2010 (እ.አ.አ)
የእግዚአብሔር ታላቅ ስራ
ኤፕረል 2010


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሚያዝያ 2010 (እ.አ.አ)

የእግዚአብሔር ታላቅ ስራ

ሚያዝያ 6፣ 1830 ዓ/ም (እ.አ.አ)

ከአንድ መቶ ሰማንያ አመት በፊት፣ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ኦሊቨር ካውደሪ፣ እና ቁጥራቸው ትንሽ የሆኑ ሌሎች የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስያንን ለማደራጀት ተሰበሰቡ። ባሉት ታሪኮች ሁሉ ይህ ያልተወሳሰበ እና መንፈሳዊ ስብሰባ ነበር። ቅዱስ ቁርባንን ተከትሎ፣ “መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ መንፈስ ቅዱስ በታላቅ ደረጃ ፈስሶብን ነበር—ሁላችንም ጌታን ስናሞግስ እና በጣም ስንደሰት፣ አንዳንዶች ተነበዩ” ብሎ ጆሴፍ ፅፎ ነበር።1

የእዚህ ቀን ድርጊቶች በአለም ትኩረት አልተሰጣቸውም ነበር፤ የጋዜጣ ርእስ ወይም የአዋጅ ነጋሪ የተከተላቸውም አልነበሩም። ይህም ቢሆን፣ ሰማያት እንዴት እንደተደሰቱ እና እግዚአብሔርን እንዳሞገሱ—በእዚያ ቀን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ወደምድር ተመልሳለችና።

ሰለሞን ቼምበርልን

ከእዚያ ቀን እስከዚህ፣ ብዙ ሚልዮን የሆነ የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች በመንፈስ ቅዱስ መነሳሳትን ተከትለዋል እና ወደተቀደሱት የጥምቀት ውሀዎችም ገብተዋል። እንደእዚህ አይነት አንድ ሰውም ሰለሞን ቼምበርልን ነበር።

ሰለሞን መንፈሳዊ ሰው ነበር እና የኀጥያቶቹን ስርየት በመፈለግ እና ሰማይ አባትን ወደእውነት እንዲመራው በመለመን በጸሎት ብዙ ሰአቶች አሳልፎ ነበር። በ1816 ዓ/ም (እ.አ.አ) አካባቢ፣ ሰለሞን በራዕይ የክርስቶስ ቤተክርስትያን በሐዋሪያት ስርዓት በኩል እንደገና በምድር ላይ የምትመሰረትበትን ቀን ለማየት እንደሚኖር ቃል ተገባለት።

ከአመቶች በኋላ ሰለሞን በጀልባ ወደ ካናዳ በሚጓዝበት ጊዜ ጀልባው ፓልማይራ ኒው ዮርክ በምትባለው ትንሽ ከተማ ላይ ቆመች። እዚያም ከጀልባው እንዲወርድ የሚገፋፋው ጠንካራ ስሜታ ተሰማው። ለምን በእዚያ እንደሚገኝ ሳያውቅ፣ ከከተማዋ ሰዎች ጋር መነጋገር ጀመረ። “ስለወርቅ መፅሐፍ ቅዱስ” ለመስማትም ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም። እነእዚያ ሁለት ቃላቶች “ ከጭንቅላቱ ላይ እስከ የእግር ጣቶቹ እንደሚሰሙ እንደ ኤሌክትሪክ ሀይል” በሰውነቴ ያለፉ መሰለኝ አለ።

ጥያቄዎቹም እዚያ ካሉትም ጋር ዳግሞ ስለተመለሰው አስደናቂ ዜናዎች ወደተነጋገረበት ወደ ጆሴፍ ስሚዝ ቤት ወሰደው። እዚያ ሁለት ቀናት ካሳለፈ እና ስለእውነት ምስክርን ከተቀበለ በኋላ፣ ሰለሞን 64 የታተሙ እና ገና ያልተሸፈኑ የመፅሐፈ ሞርሞን ገጾችን ይዞ ወደ ካናዳ ጉዞውን ቀጠለ። በሄደበትም ሁሉ፣ “በህብረተሰቡ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የሆኑትን፣ ሀብታም እና ደሀን …ወደምድር ሊመጣ ስለሆነው ለእግዚአብሔር ታላቅ ስራ እንዲዘጋጁ” ህዝቦችን አስተማረ።2

የእግዚአብሔር ታላቅ ስራ

ከእዚያ ከሚያዝያ 1830 ዓ/ም (እ.አ.አ) ቀን ጀምሮ፣ ብዙ ሚልዮኖች ዳግም የተመለሰውን ወንጌል እውነት አግኝተዋል እና ወደ ጥምቀት ውሀዎችም ገብተዋል። ይህ “የእግዚአብሔር ታላቅ ስራ” ዛሬ በመድር ላይ እንደሆነ እመሰክራለሁ። ጌታ ቤተክርስትያኑን እንደሚጠብቅ እና በነብዩ፣ በፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ እንደሚመራት እመሰክራለሁ። በእነዚህ በኋለኛ ቀናት መኖር ልዩ የሆነ በረከት ነው። እነዚህ በጥንት ነብያት አስቀድሞ የታወቀ እና በሚከታተሉ፣ ማላእክታዊ ሰራዊቶች የሚከታተሉ አስገራሚ ጊዜዎች ናቸው። ጌታ ስለቤተክርስትያኑ ያስባል እንደ ሰለሞን ቼምበርልን የመንፈስ ቅዱስ መነሳሻን የሚከተሉትን እና ይህን የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራ ለማምጣት ለመርዳት በአለም ውስጥ ከወንድሞቻቸው እና ከእህቶቻቸው ጋር አብረው የሚሰሩትን ያስብባቸዋል።

ማስታወሻዎች

  1. Joseph Smith, in History of the Church, 1፧78።

  2. “A Short Sketch of the Life of Solomon Chamberlain,” typescript, Church History Library (on the Internet at www.boap.org/LDS/Early-Saints/SChamberlain.html); see also William G. Hartley, “Every Member Was a Missionary,” Ensign, መስከረም 1978, 23። ቤተክርስትያኗ ከተደራጀች ከትንሽ ቀናት በኋላ፣ ሰለሞን ቼምበርልን በኒዎርክ ሴነካ ሀይቅ ውሀዎች ውስጥ በጆሴፍ ስሚዝ ተጠመቀ።

ከእዚህ መልእክት ማስተማር

ካሉን የማስተማሪያ መሳሪያዎች ከሁሉም በላይ ሀይለኛ የሆነው የግል ምሳሌ ነው” (Teaching, No Greater Call [1999], 18)።የሰለሞን ቼምበርሊንን ታሪክ ስትካፈሉ ፣ የምንፈስ መነሳሻዎችን የተከተለበት ጊዜዎች እንዲያስታውሱ ቤተሰብን ጋብዟቸው። ምሳሌም እንዴት ሌሎችን ለመርዳት እንደቻለ ተወያዩበት። የቤተሰብ አባላት እንዴት የአንድ ሰው ምሳሌ እንደረዳቸው እንዲካፈሉ ጋብዟቸው።

አትም