2010 (እ.አ.አ)
የእምነት ሙከራዬ
ኤፕረል 2010


ወጣቶች

የእምነት ሙከራዬ

በ13 አመቴ መፅሐፈ ሞርሞንን በየቀኑ ማንበብ ጀመርኩኝ፣ እና ከእዚያ ጊዜ ጀምሮ በየቀኑ ተባርኬአለሁ።

የ13 አመቶች የሰንበት ትምህርት ክፍላችን በአምልኮአችን የታወቅን አልነበርንም። ነገር ግን፣ እያንዳንዱን ትምህርት በመንፈስ ለማስተማር የምትጥር አስደናቂ አስተማሪ ነበረችን። አንዱ እንደዚህ አይነት ትምህርት ስለ ቅዱስ መጻህፍቶች ማንበብ ነበር።

ከትምህርቱ መጨረሻ ላይ የምንወዳደርበትን ሰጠችን። ይህም ለሁላችንም ነበር፣ ነገር ግን “መፅሐፈ ሞርሞንን በየቀኑ እንድታነቡ አላማ እሰጣችኋለሁ” ስትል ለአንድ ምክንያት እኔን እየተመለከተች ነበር። ለእራሴም፣ “አሳይሻለሁ። አደርገዋለሁ!” ብዬ አሰብኩኝ።

1 ኔፊ ምዕራፍ 1ን በእዚያ ማታ ማንበብ ጀምሬ በየቀኑ ማንበብ ቀጠልኩኝ። ስጀምር ትክክል የሆነ አስተያየት ያልኖረኝ ቢሆንም፣ ከጊዜ በኋላ ግን መፅሐፈ ሞርሞንን በማንበብ የሚሰማኝ ስሜታን መውደድ ጀመርኩኝ። በየማታ ማንበብ የሚያስደስት ጸባይ ሆነ።

ከብዙ ወሮች በኋላ ወደአልማ 32 ደረስኩኝ እና በእምነት ሙከራ ሀስብ ተደንቄ ነበር። በትምህርት ቤት ስለሳይንስ ሙከራ ተምረን ነበር፣ ስለዚህ ተንበረከኩኝ እና የሰማይ አባትን ይህን ሙከራ እየጀመርኩኝ እንደሆንኩኝ ነገርኩት። መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ አውቅ ዘንድም ጠየኩኝ።

ወደኋላ ስመለከት፣ የሰማይ አባት ጸሎቴን በብዙ ጊዜ እንደመለሰለኝ አውቃለሁ። ከመፅሐፈ ሞርሞን በየቀኑ ማንበብ ክፉን ለመቋቋም የተጨመረ ችሎታ ሰጠኝ። ወደ ሰማይ አባቴ ቅርብም ሆንኩኝ። በመንፈስ ቅዱስ ሀይልም የምደናቀፍበትን ለመቋቋም እንደተጠናቀርኩኝም ተሰማኝ። በእግዚአብሔር ቃል ሙከራ ስለማድረግ አልማ ያለው እውነት ነበር፧ “መንፈሴን ከፍ አድርጓልና፤ አዎን ግንዛቤዬን ያበራልኝ ጀምሯል፤ አዎን፣ ለእኔም አስደሳች መሆን ጀምሯል” አልማ 32፧28