2010 (እ.አ.አ)
በእርስ የሚመኩ መሆን
ጥር 2010 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት

በእርስ የሚመኩ መሆን

እነዚህን ቅዱስ መጻህፍትን እና ጥቅሶችን ወይም፣ አስፈላጊም ከሆነ፣ የምትጎበኗቸውን እህቶች ፍላጎት የሚያሟሉትን ሌሎች መሰረቶች አስተምሩ። ስለትምህርቱም ምስክራችሁን ስጡ። የምትጎብኟቸውንም የተማሩትን እና የሚሰማቸውን እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው።

በእራስ መመካት ምንድን ነው?

“‘በእራስ መመካት ማለት የሰማይ አባት በረከቶቻችንን በሙሉ በመጠቀም እራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን መንከባከብ እና ለችግሮቻችንም መልስ እራሳችን ማግኘት ነው ማለት ነው።’ ችግሮች ከመድረሳቸው በፊት የማስወገድ እና ፈተናዎች ሲመጡም ለማሸነፍ የመማር ሀላፊነት እያንዳንዳችን አለን። …

“እንዴት በእርስ የሚመኩ ለመሆን እንችላለን? በእራስ መተማመን የምንሆነው ብቁ እውቀትን፣ ትምህርትን፣ እና የማንበብና የመጻፍ ችሎታን በማግኘት ፤ ገንዘብን እና ያሉንን ነገሮች በጥበብ በመቆጣጠር፣ በመንፈስ ጠንካራ በመሆን፣ ለድንገት አጋጣሚዎች እና ለሚደርሱት በመዘጋጀት፤ እና ሰውነታዊ ጤናነት እና ህብረተሰባዊና ስሜታዊ ደህናነት በማግኘት ነው።”1

ጁሊ ቢ ቤክ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት።

የወንጌል ሀላፊነት

“ለወደፊት አላማ በመያዝ እና ስጦታችንን እና ችሎታችንን በማሳደግ ስንኖር፣ በእራስ የምንመካ እንሆናለን። በእራስ መመካት ለእራሳችን እና የሰማይ አባት እኛ እንድንከባከባቸው በአደር ለሰጠን መንፈሳዊ እና ስጋዊ ደህንነት ሀላፊነት መውሰድ ማለት ነው። በእራስ ስንመካ ብቻ ነው ሌሎችን የማገልገል እና የመባረክ የአዳኝን ምሳሌ የምንከተለው።

በእራስ መተማመን ለመጨረሻ ውጤትየምንደርስበት መንገድ እንደሆነ መረዳቱ አስፈላጊ ነው። የመጨረሻው አላማችን እንደ አዳኝ ለመሆን ነው፣ እና ያም አላማ የሚያድገው ሌሎችን ራስ ወዳጅ ያለመሆን በማገልገል ነው። ሌሎችን ለማገልገል ያለን ችሎታ የሚያድገው ወይም የሚቀንሰው በእራስ መተማመን ሚዘናችን ነው።2

የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል ካህን ሮበርት ዲ ሔልስ።

“በእራስ መተማመን የስራችን ውጤት ነው እና ሌሎች የበጎ ድርጊት ስራዎችን ሁሉ መሰረት የሚሰጥ ነው። በመንፈሳዊ እና በስጋዊ ደህንነታችን ላይ በጣም አስፈላጊ የሆነም ነው። ስለዚህ የመመሪያ መሰረት፣ ፕሬዘደንት ሜሪያን ጂሮምኒ [1897–1988 (እ.አ.አ)] እንዳሉት፧ “ለምንፈልገው እንስራ። በእራስ የምንተማመን እና ጥገኛ ያልሆንን እንሁን። ደህንነት በሌላ ምንም መሰረታዊ መመሪያ ሊገኝ አይቻልም። ደህንነት የግል ጉዳይ ነው፣ እና የእራሳችንን ደህንነት በስጋዊ እና በመንፈሳዊ ነገሮች ማከናወን አለብን’ …

“ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል [1895–1985 (እ.አ.አ.)] በእራስ መተማመንን በሚመለከት በተጨማሪ እንዳስተማሩት፧ ‘የእያንዳንዱ ሰው ማህበራዊ፣ መንፈሳዊ፣ ሰውነታዊ፣ ወይም የገንዘብ ደህንነት ሀላፊነት መጀመሪያ የሚያርፈው በግል ላይ፣ ሁለተኛም በቤተሰቡ ላይ፣ እና ሶስተኛም ታማኝ አባል ከሆነውም በቤተክርስትያኗ ላይ ነው።’”3

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን።

ማስታወሻዎች

  1. “The Welfare Responsibilities of the Relief Society President,” Basic Principles of Welfare and Self-Reliance (2009), 4–5.

  2. “A Gospel Vision of Welfare: Faith in Action,” Basic Principles of Welfare and Self-Reliance (2009), 1–2.

  3. “Guiding Principles of Personal and Family Welfare,” ሊያሖና, የካቲት 1987, 3.

አትም