2010 (እ.አ.አ)
ገንዘብን በጥበብ መቆጣጠር እና ከእዳ መውጣት
ፌብሩወሪ 2010


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ የካቲት 2010 (እ.አ.አ)

ገንዘብን በጥበብ መቆጣጠር እና ከእዳ መውጣት

እነዚህን ቅዱስ መጻህፍትን እና ጥቅሶችን ወይም፣ አስፈላጊም ከሆነ፣ የምትጎበኗቸውን እህቶች ፍላጎት የሚያሟሉትን ሌሎች መሰረቶች አስተምሩ። ስለትምህርቱም ምስክራችሁን ስጡ። የምትጎብኟቸውንም የተማሩትን እና የሚሰማቸውን እንዲካፈሉ ጋብዟቸው።

ገንዘብን መቆጣጠር

“‘በጥበብ መኖር’… ገንዘቦቻችንን [መቆጠብ]፣ የገንዘብ ጉዳዮችን በጥበብ አላማ ማውጣት፣ ለግል ጤንነት በሙሉ አስቀድሞ አላማ ማውጣት፣ እና ለትምህርት እና ለስራ ችሎታ እድገት በብቁ መዘጋጀት፣ በቤት ውስጥ በመስራት እና በማከማቸው እና ስሜታዊ ጥንካሬን በማሳደግ ላይ ትክክለኛ የሆነ ትኩረትን መስጠት ማለት ነው። … በጥበብ እና በወደፊት በመመልከት ከኖርን፣ በእርሱ እጅ ላይ እንደሆንን አይነት ደህና እንሆናለን።”1

ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል (1895–1985)።

በግል የምንመካ ለመሆን እንዲረዱን ምን ችሎታዎች ያስፈልጉናል? … በቤተክርስትያኗ መጀመሪያ ቀናት ውስጥ፣ ብሪገም ያንግ እህቶችን በቤተሰባቸው ህመምን ለማስወገድ እዲማሩ፣ በቤታቸው ውስጥ ምግብ የማከማቸት እና እቃዎችን የመስራት ዘዴዎችን እንዲመሰርቱ፣ እና ሒሳብ እና የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ችሎታን እና ሌሎች የሚረዱ ችሎታዎችን እንዲማሩ ለመኗቸው። እነዚህ መመሪያ መሰረቶች አሁንም ጠቃሚ ናቸው። ትምህርት በጣም አስፈልጊ በመሆን ቀጥሏል። …

“ኤጲስ ቆጶሶችን በዎርዶቻቸው ያሉ እህቶች ምን አይነት ችሎታዎች እንደሚያስፈልጋቸው ጠየኩኝ፣ እነርሱም የገንዘብ መጠንን መወሰን ብለው መለሱ። ሴቶች በብርድ የመግዛትን እና የገንዘብም መጠን በተመደበበት ያለመኖር ያለው ውጤታ እንዲገባቸው ያስፈልጋል። ሁለተኛው ችሎታ ኤጲስ ቆጶሶች የዘረዘሩት ምግብ መቀቀልን ነበር። በቤት የተዘጋጁ እና የተበሉ ምግቦች ብዙም አያስከፍሉም፣ጤንነት ይሰጣሉ፣ እና ለጠንካራ የቤተሰብ ግንኙነትም ይረዳሉ።”2

ጁሊ ቢ ቤክ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት።

እዳን ማስወገድ

“ለገንዘብ ነጻነት አምስት ዋና ደረጃዎችን በሀሳብ ላቅርብ።

“መጀመሪያ አስራትን ክፈሉ።

“ሁለተኛ፣ ወጪአችሁ ከምታገኙት በታች ይሁን።

“ሶስተኛ፣ ለማጠራቀም ተማሩ።

“አራተኛ፣ የገንዘብ ሀላፊነታችሁን አክብሩ።

“አምስተኛ፣ ልጆቻችሁ የእናንተን ምሳሌ እንዲከተሉ አስተምሯቸው።3

የአስራ ሑለት ሐዋሪያት ቡድን አባል ካህን ጆሴፍ ቢ ወርዝልን (1917–2008)።

“በእዳ ውስጥ ስንገባ፣ ውድ እና ዋጋው ታላቅ የሆነውን የነጻ ምርጫችንን ክፍል አሳልፈን እንሰጣለን እና እራሳችንንም በግል በተመደበ አገልጋይነት አናስገኛለን። የተበደርነውን—እኛን፣ ቤተሰቦቻችንን፣ እና ሌሎችን ለመርዳት ለመጠቀም የምንችልበትን ንብረቶችለመክፈል—ጊዜአችንን፣ ሀይላችንን፣ እና ችሎታችንን በግድ እንሰጣለን። …

“አሁን እዳችንን ለመክፈል እና የወደፊት እዳዎችን ለማስወገድ—ጥሩ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ለመሆን—በአዳኝ እምነታችንን መጠቀም ያስፈልገናል። እነዚያን ቃላቶችን ፣ ‘ለማድረግ በቂ ገንዘብ የለንም’፣ ለማለት ታላቅ እምነት ያስፈልገዋል።ሌሎች እና እራሳችን የሚያስፈልገንን ለማሟላት ፍላጎታችንን አሳልፈን ስንሰጥ ህይወት የሚሻል እንደሆነ ለማመን እምነት ያስፈልገዋል።”4

የአስራ ሑለት ሐዋሪያት ቡድን አባል ካህን ሮበርት ዲ ሔልስ።

ማስታወሻዎች

  1. “Welfare Services: The Gospel in Action,” Ensign, ህዳር 1977, 78።

  2. “The Welfare Responsibilities of the Relief Society President,” Basic Principles of Welfare and Self-Reliance (2009), 5

  3. “Earthly Debts, Heavenly Debts,” Liahona, ግንቦት 2004, 41, 42።

  4. “A Gospel Vision of Welfare: Faith in Action,” Basic Principles of Welfare and Self-Reliance (2009), 1።

ለየቤት ለቤት አስተማሪዎች እርዳታዎች

ከጉብኝት ረጂአችሁ ጋር ይህም መልእክት ለእያንዳንዷ እህት ጉዳዮች በጥንቃቄ ለማመሳሰል እንዴት እንደምትችሉ ተመካከሩ። ምን በግል የመተማመን ችሎታዎችን ከእርሷ ጋር ለመካፈል ትችላላችሁ?

የግል ዝግጅት

ሚልክያስ 3፧10

ማቴዎስ 6፧19–21

ሉቃስ 12፧15

ትምህርት እና ቃል ኪዳን 38፧30; 88፧119

ለተጨማሪ መረጃዎች፣ All Is Safely Gathered In: Family Financesን (item no. 04007) ተመልከቱ።

አትም