ወጣቶች
የእራሴ መፅሐፈ ሞርሞን
በነሐሴ 2005 (እ.አ.አ)፣ ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሒንክሊ [1910–2008 (እ.አ.አ)] ለቤተክርስትያኗ አባላት መፅሐፈ ሞርሞንን ከአመቱ መጨረሻ በፊት እንዲያነቡ መፈታተኛ ሲያቀርቡ፣ መፅሐፉን በሙሉ ለማንበብ ለእራሴ ቃል ገባሁ። የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮችን ባውቃቸውም፣ ይህን በሙሉ አንብቤ አልጨረስኩም ነበር። አሁን የገባሁትን ቃል ለማክበር ወስኜ ነበር።
ቅዱስ መጻህፍትን በህይወቴ እንድጠቀምባቸው እና የእራሴም እንዳደርጋቸው ተምሬ ነበር። ስለዚህ ሳነብ ከገጹ ጫፍ ላይ የመልእክቱ ዋና ሀሳብ ምን እንደሆነ እንደማስብ ጻፍኩኝ። የተደጋገሙትን ቃላት እና የተደራደሩ ቃላትን ትኩረት ለመስጠት ከስራቸው አሰመርኩኝ።
ለሌሎች የተነገሩት የእግዚአብሔር ቃላት ለእኔም የተነገሩ ቃላት እንዲሆኑ ዘንድ በቅዱስ መጻህፍት ውስጥ ካሉት ስሞች አጠገብ ስሜን ጻፍኩኝ። ለምሳሌ፣ በ2ኛ ኔፊ 2:28 ውስጥ ስሜን ጻፍኩኝ፧ “እናም አሁን፣ [ሂለሪ]፣ በታላቁ አማላጅ እንድትመኩ እናም ታላቅ ትዕዛዛቱን እንድትሰሙ… እፈልጋለሁ።” መፅሐፈ ሞርሞንን በተጨማሪም የእራሴ ሳደርገው፣ በየቀኑ ይህን ስለማነብ በጣም ተደሳች ሆንኩኝ።
በየቀኑ ሳነብ፣ ጸሎቴም ከልብ የመጡ እና የራሴም ሆኑ። በትምህርቴም ማተኮርና ከሌሎች ጋር ጓደኛ እንድሆን በመንፈስ የምገፋፋበትን ማዳመጥ ቻልኩኝ። በአመቱ የመጨረሻ ምሽት ላይ መፅሐፈ ሞርሞንን ጨረስኩኝ።
መፅሐፈ ሞርሞንን፣ ከሌሎች ቅዱስ መጻህፍት ጋር፣ የማንበብ አስፈላጊነት ገባኝ፣ እናም በህይወቴ ውስጥ ለብዙ ጊዜዎች ይህን ለማድረግም እፈልጋለሁ።