የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሚያዝያ 2010 (እ.አ.አ)
የግል ራዕይን መፈለግ እና መቀበል
እነዚህን ቅዱስ መጻህፍትን እና ጥቅሶችን ወይም፣ አስፈላጊም ከሆነ፣ የምትጎበኗቸውን እህቶች ፍላጎት የሚያሟሉትን ሌሎች መሰረቶች አስተምሩ። ስለትምህርቱም ምስክራችሁን ስጡ። የምትጎብኟቸውንም የተማሩትን እና የሚሰማቸውን እንዲካፈሉ ጋብዟቸው።
የግል ራዕይን እንዴት መፈለግ እችላለሁ?
“የግል ራዕይን ለመቀበል ልክ ነብያት እንደሚያደርጉት፣ ቅዱስ መጻህፍትን በማጥናት፣ በመጾም፣ በመጸለይ፣ እና እምነትን በመገንባት፣ እንዘጋጃለን። እምነት ዋና ነው። ለመጀመሪያው ራዕይ ጆሴፍ የተዘጋጀበትን አስታውሱ፧
“‘ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው …እግዚአብሔርን ይለምን፥ …
“ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን።’”1
የአስራ ሑለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል ካህን ሮበርት ዲ ሔልስ።
ጸሎት የእናንተ የግል የሰማይ ቁልፍ ነው። የቁልፍ መክፈቻውም በናንተ በኩል በሚገኘው መጋረጃ ላይ ነው።
“ነገር ግን ይህ ብቻ አይደለም። ራዕይ ያለምንም ጥረት እንደሚፈስ ስላሰበው፣ ጌታ አለ፧
“‘አልተረዳህም፤ በደንብ ሳታስብ እኔን ከመጠይቅህ ባሻገር እንደምሰጥህ ገምተህ ነበር።
ነገር ግን እነሆ፣ እንዲህ እልሃለሁ፣ በአእምሮህ ውስጥ ልታጠናው ይገባል፣ ከዛም ትክክለኛ መሆኑን ልትጠይቀኝ ይገባል እናም ትክክለኛ ከሆነ በውስጥህ ደረትህ እንዲቃጠል አደርጋለሁ፤ ስለዚህ ትክክል እንደሆነ ይሰማሃል።’”2
ፕሬዘደንት ቦይድ ኬ ፓከር፣ የአስራ ሑለት ሐዋሪያት ቡድን ፕሬዘደንት።
የግል ራዕይ እንዴት መቀበል እችላለሁ?
“በሚታወቀው አይነት፣ ራእይ ወይም መነሳሻ የሚመጣው ወደ ዓዕምሮ በሚመጣው ቃል ወይም ሀሳብ፣ (ኢኖስ 1፧10ን ፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳን 8፧2–3ን ተመልከቱ) በድንገት መረዳት (see ትምህርት እና ቃል ኪዳን 6፧14–15) ፣ ድርጊቶችን ለማከናወን ስለቀረበ የጥሩ ወይም መጥፎ ስሜታ፣ ወይም በድራማ አይነት አነሳሽ ጨዋታዎች ነው። የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን ፕሬዘደንት የሆኑት ፕሬዘደንት ቦይድ ኬ ፓከር እንዳሉት፣ ‘በመነሳሳት የሚመጣው እንደ ድምጽ ሳይሆን እንደ ስሜታ ነው።’”3
የአስራ ሑለት ሐዋሪያት ቡድን አባል ካህን ዳለን ኤች ኦክስ።
“ቤተመቅደስ የመማሪያ ቤት ነው። ብዙው በቤተመቅደስ ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት ምሳሌአዊ እና በመንፈስ የምንማረው ነው። ይህም ማለት ከበላይ እንማራለን ማለት ነው። … ወደ ቤተመቅደስ ስለዘለአለም እውነት የሚያስተምሩትን በመማር እና በማሰላሰል ጸባይ በየጊዜው ስንሄድ ስለስነ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ትርጉሞች የሚገቡን ይጨምራሉ። … ወደቤተክርስትያን በየጊዜው ስንሄድ የምንቀበለውን የመንፈስ ጥንካሬን እና ራዕይን እንደሰትባቸው።”4
ስልቪያ ኤች ኦልረድ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ።
© 2010 በIntellectual Reserve, Inc መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩኤስኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/09 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/09 (እ.አ.አ) Visiting Teaching Message, March 2010 (እ.አ.አ) ትርጉም። Amharic. 09364 506