የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥር 2010 (እ.አ.አ)
ለትንሽ ጊዜ ታማኝ ሁኑ
የከርትላንድ ዘመን የሚጸና አንድ ትምህርት ቢኖር መንፈሶቻችን ፅኑ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው ነው። የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ሁሉ ለመቋቋም ወደ ጌታ በየቀኑ ቅርብ መሆን ያስፈልገናል።
ባለፈው በጋ ባለቤቴ እና እኔ የመንታ የልጅ ልጆቻችንን ወደ ከርትላንድ ኦሀዮ ወሰድናቸው። ይህም ወደ ሚስዮን ከመሄዳቸው በፊት ከእነርሱ ጋር የምናሳልፍበት ልዩ እና ውድ እድል ነበር።
በእዚያ ጉብኝታችን ጊዜ፣ የነብዩ ጅሴፍ ስሚዝ እና በከርትላንድ ይኖሩ የነበሩትን ቅዱሳን አጋጣሚዎች በደንብ እንዲገባን ለመማር ቻልን። የእዚያ የቤተክርስትያኗ የታሪክ ዘመን በተለያዩ ፈተናዎች ብቻ ሳይሆን በታላቅ በረከቶች የሚታወቅ ጊዜ ነበር።
በከርትላንድ ውስጥ ጌታ ይህች አለም ከዚህ በፊት አጋጥሟት ከነበሩት በላይ በጣም አስደናቂ የሆኑ ሰማያዊ መገለጥን እና መንፈሳዊ ስጦታዎችን ሰጠ። ስልሳ አምስት የትምህርት እና ቃል ኪዳን ክፍሎች—እንዲሁም እንደ ዳግም ምፅዓት፣ እርዳታ የሚፈልጉትን እንደመንከባከብ፣ እንደ ደህንነት አላማ፣ እንደ የክህነት ስልጣን ባለስልጣንነት፣ እንደ ጥበብ ቃል፣ እንደ አስራት፣ እንደ ቤተመቅደስ፣ እና እንደ ቅድስና ህግ አይነት አዲስ ብርሀን እና እውቀት ያመጡ ራዕያት—የተሰጡት በከርትላንድና በአካባቢዋ ነበር።1
ይህም እኩል የሌለው የመንፈሳዊ እድገት ዘመን ነበር። በእርግጥም፣ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደሚነድ እሳት ነበር። ከሰማይ አባታችን እና ከልጁ፣ ከአለም አዳኝ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በተጨማሪ ሙሴ፣ ኤልያስ፣ እና ሌሎች ሰማያዊ ስዎች በዚህ ጊዜ መጥተው ነበር።2
ጆሴፍ ከተቀበላቸው ብዙ ራዕዮች መካከል አንዱ “የወይራ ቅጠል … ከገነት ዛፍ የተቀጠፈች፣ ለእኛ የተሰጠ የጌታ የሰላም መልእክት” (ለትምህርት እና ቃል ኪዳን 88መግቢያ) ብሎ የጠራው ራዕይ ነበር። ይህም አስደናቂ ራዕይ የሚያነሳሳ ግብዣ በተጨማሪም ነበረው፣ “ወደ እኔ ቅረቡ እና ወደእናንተ እኔም እቀርባለሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳን 88:63)። የከርትላንድ ቅዱሳን ወደ ጌታ ሲቀርቡ፣ የሰማይ በረከቶችን በታማኞች ራስ ላይ በማፍሰስ በእውነትም ወደ እነርሱ ቀረበ።
ከመጠን በላይ መንፈሳዊ ስጦታ
የእነዚህ መንፈሳዊ መገለጥ መፈጸሚያም የደረሰው በመጋቢት 27፣ 1836 (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ቤተመቅደስ በሚቀደስበት ጊዜ ነበር። በእዚያ ከነበሩት አንዱ፣ ቀኑን እንደ “በዓለ ሀምሳ” የገለጸው፣ የ28 አመት ዊልያም ድሬፐር ነበር። እንዲህም ጻፈ፧ “የጌታ መንፈስ ከመጠን በላይ የሚፈስበት ጊዜ ስለነበር፣ በሙሉ ለመጻፍ እስክሪብቶዬ እና ለመግለፅ ምላሴ ብቁ አደሉም። ነገር ግን በእዚያ የነበሩት በቋንቋ እንዲናገሩ እና ራዕይ እንዲኖራቸውና መላእክትን እንዲያዩና እንዲተነብዩ፣ እና በዚህ ትውልድ ታውቆ የማይውቅ የደስታ ጊዜ እንዲኖራቸው ዘንድ፣ መንፈስ ፈሰሰ እና እንደ ሀይለኛ ነፋስ ነፈሰ እና ቤትን ሞላ ለማለት እችላለሁ።”3
