የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መስከረም 2010 (እ.አ.አ)
መፅሐፈ ሞርሞን እንደ ግል መመሪያ
ከሁሉም በሚሻሉት ጊዜአችን፣ ሁላችንም ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ወደቤት ለመመለስ ፍላጎት ይሰማናል። መንገዱን ለመስጠት እና እንዴት እንደምንከተለው ለማስተማር ውድ ልጁን አዳኛችን እንዲሆን በስጦታ ሰጥቶናል። መንገዱንም እንዲጠቅሙልን ነቢያትን ሰጥቶናል። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የነቢያት መዝገብ የሆነውን መፅሐፈ ሞርሞንን እንዲተረጉም ተነሳስቶ ነበር። ይህ ወደ ቤት ወደ እግዚአብሔር በምንጓዝበት መንገድ እርግጠኛ መመሪያችን ነው።
ይህን ውድ መፅሐፍ በተመለከተ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ ብሏል፧ “ለወንድሞች መጽሐፈ ሞርሞን በምድር ካሉ መጽሐፍት በሙሉ የበለጠ ትክክል እንደሆነ፣ እናም የኃይማኖታችን የማዕዘን ድንጋይ እንደሆነና ከማንኛውም ሌላ መጽሐፍ በበለጠ በውስጡ ባሉት አስተያየቶች በመኖር ሰው ወደ እግዚአብሄር ሊቀርብ እንደሚችል ነገርኳቸው።”1
የመፅሐፈ ሞርሞን አስተያየቶች በውስጡ የምናገኛቸው የእግዚአብሔር ትእዛዛቶች ናቸው። አንዳንዶቹ ከአዳኝ በነቢያቱ በኩል የመጡ ምን እንደምናደርግ እና ምን መሆን እንዳለብን የሚገልጹልን ትእዛዛት ናቸው። መፅሐፈ ሞርሞን እምነታችንን እና የእርሱን ትእዛዛት ለመከተል ውሳኔአችንን ለማጠናከር መፅሐፈ ሞርሞን የአዳኝን ምሳሌ ይሰጠናል። መፅሐፉ እንድንመራበት በክርስቶስ ትምህርቶች የተሞላ ነው። ይህ ከ2ኛ ኔፊ የመጣ ምሳሌ ነው፧
“[ኢየሱስ] ለሰዎች ልጆች፣ እኔን ተከተሉኝ አለ። ስለዚህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ የአብን ትዕዛዛት ለመጠበቅ ፈቃደኞች ከመሆን በስተቀር ኢየሱስን ልንከተለው እንችላለን?
“እናም አብ እንዲህ ይላል፥ ንስሀ ግቡ፣ ንስሀ ግቡ፣ እናም በተወደደው ልጄ ስም ተጠመቁ።” 2 ኔፊ 31፧10–11።
በጠበበውና በቀጠነው መንገድ ላይ ለመቆየት እንዲረዳን እንደ እሳት ጥምቀት መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንዳለብን መፅሐፉ ግልፅ ያደርግልናል። ሳንታክት ዘወትር መጸለይ እንዳለብን፣ እና ይህን ካደረግን ይህ ቃል ኪዳን እንደሚኖረን ተምረናል፧ “ስለሆነም ፍጹም የሆነ የተስፋ ብርሃን፣ እናም የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር እየኖራችሁ በክርስቶስ ባላችሁ ፅኑነት መቀጠል አለባችሁ። ስለሆነም አብም፣ የክርስቶስን ቃል በመመገብ፣ እናም እስከመጨረሻው በመፅናት የምትቀጥሉ ከሆነ፣ እነሆ አብ እንዲህ ይላል፧ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል 2 ኔፊ 31፧20።
ለእግዚአብሔር እና ለሁሉም ሰዎች ፍቅር ሲኖረን ምን ማለት እንደሆነ መፅሐፈ ሞርሞን በንጉስ ቢንያም ስብከት ውስጥ ግልፅ ያደርግልናል። በኃጥያት ክፍያ ሀይል እና ለትእዛዛት ባለን ታማኝ ታዛዥነት በኩል ፍጥረታችን ሲቀየር፣ በእግዚአብሔር ፍቅር እንሞላለን (ሞዛያ 4፧1–12 ተመልከቱ)።
መፅሐፈ ሞርሞንም በዚህ ህይወት ንጹህ ሆነን ክፋትን ለመፈጸም ምንም ፍላጎት የማይኖረን ለመሆን እንደምንችልም ልበ ሙሉነትን ይሰጣናል። (ሞዛያ 5:2 ተመልከቱ)። ይህ ተስፋ በመንገዱ ላይ እያለን ሰይጣን ሊፈትነን እና ተስፋ ሊያስቆርጠን ሲሞክር መበረታቻና መፅናኛ ይሰጠናል።
ከመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ትንሽ መስመሮችን ሳንብ፣ ይህ መፅሐፍ እውነተኛ እንደሆነ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ፣ እርሱን ወደቤት ለመከተል እንደምንችል፣ እና የምንወዳቸውንም ከእኛ ጋር ወደቤት ለመውስድ እንደምንችል ያልኝ ምስክር ሲጠናከር ይሰማኛል። ለእኔ ይህ ከመፅሀፍት ሁሉ ታላቅ የሆነልኝ ነው። ይህም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
እኛ እና የምንወዳቸውም ከዚህ በጥልቅ እና በየቀኑ እንደሚጠጡ ጸሎቴ ነው። እውነተኛ መመሪያ እንደሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለሁ።
© 2010 በIntellectual Reserve, Inc መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩኤስኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/09 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/09 (እ.አ.አ) First Presidency Message, September 2010 (እ.አ.አ) ትርጉም። Amharic። 09369 506