2010 (እ.አ.አ)
የፔትሪያርካል በረከት
ፌብሩወሪ 2010


ወጣቶች

የፔትሪያርካል በረከታችሁ

ፕሬዘደንት ሞንሰን ፔትሪያርካል በረከትን እንደ “አቅጣጫችሁን የሚቀይስላችሁ እና መንገዳችሁን የሚመራችሁ የግል ሊያሆናችሁ” በለው ገልጸውታል። ይህ በረከት ምንድን ነው፣ እና ህይወታችሁን እንዴት ለመምራት ሊረዳችሁ ይችላል?

የፔትሪያርክ በረከት ምንድን ነው?

በረከታችሁ ሁለት አላማዎች አኩት። መጀመሪያ፣ ዘራችሁን፣ ወይም በየትኛው የእስራኤል በት ጎሳዎች አባል እንደሆናችሁ ይገልጻል። ሁለተኛ፣ ለመምራት የሚረዳችሁን መረጃ የያዘ ነው። በረከታችሁ የተስፋ ቃላት፣ መገሰጽያ፣ እና ማስጠንቀቂያ ሊኖረው ይችላል።

በረከቴን ለመቀበል ስንት አመቴ መሆን አለብኝ?

የተወሰነ እድሜ የለም፣ ነገር ግን የበረከቱን ቅዱስ ሁኔታ ለመረዳት ብቁ እድሜ ቢኖራችሁ ይገባል። ብዙ አባላት በረከታቸውን በወጣትነታቸው ለመቀበል ማሰብ ይጀምራሉ።

በረከትን እንዴት እቀበላለሁ?

መጀመሪያ ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ወይም ከቅርንጫፍ ፕሬዘደንታችሁ ጋር ተነጋገሩ። የተዘጋጃችሁ እና ብቁ ከሆናችሁ፣ የብቁነት መዝገብ ትቀበላላችሁ። ከእዚያም በኋላ፣ በአካባቢያችሁ ካሉት ፔትሪያርክ ጋር ቀጠሮ ያዙ።

በበረከቴ ምን አደርጋለሁ?

በሚጠበቅበት ቦታ አስቀምጡት፣ እና በየጊዜውም አንብቡት። በረከታችሁ ቅዱስ እና የግል እንደሆነ አስታውሱ። ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ለመካፈል ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ከሌሎች ህዝቦች ጋር አትካፈሉት። ደግሞም፣ በፔትሪያርክ በረከታችሁ ውስጥ ያሉት በረከቶች በታማኝነታችሁ እና በጌታ ጊዜ ላይ የተመኩ ናቸው።