እነዚህ የመንፈስ መግለጥ በቤተመቅደስ ውስጥ ለነበሩት ብቻ የተገለጠ አልነበረም፣ “በአካባቢው የነበሩት ህዝቦችም (በውስጥ ልዩ የሆኑ ድምጾችን ሰምተው፣ እና እንደ እሳት ምሶሶ አይነት ብርሀን በቤተመቅደስ ላይ ሲያርፍ አይተው) ጎረቤቶች ሮጠው ተሰበሰቡ፣ እና በእዚያ በነበረው ተደንቀው ነበር።”4
በኋላ የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንት የሆኑት ሎሬንዞ ስኖው (1814–1901)፣ በዚህ በተባረከ ጊዜ በከርትላንድ ውስጥ ይኖሩ ነበር። እንዲህም አሉ፣ “እነዚህን አስደናቂ መገለጥን ከተቀበሉ በኋላ ቅዱሳንን ምንም አይነት ፈተና ሊያደናቅፋቸው የሚችል የለም ብሎ የሚያሳምን ነበር።”5
ነገር ግን፣ ታላቅ መንፈሳዊ አጋጣሚዎች ከፈተናዎች እና ከተቃራኒዎች ነጻ የሚያደርጉን አይደሉም። ቤተመቅደሱ ከተቀደሰ በኋላ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ላይ የኢኮኖሚ ችግር መጣ፣ እና ከርትላንድም ይህን በጥልቅ ተሰማት። ባንክ ቤቶች ብዙዎችን በገንዘብ ችግር ላይ ጥለዋቸው ወደቁ። ችግርን ለማባዛትም፣ ወደ ከርትላንድ ከሀገራቸው ወጥተው የመጡት፣ እዚያ ከደረሱ በኋላ ምን እንደሚያደርጉ ወይም እንዴት እንደሚኖሩ ሳያውቁ፣ ትንሽ ንብረቶች ይዘው ነበር የመጡት።
ከብዙም ጊዜ በፊት፣መስደድ ተጀመረ እና በቅዱሳን ላይም ለአመፅ የተነሱ ቡድኖች ተጀመሩ። የቤተክርስትያኗ አባሎች—እንዲሁም በቤተመቅደስ መቀደስ ጊዜ የነበሩት፣ ለነብዩ ቅርብ የነበሩት—አመጹ እና ጆሴፍን እንደ ወደቀ ነቢይ አወገዙት።
በከርትላንድ ቤተመቅደስ አጠገብ ከባለቤቴ እና ከልጅ ልጆቼ ጋር አብሬ ስሄድ፣ እንዴት አንዳንዶች የመንፈስ መገለጥን በምስክርነት ከተመለከቱ በኋላ እንዴት በታማኝነት ለመቅረት አለመቻላቸው እንዴት አሳዛኝ እንደሆነ አሰላስልኩበት። የማያምኑትን ስድበች እና ግሰጻ ለመፅናት አለመቻላቸው እንዴት አሳዛኝ ነበር። በገንዘብ ፈተና ወይም በሌሎች ስቃዮች ሲፈተኑ፣ በታማኝነት ለመቆየት በውስጣቸው ጥንካሬን ለማግኘት አለመቻላቸው እንዴት የሚያሳዝን ነው። በቤተመቅደስ ቅደሳ ጊዜ የነበረውን ተምራታዊ የመንፈስ አዝመራን በመርሳታቸው እንዴት የሚያጸጽት ነበር።
ትምህርቶች
ከዚህ ከቤተክርስትያኗ ታሪክ አስደናቂ ዘመን ምን ለመማር እንችላለን?
የከርትላንድ ዘመን የሚጸና አንድ ትምህርት ቢኖር መንፈሶቻችን ፅኑ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው ነው። ፕሬዘንደት ሔሮል ቢ ሊ (1899–1973) እንዳስተማሩት፧ “ምስክር አሁን ያላችሁ እና ሁልጊዜም የምትጠብቁት ነገር አይደለም። በምናደርግበት ላይ በመመካት፣ ምስክር አድጎ እና ወደ እርግጠኛነት ብልፅግና የሚያድግ፣ ወይም እየመነመነ የሚቀነስ ነው። እኔም ቀን በቀን የምናገኘው ምስክር ከጠላት መጥመጃ የሚያድነን ነገር ነው እላለሁ።6 ሁላችንም መጋጠም ካለብን ጠላት ለመዳን በጌታ ሁልጊዜም በቅርብ መቆየት ያስፈልገናል።
በአንዳንድ ሁኔታዎችም የዛሬው አለማችን ከ1830 (እ.አ.አ) ከርትላንድ ጋር አንድ አይነት ነው። እኛም በገንዘብ ችግር ጊዜ ነው የምንኖረው። ቤተክርስትያኗን እና አባሎቿን የሚሳድዱ እና የሚሰድቡ አሉ። የግለሰብ እና የቡድን ፈተናዎች አንዳንዴ የሚያጥለቀልቁ ይመስላሉ።
