሰዳል፤ ምክንያቱም ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፣ ልጆችሽንም አድናለሁ።

፳፮ እናም አስጨናቂዎችሽን ስጋቸውን አስበላቸዋለሁ፤ እንደጣፋጭም ወይን ጠጅም በደማቸው ይሰክራሉ፤ እናም ስጋ ለባሹም ሁሉ እኔ ጌታ አዳኝሽና መድኃኒትሽና፣ የያዕቆብም ኃያል እንደሆንኩ ያውቃሉ