2010 (እ.አ.አ)
በመንፈሳዊነት የተዘጋጀ ስለመሆን
ፌብሩወሪ 2010


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ የካቲት 2010 (እ.አ.አ)

በመንፈሳዊነት የተዘጋጀ ስለመሆን

ከነብያችን የመጣ ምክር

የእምነት መሰረት

“ጥልቅ የሆነ የእምነት መሰረት እና ጠንካራ የሆነ የእውነት ምስክር ከሌለን፣ ወደ እያንዳንዳችን መምጣታቸው የማይቀሩትን ሀይለኛ አውሎ ነፋሶችን እና ቀዝቃዛ የፈተና ነፋሶችን ለመቋቋም ችግር ይኖረን ይሆናል።

“የስጋ ህይወት የፈተና ጊዜ፣ ወደ ሰማይ አባታችን ፊት ለመመለስ ብቁ እንደሆንን የምናረጋገጥበት ጊዜ ነው። ለመፈተን፣ ችግሮችን እና እዳዎችን መቋቋም አለብን። እነዚህ ሊያዳክሙን ይችላሉ፣ እና የነፍሶቻችን ገጽም ይሰበራል እና ይቆራረሳል—ይህም፣ የእምነት መሰረቶቻችን፣ የእውነት ምስክሮቻችን በውስጣችን በጥልቅ የተቀበሩ አይደሉም ማለት ነው።”1

ከድሮው ትምህርት ተማሩ

“ከሆንነው በላይ የሚሆነውን በእራሳችን ስንፈልግ፣ የተለያዩ ጥያቄዎች አስተሳሰባችንን ይመሩልናል፧ እኔ ለመሆን እንደምፈልገው ነኝ? ትላንትና ከነበርኩት ዛሬ ወደአዳኝ የቀረብኩኝ ነኝ? ነገስ በተጨማሪ ቅርብ እሆናለሁ? በጥሩ ለመቀየር ግብዝና አለኝ? …

“አመቶቹ መጥተዋልም ሄደዋልም፣ ነገር ግን የወንጌል ምስክር አስፈላጊነት ዋና መሆኑ ቀጥሏል። ወደፊት ስንገፋ፣ የድሮውን ትምህርቶች ችላ አንበል።”2

የግል ሊያሆናችሁ

“የፔትሪያርካል በረከታችሁ የእናንተ እና የእናንተ ብቻ ነው። አጭር ወይም ረጅም፣ ውስብስብ ያልሆነ ወይም በጣም ጥልቅ ሊሆንም ይችላል። ረጅምነት እና ቋንቋ ፔትሪያርካል በረከት አያደርጉትም። እውነተኛ ትርጉም የሚሰጠው መንፈስ ነው። በረከታችሁ በጥንቃቄ የሚታጠፍ እና የሚሸጎጡ አይደሉም። በፍሬም ውስጥ የሚቀመጥ ወይም የሚታተምም አይደለም። ነገር ግን፣ መነበብ ይገባዋል። መወደድ ይገባዋል። መከተል ይገባዋል። የፔትሪያርክ በረከታችሁ ከሁሉም በላይ ጭለማ የሆኑትን ማታዎቻችሁን ረድቶ ያሳልፍላችኋል። በህይወት አደጋዎች ውስጥም ይመራችኋል። …የፔትሪያርክ በረከታችሁ አቅጣጫችሁን የሚቀይስላችሁ እና መንገዳችሁን የሚመራችሁ የግል ሊያሆናችሁ ነው። …

“ቃል ለተገባው በረከት ለመሟላት ስንመለከት፣ ስንጠብቅ፣ እና ስንሰራ ትእግስት አስፈላጊ ይሆናል።”3

ወደ እርሱ ኑ

“ብቻችሁን እንደማትሄዱ አስታውሱ። … በህይወት ስትሄዱ፣ ሁልጊዜም ወደብርሀን ተራመዱ፣ እና የህይወት ጥላም ወደኋላችሁ ይወድቃል። …

“ወደ ቅዱስ መጻህፍት ለመነሳሳት ስመለከት፣ በየጊዜው አንድ ልዩ ቃል በግልፅ ይታያል። ያ ቃልም ‘ኑ’ ነውጌታ እንዲህ አለ፣ ‘ወደ እኔ ኑ።’ እንዲህም አለ፣ ‘ኑ ከእኔም ተማሩ።’ ደግሞም እንዲህ አለ፣ ‘ኑ፣ ተከተሉኝ።’ ያን ቃል ኑ እወደዋለሁ። ልመናዬም ወደጌታ እንድንመጣ ነው።”4

ማስታወሻዎች

  1. “How Firm a Foundation,” Liahona, ህዳር 2006, 62

  2. “Becoming Our Best Selves,” Liahona, ሚያዝያ 2006, 3, 5።

  3. “Your Patriarchal Blessing: A Liahona of Light,” Ensign, ህዳር 1986, 66

  4. የ16-ስቴኮች መነሳሻ ስብሰባ፣ ብሪገም ያንግ ዩንቨርስቲ፣ ህዳር 16፣ 1986።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

Teaching, No Greater Call እንደሚለው፧ “ችሎታ ያለው አስተማሪ ፣ … ’ዛሬ ምን አስተምራለሁ?’ ብሎ ሳይሆን፣ ‘የማስተምራቸው ለማወቅ የሚያስፈልጋቸውን እንዴት እንዲያገኙ እረዳቸዋለሁ?’ በማለት ያስባል” ([1999]፣ 61)። ከዚህ አንቀፅ ግለሰቦች እንዲማሩ ለመርዳት፣ ወረቀት እና እርሳስ ስጧቸው እና የፕሬዘደንት ሞንሰንን ቃላቶች እንዲያነቡ እና በመንፈስ ስለመዘጋጀት ያገኟቸውን እውነቶች እንዲፅፉ ጊዜ ስጧቸው። ትንሽ ልጆች ምን እንደተማሩ ስዕል ለመሳል ይችላሉ። የጻፉትን ወይም የሳሉትን እንዲካፈሉ ለማድረግም አስቡበት።