በእዚያም ጊዜ ነው ከሌላ ጊዜ በላይ ወደ ጌታ መቅረብ የሚያስፈልገን። ይህን ስናደርግ፣ ጌታ ወደ እኛ መቅረቡ ምን ማለት እንደሆነ እናውቃለን። በተጨማሪ ትጋት እርሱን ስንፈልግ፣ በእርግጠም እናገኘዋለን። ጌታ ቤተክርስትያኑን እና ታማኝ ቅዱሳኑን እንደማይተውም በግልፅ እንመለከታለን። አይኖቻችን ይከፈታሉ፣ እና የሰማይ መስኮቶችን ሲከፍት እና ተጨማሪ ብርሀኑን ሲያፈስብንም እናያለን። መንፈሳዊ ጥንካሬን በማታ ጭለማም ለመዳን እናገኛለን።
ምንም እንኳን አንዳንድ የከርትላንድ ቅዱሳን የመንፈስ አጋጣሚዎቻቸውን ቢረሱም፣ ብዙዎቹ አልረሱም። ብዙዎቹም፣ በተጨማሪም ዊልያም ድሬፐር፣ እግዚአብሔር የሰጣቸውን የመንፈሳዊ እውቀት ያዙ እና ነብዩንም በመከተል ቀጠሉ። በመጨረሻም፣ እስከ መጨረሻ የጸኑት “በማያልቅ ደስታ … [እስከሚኖሩ]” ድረስ ሞዛያ (2:41)፣ በጉዞአቸውም ታላቅ ፈተናዎች አጋጠሟቸው ነገር ግን ደግሞም የሚያስደስት መንፈሳዊ እድገትም አጋጠማቸው።
ለፅናት ትችላላችሁ
ተስፋ ለመቁረጥ ወይም እምነት ለማጣት የምትፈተኑ ከሆናችሁ፣ በከርትላንድ በታማኝነት ስለቀሩት እነዚያ ታማኝ ቅዱሳንን አስታውሱ። ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ፅኑ። ይህን ልታደርጉ ትችላላችሁ! እናንተ የልዩ ትውልድ አባሎች ናችሁ። በወብታዊው ምድር ላይ በዚህ በአስፈላጊ ጊዜ ለመኖር የተዘጋጃችሁ እና የተጠበቃችሁ ነበራችሁ። ሰለስቲያል ተመላጅነት አላችሁ እና ስለዚህ ህይወታችሁን የዘለአለም ውጤታማ ታሪክ የማድረግ ችሎታም አላችሁ።
ጌታ በእውነት ምስክር ባርኳችኋል። ተፅዕኖውን እና የሀይሉ ምስክር ተሰምቷችኋል። እርሱን በመፈለግ ከቀጠላችሁ፣ ቅዱስ አጋጣሚዎች ለእናንተ በመስጠት ይቀጥላል። ከእነዚህ እና ሌሎች መንፈሳዊ ስጦታዎች ጋር፣ የእራሳችሁን ህይወት በጥሩ ለመቀየር ከመቻል በተጨማሪ ቤቶቻችሁን፣ ዎርዶቻችሁን ወይም ቅርንጫፎቻችሁን፣ ህብረተሰቦቻችሁን፣ ከተማዎቻችሁን፣ ስቴቶቻችሁን፣ እና ሀገሮቻችሁን በጥሩነታችሁ ለመባረክ ትችላላችሁ።
በእዚያ ጊዜ ይህን ለማየት የሚያስቸግር ይሆናል፣ ነገር ግን ለትንሽ ጊዜም ፅኑ፣ ምክንያቱም “ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት” እና እርሱን ለሚጠብቁት ያዘጋጀው (1 ቆሮንጦስ 2፧9፣ ደግሞም ትምህርት እና ቃል ኪዳን 76፧10ን133፧45ን ተመልከቱ)።
ዳግም ስለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እውነትነት እና ስለዚህች የእርሱ ቤተክርስትያን እውነትነት እመሰክራለሁ። በልቤ እና በነፍሴ በሙሉ እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ልጁ እንደሆነ እና እንደዚህች ታላቅ ቤተክርስትያኑ መሪ እንደቆመ እመሰክራለሁ። አሁንም በምድር ላይ እንደገና ነቢይ አለን፣ እንዲሁም ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን።
የከርትላንድን ትምህርት ሁልጊዜም—እንዲሁም ነገሮች ተስፋ የሚያስቆርጡ ሲሆኑ—እናስታውስ እና ለትንሽም ጊዜ እንፅና። ይህን እወቁ እና አስታውሱ፧ ጌታ ይወዳችኋል። ያስታውሳችኋል። “በእምነት እስከመጨረሻ የሚጸኑትን” ያፅናናቸዋልትምህርት እና ቃል ኪዳን 20፧25።
© 2009 በIntellectual Reserve, Inc መብቱ በህግ የተጠበቀ። በዩኤስኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/09 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/09 (እ.አ.አ)። First Presidency Message, January 2010 (እ.አ.አ) ትርጉም። Amharic. 09361 506