2011 (እ.አ.አ)
በህይወቴ ውስጥ የነበሩት ብዙ ሚስዮኖች
ፌብሩወሪ 2011


ወጣቶች

በህይወቴ ውስጥ የነበሩት ብዙ ሚስዮኖች

ከሚስዮኖች ጋር ወደ ቤተክርስቲያን በሄድኩበት በመጀመሪያው ሰንበት፣ በመንደሬ ውስጥ አብሬአቸው ያደኩትንና የማውቃቸውን ሰዎች አየሁ። ከትምህርት ቤት ጥሩ ጓደኛዬ የነበረቸውን፣ የመጀምሪያ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ጸሀፊዎችን፣ በድሮ ክፉ ያደረኩባትን አንድ ልጅ፣ እና አንድ ጊዜ እወደው የነበረውን ልጅ አየሁ።

እያንዳንዶቹም ከእኔ ጋር ይቆይ የነበረ ተፅዕኖ ነበራቸው። ጥሩ ጓደኛዬ ታማኝነት የነበራት ወጣት ሴት ነበረች፣ እናም በእርሷም ምክንያት ስለቤተክርስትያኗ መማር ጀመርኩኝ። ከትምህርት ቤት ያስታወሱኝ ጸሀፊዎቹ አስፈላጊ እንደሆንኩኝ አስተማሩኝ። ስለአምላካዊ ፍቅር እና ልግስና ድሮ ክፉ ሆኜባት ብኖርም ባቀፈችኝ ወጣት ሴት ምክንያት ተማርኩኝ። በወጣትነቴ እወደው የነበረውም ጥሩ ምሳሌ ሰጠኝ፣ ብርሀኑን አወኩኝ እናም በእርሱ አካባቢ ለመገኘት ፈለግኩኝ።

እነዚህ አጋጣሚዎች ከሚስዮኖች ጋር ከመገናኘቴ በፊት፣ የሰማይ አባት ወጌልን ለመቀበል በአካባቢዬ ባሉት ሰዎች እንዳዘጋጀኝ እንድማር ረድተውኛል። ከእነርሱም ትትንሽ ነገሮች ትልቅ ውጤት እንደሚኖራቸው ተማርኩኝ። ከሁሉም በላይ፣ የሚስዮን ስራ የሚጀምረው ከእኔ እንደሆነም ተማርኩኝ።